Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2022
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

በግእዝ ቋንቋ የምናደርገው ጸሎት በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በእንግሊዝኛና በሌሎች ቋንቋዎች ከምናደረገው ጸሎት የተሻለ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 13, 2022

💭 በግእዝ ቋንቋ የምናደርገው ጸሎት በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በእንግሊዝኛና በሌሎች ቋንቋዎች ከምናደረገው ጸሎት የተሻለ ነው። ቃላቱን በትርጉም ደረጃ ባንረዳቸውም እንኳ የድምጽ አጠራሩ/አገላለጹ ግን ከየትኛውም ቋንቋ የላቀ መንፈሳዊነት ነው ያለው።

በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት ጦርነት አንዱ ዓላማ የግዕዝ ቋንቋን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ነው። አንዳንድ የትግራይ ሜዲያዎች ሰሞኑን በግዕዝ ፋንታ በጨፍጫፊዎቻችን እስማኤላውያን አረቦች ቋንቋ፤ በአረብኛ ዜናዎችን መስራት ጀምረዋል። ዋይ! ዋይ! ዋይ! ቀደም ሲል በኤርትራም እንዲህ ነበር የተደረገው። እንቁላል ቀስበቀስ በእግሩ ይሄዳል! ዓላማው በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነትን፣ ቀጥሎ የግዕዝ ቋንቋን በመጨረሻም ተዋሕዶ ክርስትናን በመንጠቅ የዲያብሎስ ልጅ ማድረግ ነው። እንግዲህ የዋቄዮ-አላህ ጭፍራው የምኒልክ ተልዕኮ እየተሳካ ነው ማለት ነው። ዛሬ ኢትዮጵያዊነታቸውን የተነጠቁት ክርስቲያን ‘ኤርትራውያን፤ “መርሃባ!፣ ምሽ አላህ! ፣ ሹክራል! ላ! ላ! ወዘተ” ሲሉ ይሰማሉ። አረብኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ዮሩባ፣ የሰሜን አውሮፓ ቋንቋዎች ወዘተ ደግሞ በድምጽ፣ በአነጋገር፣ በአጻጻፍ፣ በአገባብ አጋንንታዊ ይዘቶች ያሏቸው ናቸው። ሱዳንና ግብጽም እኮ በዚህ መልክ ነበር ቀስበቀስ አረብ እና ሙስሊም የሆኑት። እግዚኦ! ከዚህ ዓይነት ውድቀት ያድነን! 😠😠😠 😢😢😢

በርግጥ ቋንቋን እግዚአብሔር አልፈጠረም፤ በቋንቋ መንግስተ ሰማያት አይገባም፡ ነገር ግን የመጀመሪያው አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው የመጀመሪያው ቋንቋ ግእዝ ስለሆነ እርስበርስ ለመግባባት እንችል ዘንድ ሁላችንም አሁን ግእዝ ቋንቋን ማወቅ ሊኖርብን ነው።”

አዎ! ዲያብሎስ በቋንቋ እርስበርሳችን ተጨፋጭፈን ኢትዮጵያዊውን የግዕዝ ቋንቋ፣ ፊደል ወይንም ልሳን እንድንከዳት ይሻል፤ ኢትዮጵያዊ ባልሆኑትና ምንም ዓይነት መንፈሳዊነት በሌለባቸው በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛ ወይንም በኦሮምኛ ቋንቋዎች እየተነጋገርን መንፈሳችንን እንድናዳክም እየሠራ ነው። ታዲያ በፍጻሜ ዘመን፣ ለድሉ ጥቂት ሰዓት በቀረን በዚህ ወቅት ይህ አሳዛኝ ክስተት ከመከሰቱ በፊት ፈጥነን ግእዝ ቋንቋን መማር ይኖርብናል።

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል ❖

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎ’ በነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግእዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።

ግእዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል

፩ኛ. የ ”ግእዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ

፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ

፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ

፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ

፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ

፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ

፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።

፰ኛ. «ግእዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ “አንደኛ” ቢባል ይስማማዋል።

፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግእዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።

፲ኛ. ሌላው ነገር የግእዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉ።

አማርኛ ቋንቋ ከግእዝ ያገኛቸውን በሙሉ ይዞ ሌሎች ፯ ፊደላትን በመጨመር ግእዝ ፳፮ ሲሆን አማርኛ ደግሞ ፴፫ ነው “ቨ”ን ሳይጨምር ማለት ነው።

የግእዝን ፊደሎች ትርጉም ስንመለከት

ሀ፦ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፥ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው

ለ ፦ ብሂል ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፥ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ

ሐ ፦ ብሂል ሐመ ወሞተ ፥ ስለኛ ታመመና ሞተ

መ፦ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው

ሠ ፦ ብሂል ሠረቀ በሥጋ ፥ በሥጋ ተገለጠ

ረ ፦ ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ ፥ ምድር በቃሉ ረጋች

ሰ ፦ ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ቀ ፦ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ፥ ቃል መጀመሪያ ነበር

በ ፦ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ፥ ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ

ተ ፦ ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ኀ ፦ ብሂል ኀያል እግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔር ኀያል ነው

ነ ፦ ብሂል ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፥ መከራችንን ያዘልን ሕመማችንን ተሸከመልን

አ ፦ ብሂል አእኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔርን ፈፅሜ አመሰግነዋለሁ

ከ ፦ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር ፥ ጌታችን ቻይ ነው

ወ ፦ ብሂል ወረደ እምሰማይ ፥ ጌታ ከሰማይ ወረደ

ዐ ፦ ብሂል ዐርገ ሰማያተ ፥ ወደ ሰማይ ዐረገ

ዘ ፦ ብሂል ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፥ ጌታ ሁሉን የሚይዝ

የ ፦ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን ታደርጋለች

ገ ፦ ብሂል ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፥ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ

ጠ ፦ ብሂል ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ፥ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁ

ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው

ጸ ፦ ብሂል ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ፥ ጸጋ እና በረከት ተሰጠን

ፀ ፦ ብሂል ፀሐይ ጸልመት በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ ፥ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች

ፈ ፦ ብሂል ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፥ ጌታ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ

ፐ ፦ ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፥ ፓፓኤል የአምላክ ህቡዕ ስም

ትርጉማቸዉ ይሄን ይመስላል።

ስለዚህ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው የሚለው መላምት የበለጠ ጥንካሬ አለው

አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ፍቺውን ስንመለከት ደግሞ ግእዝ (የዜማ ስም፥ ግእዝ፣ እዝል እና አራራይ። የፊደል ስም ሀ ፦ ግእዝ ሁ ፥ ካዕብ ሂ ፥ ሳልስ …… ) በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 11 ፥ ፮ ላይ እግዚአብሔርም አለ ” እነሆ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው” ይላል።

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: