Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2022
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 27th, 2022

Magnificent Russo-Ukrainian Orthodox Chant | አስደናቂው የሩሶ-ዩክሬን ኦርቶዶክስ ዝማሬ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2022

😇 Orthodox Christian Chant – Requiem 😇

❖ [Psalm 50:51] + Requiem

❖ [መዝ. ፶፥፶፩] + ጸሎተ ፍትሐት

😲 በእውነት ድንቅ ዝማሬ ነው፤ የቅዱስ ያሬድ ውብ ዜማ ሲታከልበት የእግዚአብሔርን ዙፋን የሚሸከሙት የነገደ መላዕክትን የኪሩቤልን እና የሱራፌልን ድምጽ የሰማሁ ሆኖ ነው የተሰማኝ። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

😲 It is indeed a wonderful Chant. With the beautiful melody of St. Jared, I felt as if I had heard the voice of the the angels; The Cherubim and The Seraphim carrying the throne of God. Praise be to God!

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፶]❖❖❖

😇 የአሳፍ መዝሙር

፩ የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።

፪ ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።

፫ አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።

፬ በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፤

፭ ከእርሱ ጋር ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት።

፮ ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።

፯ ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፤ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፤ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።

፰ ስለ ቍርባንህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው።

፱ ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፤

፲ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና።

፲፩ የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው።

፲፪ ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና።

፲፫ የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?

፲፬ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤

፲፭ በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።

፲፮ ኃጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር አለው። ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ? ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትወስዳለህ?

፲፯ አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥ ቃሎቼንም ወደ ኋላህ ጣልህ።

፲፰ ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጥ ነበር እድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።

፲፱ አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።

፳ ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፥ ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋት አኖርህ።

፳፩ ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፤ እኔ እንደ አንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ፤ እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ።

፳፪ እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፤ አለዚያ ግን ይነጥቃል የሚያድንም የለም።

፳፫ ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።

❖❖❖ [Psalm 50:] ❖❖❖

😇 A Psalm of Asaph

1 The Mighty One, God the Lord, Has spoken and called the earth From the rising of the sun to its going down.

2 Out of Zion, the perfection of beauty, God will shine forth.

3 Our God shall come, and shall not keep silent; A fire shall devour before Him, And it shall be very tempestuous all around Him.

4 He shall call to the heavens from above, And to the earth, that He may judge His people:

5 “Gather My saints together to Me, Those who have made a covenant with Me by sacrifice.”

6 Let the heavens declare His righteousness, For God Himself is Judge. Selah

7 “Hear, O My people, and I will speak, O Israel, and I will testify against you; I am God, your God!

8 I will not rebuke you for your sacrifices Or your burnt offerings, Which are continually before Me.

9 I will not take a bull from your house, Nor goats out of your folds.

10 For every beast of the forest is Mine, And the cattle on a thousand hills.

11 I know all the birds of the mountains, And the wild beasts of the field are Mine.

12 “If I were hungry, I would not tell you; For the world is Mine, and all its fullness.

13 Will I eat the flesh of bulls, Or drink the blood of goats?

14 Offer to God thanksgiving, And pay your vows to the Most High.

15 Call upon Me in the day of trouble; I will deliver you, and you shall glorify Me.”

16 But to the wicked God says: “What right have you to declare My statutes, Or take My covenant in your mouth,

17 Seeing you hate instruction And cast My words behind you?

18 When you saw a thief, you consented with him, And have been a partaker with adulterers.

19 You give your mouth to evil, And your tongue frames deceit.

20 You sit and speak against your brother; You slander your own mother’s son.

21 These things you have done, and I kept silent; You thought that I was altogether like you; But I will rebuke you, And set them in order before your eyes.

22 “Now consider this, you who forget God, Lest I tear you in pieces, And there be none to deliver:

23 Whoever offers praise glorifies Me; And to him who orders his conduct aright I will show the salvation of God.”

____________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: