Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2022
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 22nd, 2022

Psychologist Dr. Jordan Peterson on the Crucifixion of Christ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2022

✞✞✞ Day 6: Trial, Crucifixion, Death, and Burial on Good Friday

Friday’s events are recorded in Matthew 27:1-62, Mark 15:1-47, Luke 22:63, Luke 23:56, and John 18:28, John 19:37.

In the early morning hours, as Jesus’ trial was getting underway, Peter denied knowing his Master three times before the rooster crowed.

Good Friday is the most difficult day of Passion Week. Christ’s journey turned treacherous and acutely painful in these final hours leading to his death.

According to Scripture, Judas Iscariot, the disciple who had betrayed Jesus, was overcome with remorse and hanged himself early Friday morning.

Meanwhile, before the third hour (9 a.m.), Jesus endured the shame of false accusations, condemnation, mockery, beatings, and abandonment. After multiple unlawful trials, He was sentenced to death by crucifixion, one of the most horrible and disgraceful methods of capital punishment known at the time.

Before Christ was led away, soldiers spit on him, tormented and mocked him, and pierced him with a crown of thorns. Then Jesus carried His cross part of the way to Calvary and then a man named Simon was compelled to carry it the rest of the way. At Calvary, Jesus was again mocked and insulted as Roman soldiers nailed Him to the wooden cross.

Jesus spoke seven powerful statements from the cross, including “Father, forgive them, for they do not know what they are doing” (Luke 23:34, NIV), “Father, into your hands I commit my spirit” (Luke 23:46, NIV), and His last words were, “It is finished” (John 19:30).

Then, about the ninth hour (3 p.m.), Jesus breathed his last breath and died.

By 6 p.m. Friday evening, Nicodemus and Joseph of Arimathea took Jesus’ body down from the cross and lay it in a tomb.

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Psychology, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2022

ልክ አሁን የሕማማተ መስቀልን ፀሎት አንብቤ እንደጨረስኩ፤ ከጎረቤቴ ሕንጻ ጣራ ላይ ፲፫ ርግቦች ተነስተው በዙሪያዬ አንድ ጊዜና በአንድ ላይ ጅው ብለው በመብረር የተነሱበት ጣራ ላይ ተመልሰው አረፉ። ተገርሜ በመመሰጥ፤ “ምን የሚሉኝ ነገር ሊኖር ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ ጠየቅኩ። ፲፫/13ቱ ሕማማተ መስቀል?

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ “የድኅነት ቀን” ይባላል

✞ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል

  • ፩ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
  • ፪ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
  • ፫ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
  • ፬ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
  • ፭ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
  • ፮ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
  • ፯ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
  • ፰ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
  • ፱ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
  • ፲ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
  • ፲፩ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
  • ፲፪ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
  • ፲፫ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)

✞ ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

  • ፩. ፀሐይ ጨለመ፤
  • ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
  • ፫. ከዋክብት ረገፉ፤
  • ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
  • ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
  • ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
  • ፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡

✞ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

  • ፩. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”፤
  • ፪. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ”፤
  • ፫. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው”፤
  • ፬. እመቤታችንን “ሴትዮሆይ፣እነሆልጅሽ”፤ ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
  • ፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”
  • ፮. “ተጠማሁ”፤
  • ፯. “ዅሉተፈጸመ” (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ “ወፍናሠርክይ በርህ ብርሃነ ፀሐይ” እንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖለእግዚአብሔር” እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Good Friday Crucifixion | ዓርብ ስቅለት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2022

✞✞✞ ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) –የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት✞✞✞

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር” በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤” አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት “ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ ወኀጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንምከፍርድአታድን፤” ትላለችና “እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤” ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ “በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞችነን፤” ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡

ልክ አሁን የሕማማተ መስቀልን ፀሎት አንብቤ እንደጨረስኩ፤ ከጎረቤቴ ሕንጻ ጣራ ላይ ፲፫ ርግቦች ተነስተው በዙሪያዬ አንድ ጊዜና በአንድ ላይ ጅው ብለው በመብረር የተነሱበት ጣራ ላይ ተመልሰው አረፉ። ተገርሜ በመመሰጥ፤ “ምን የሚሉኝ ነገር ሊኖር ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ ጠየቅኩ። ፲፫/13ቱ ሕማማተ መስቀል?

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: