Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2022
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 19th, 2022

Easter Bunny: America, Your President Looks Dazed, Confused & Sick – He Needs Medical Attention!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2022

🐇 የፋሲካ ጥንቸል፤ አሜሪካ ሆይ፣ ፕሬዝዳንትሽ ደንግጠዋል፣ ግራ ተጋብተዋል፣ ታመዋል ፥ የህክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል!

💭 It’s so important to make sure you take good care of Joe Biden – more than Vladimir Putin!

💭 ጆ ባይደንን በጥሩ ሁኔታ መንከባከብሽን ማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ነው ከቭላድሚር ፑቲን የበለጠ!

🐇 The Easter Bunny was seen moving a “confused” Joe Biden along after he “wandered off” to answer questions and take selfies with kids at the White House’s Easter Egg Roll.

The president began discussing Pakistan and Afghanistan with a crowd before the bunny was seen ushering him away in a video which was first posted to Twitter by journalist journalist Thomas C. Dillon.

Former California House candidate Buzz Patterson commented on the video: “Some staffer in a bunny outfit interrupts the most important person in the world. Only in Biden’s America”.

👉 Courtesy: Sky News

_____________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Health, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Muslims Attack Easter Week Processions in Spain | ሙስሊሞች በእስፔን ውስጥ የሰሙነ ሕማማት ሂደቶችን አጠቁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2022

💭 Muslim Youths Attack Easter Week Processions in Spain — Pelt Christians with Rocks and Projectiles

😈 የተለመደው የሰይጣናዊው ረመዳን ጂሃድ መሆኑ ነው! መሀመድ ከሲዖል ፊሽካ ነፍቶላቸው ነው። በሃገራችንም የምንጠብቀው ነው!

ባለፈው ሳምንት ላይ ባርሴሎና አቅራቢያ በምትገኘዋ የኤል ቬንድሬል ከተማ(ታራጎና፤ እስፔን)፣ በካቶሊኮቹ ሰሙነ ሕማማት/ቅዱስ ሳምንት ወቅት ከሰሜን አፍሪካ የመጡ መሀመዳውያን ሰፋሪዎች እንደተለመደው በዓሉን በየዕለቱ ለማክበር በወጡት ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። የፖሊስ ምንጮች እንደገለፁት፤ ሁለቱም የታሰሩት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች የ፳፬/24 አመት እድሜና የሞሮኮ ዜግነት ያላቸው መሀመዳውያን ናቸው።

ላለፉት ሁለት ዓመታት በኮሮና ሳቢያ በአደባባይ ማክበር ተከልክሎ የነበረው ይህ ዝነኛው የእስፔን ሰሙነ ሕማማት ወይንም የቅዱስ ሳምንት በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ቱሪስቶችን ሳይቀር ከየአቅጣጫው በመሳብ የሚታወቀው ክብረ በዓል በካቶሊክ ክርስቲያኖች ዘንድ በታላቅ ስሜት ዘንድሮም ተከብሮ ውሏል። በርካታ ከተሞችና መንደሮች ሰሙነ ሕማማትን/የቅዱስ ሳምንትን በየጎዳናዎችና አደባባዮች ነው በታላቅ ድምቀት የሚያከብሩት። በተለያዩ ጉዞዎችና በዓላት ደረጃዎችን ወይም ዙፋኖችን፣ መስቀሎችን፣ የጌታችንንና የእመቤታችንን ስዕሎችንና ከባባድ ሐውልቶችን፤ ልክ እንደኛ ጥምቀት ከተራ ታቦታት፤ ለረጅም ርቀት በመሸከም ተመስጠው ይጓዛሉ/ይንቀሳቀሳሉ።

ይህ ወቅት በደቡባዊው እስፔን በአንዳሉሲያ በከበሮ እና ጥሩምባ የታጀበ በጣም ደማቅ ክብረ በዓል ነው። በቀንም በሌሊትም ጎዳናዎች በከበሮና ጥሩምባ የታጀቡ ዜማዎችን፣ የአበቦች ቀለም እና የቅዱሳን ስዕሎች፣ ቅርፃቅርፆችና ኃውልቶች ጥበብ የሚቀላቀሉባቸው ቦታዎች ይሆናሉ፣ በዚህም ስሜትን የሚነካ ምስል ይፈጥራል። በጣም ዝነኛው የሴቪያ ከተማ የቅዱስ ሳምንት አከባበር ነው። እኔ ብዙ ጊዜ ይህን ክብረ በዓል በቦታው ተገኝቼ ለመታዘብ ዕድሉ ነበረኝ። እጅግ በጣም የሚመስጥና የሚያነቃቃ ክብረ በዓል ነው። ይህን ደግሞ ከፊሉን የደቡብ እስፔይን ክርስቲያን ሕዝብ ለሰባት መቶ ዓመታት ያህል በእስልምና ባርነት ቀንበር አስረውት የነበሩት መሀመዳውያኑ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች በጣም ነው የሚቃወሙት። ግዜና አጋጣሚ ባገኙ ቁጥርና መሀመድ ከሲዖል ሆኖ ፊሽካ ሲነፋላቸው የተለመደውን ይህን መሰሉን ጽንፈኛ ተግባር በመላው ዓለም ይፈጽማሉ። ይህ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ እስከ ኢየሩሳሌም፣ ስዊደን፣ እስፔንና ሩሲያ/ዩክሬይን ድረስ የሚታየን የረመዳን ጂሃድ ሆን ተብሎ ነው በሑዳዴ ጾም ቀናት የሚካሄደው። ዘንድሮ የሑዳዴ ጾምና የአይሁዶች ፓሻ/ፋሲካ እንዲሁም ሉሲፈራዊው የእስልምና ረመዳን በአንድ ሰሞን ነው እየዋሉ ያሉት። በየአሥር ዓመቱ በአንድ ላይ ይውላሉ። ይህ ደግሞ ለአውሬው ጭንብሉን ይገልጥ ዘንድ ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮለታል።

With Easter processions cancelled for the past two years due to the coronavirus pandemic, Spain’s colourful Holy Week marches make their eagerly awaited return to the streets. The holiday, which runs until Easter Day on April 17, is a time when huge crowds traditionally gather to watch the elaborate processions in this deeply Catholic country. In the southern city of Seville, locals prepare to watch the religious festivities.

A group of Muslim migrants from a local shelter pelted Christians with rocks and projectiles at an Easter procession in Granada, Spain during Holy Week.

This is not the first time this has happened. On Palm Sunday, a group of North Africans had tried to attack the Easter procession in El Vendrell (Tarragona).

A group of unaccompanied minor refugees from the Bermúdez de Castro hostel in Granada disrupted the Catholic procession in the early hours of Holy Thursday morning (…) Fortunately, the quick intervention of the police prevented serious incidents.

Total outrage in Granada. The procession had been on the road for about an hour and a half, and as it went down the Cuesta del Chapiz, a large number of objects began to rain down on those present. All of these projectiles came from the migrant shelter mentioned above, as several sources confirmed.

The president of Vox Granada, Onofre Miralles, condemned the events through his networks: “Yesterday I had the honour of accompanying the procession. I was informed that objects were thrown at the procession from the reception centre for underage migrants. They are directed against our culture and our tradition. I demand action on the part of the Region of Andalusia”.

This is the umpteenth attack on a Catholic procession during Holy Week. It is not the first incident and unfortunately it will not be the last. Last Sunday, a group of North Africans had tried to attack the Easter procession in El Vendrell (Tarragona).

______________

Posted in Ethiopia, Faith, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት (ዘሰሉስ) | ጌታችንን እንደዛሬዎቹ ፈሪሳውያን የጠየቁት የካህናትና የሕዝብ አለቆች ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2022

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡

ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠው ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም አይሁድ ጌታችንን “ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያኝ ካህናት አይደለህ፤ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” የሚል ነበር፡፡ እርሱም ሲመልስ “እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይን? ወይስ በሰው ፈቃድ?” አላቸው፡፡ እነርሱም “ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፡፡” ተባብለው “ከወዴት እንደሆነ አናውቅም” ብለው መለሱለት፤ እርሱም “እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም፡፡” አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቦናቸው በክፋትና ጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡[ማቴ ፳፩፥፳፫፡፳፯]

ዳግመኛም ይህ ዕለት ጌታችን ስለዳግም ምጽአቱ ሰፊ ትምህርት የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ [ማቴ ፳፬ እና ፳፭ እንዲሁም ማር ፲፪ እና ፲፫፣ ሉቃ ፳ እና ፳፩] ላይ የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሠንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡

ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: