ብሪታኒያውያን | አይሁድ እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ይምጡ፤ ሙስሊሞች ግን አይምጡብን
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 15, 2022
💭ጀግናው ክርስቲያን ቦብ ከአንድ እንግሊዛዊ ብሔርተኛ ጋር በለንደኑ ሃይድ ፓርክ
👉 የቦብ ሃሳብ በጥቂቱ፦
❖ አንድ ሕዝብ አኗኗሩን በክርስቶስ ላይ ካልመሠረተና እንደ ክርስቲያን መኖር ያለበትን ሕይወት ካልኖረ በውስጡ ባዶ ስለሚሆን ከምድር ተጠርጎ ቢጠፋ ብዙም ሊያሳስብን አይገባም።
❖ ብሪታናውያን ከክርስቲያናዊ ህይወት በመራቃቸው ከዚህ ምድር ተጠርገው ቢሄዱ እንባ አላነባላቸውም፤
መንፈሳዊ ሞት ስጋዊ ሞትንም ያስከትላልና ነው።
❖ የሀገር መሰረቱ ቤተሰብ ነው። የትውልድ ምሰሶው ቤተሰብ ነው። ይህ የማህበረሰብ መሰረት ጠንካራ ሲሆን ጠንካራ ሀገር መፍጠር ይቻላል። ይህ የማህበረሰብ መሰረት ሲናጋ የሀገር ህልውና አደጋ ውስጥ ይገባል።
የክርስቲያናዊ ቤተሰብ የቤት ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ የሌለበት ሕይወት ባዶ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ አንዳች ልናደርግ አንችልም፡፡ ሕይወት ያለ ክርስቶስ ሞት ነው፡፡ ሠላምና እውነተኛ መንገድም እርሱ ብቻ ነው፡፡ (ኤፌ.፮፥፲)፣ (ዮሐ.፲፬፥፮)፡፡ ያለ ክርስቶስ ክርስትና የለም፡፡ እርሱ የሌለበት ትዳር፣ ቤትና ኑሮ ትርጉም የለውም፡፡ የመልካም ቤተሰባዊ ሕይወት መሰረቱ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስን መሰረት ያላደረገ ትዳርና ጎጆ ውጤቱ ጭቅጭቅ፣ ሁከት፣ስቃይ፣ መለያየትና አድመኝነት ነው፡፡ ክርስቶስን ራስ ያላደረ ቤተሰባዊ ሕይወት ጅራት (ኋለኛ) ነው የሚሆነው፡፡ ክርስቶስን ራስ ያደረገ ቤተሰባዊ ሕይወት የመፈቃቀር፣ የደስታ፣ የሠላም የተስፋና የእምነት ምንጭ ነው፡፡
❖ እንግሊዞች ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን ክደዋል፣ ቤተሰባዊ አኗኗራቸውን እየተውና ልጆችንም ከመውልድ እየተቆጠቡ ስለሆነ እንደ ሕዝብ እየሞቱ ቢያልቁ አያስገርመኝም።
❖ ክርስትና የሞራል መምሪያ እምነት ብቻ አየደለም ለመንፈሳዊ ሕይወት ትልቅ ቦታ ያለው ሃይማኖት እንጂ።
❖ ዘረኞችና የዘውግ ብሔርተኞች ግን የክርስትና ጠላቶች ስለሆኑ መንፈሳዊውን ክርስትናን ለመሸርሸር ሲሉ ክርስትናን የባሕል፣ የወግና የበዓላት ባሕርይ ብቻ ይዞ እንዲጓዝ ይሻሉ ፥ ይህ ክርስትና አይደለም።
❖ የዘውግ ብሔርተኞች ዋንኛው ችግራቸው በጥላቻ የተሞሉ መሆናቸው ነው። አንድ ብሔር በራሱ ብቻ መኩራራት የሚጀመር ከሆነ ሌሎች ብሔሮችን በቀላሉ ወደ መጥላት ያመራል፤ ይህም ከክርስትና አስተምህሮ ጋር እንዲጻረር ያደርገዋል። ክርስትና ሁሉንም ብሔሮች የሚያቅፍ በክርስቶስ ሁሉም አንድ የሚሆኑበት እምነት ነውና።
👉 ብሔርተኛው፦
☆ የዘር ጥላቻ ጉዳይ አይደለም፤ እኔ ለምሳሌ ሶማሌዎችን አልወዳቸውም፤ ግን ይህ ዘረኛ በመሆኔ ሳይሆን በእነርሱ ዘንድ የማየው ነገር ከእኔ አኗኗር ጋር ስለማይጣጣም ነው
ቦብ፦ እሺ፡ ኢትዮጵያውያንስ?
👉 ብሔርተኛው፦
☆ ከአይሁድ እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ጋር ምንም ችግር የለኝም እዚህ መጥተው ቢሰፍሩ አልቃወምም፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ግን ወደ ብሪታኒያ መጥተው እንዲሠፍሩ አልሻም።
👉 ቦብ፦
ስለዚህ ያንተ ችግር/ ጉዳይ ብሔር-ተኮር ሳይሆን እምነትና ሃይማኖት-ተኮር ነው ማለት ነው። አዎ! ስለዚህ ችግሩ፤ አንዳንድ ብሔሮች አብረው መኖር አይችሉም ሳይሆን ፥ አንዳንድ እምነቶች ጎን ለጎን አብረው መኖር አይችሉም ፥ በዚህ እኔም እስማማለሁ።
😈 የዲያብሎስ መንግስታዊ ሕግ የ “መቀላቀል” ሕግ ሲሆን ✞ የእግዚአብሔር መንግስታዊ ሕግ ደግሞ የ “መለየት” ሕግ ነው። ምኒልክም የዛሬዋን የአብዛኛውን የዚህ ከንቱ ትውልድ ኢትዮጵያ የመሰረቷት በመቀላቀል ሕግ ነው። የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለን ስንወጣ የምናመልጥባት ስፍራ ጭምር ትድናለች፡፡ የሚጠፉትን የምናድነው በመደባለቅ ሳይሆን ጥሪውን ተቀብለን ለእግዚአብሔር በመለየት ነው፡፡
❖[ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፳፪፥፲]❖
“በበሬና በአህያ በአንድነት አትረስ።”
❖[መጽሐፈ ዕዝራ ምዕራፍ ፱፲፤፲፩፤፲፪]❖
“አሁንስ አምላካችን ሆይ። ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡባት ምድር በምድር አሕዛብ ርኵሰት ረክሳለች፥ ከዳር እስከ ዳርም ድረስ ከርኵሰታቸው ከጸያፍ ሥራቸውም ተሞልታለች፤ አሁንም ትበረቱ ዘንድ፥ የምድሩንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ለዘላለም ለልጆቻችሁ ታወርሱአት ዘንድ ሴቶች ልጆቻችሁን ለልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችሁ አትውሰዱ፥ ሰላማቸውንና ደኅንነታቸውንም ለዘላለም አትሹ ብለህ በባሪያዎችህ በነቢያት ያዘዝኸውን ትእዛዝ ትተናልና ከዚህ በኋላ ምን እንላለን?”
❖[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፪፥፵፫]❖
“ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ፥ እንዲሁ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም።”
❖[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፯፥፩]❖
እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።
❖[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፬]❖
ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
_______________
Leave a Reply