Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2022
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 30th, 2022

አስደናቂ ክስተት በኡራኤል ዕለት | የትክክለኛዋ ኢትዮጵያ ካርታ + ገዳም ጉንዳ ጉንዶ + የባኩ ፍንዳታ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 30, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 😇 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

💭 በድጋሚ የቀረበ፤

💭 የዛሬዋ ኢትዮጵያ “አገር” ኢትዮጵያ ዘስጋ፤ በቁማቸው በሞቱ የስጋ ሰዎች ምናባዊ ምስል የተቀረጸችና የተፈጠረች የ”ፈጠራ” አገር ናት። “ኢትዮጵያዊነትም” አሁን አፄ ምኒልክ በፈጠሯት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረውንም ህዝብ ማነትና ምንነት አይወክልም፤ አይገልጽምም። ይህች አሁን ያለችዋ፣ ላለፉት ፻፴/130 ዓመታት ወለም ዘለም እያለች ለ፬/4 ትውልድ ዘልቃ የቆየችው ትክክለኛዋ፣ የእምቤታችን አሥራት አገር የሆነችዋ ኢትዮጵያ ሳትሆን የአፄ ምኒልክ ፪ኛው የስጋ ምኞት ራዕይ የፈጠራት የፈጠራ (ሐሰት) ኢትዮጵያ ናት። በሰሜን ኢትዮጵያውያን ወንድማማች ሕዝብ (የትግራይ/ኤርትራ ኢትዮጵያውያን)መካከል እስከ ዛሬ ድረስ የዘለቀ ጠብ ዘርተው በመከፋፈላቸው እግዚአብሔር አምላክን እጅግ በጣም አስቆጥተውታል፤ ([መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፮፥፲፮]እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ)ይህም እግዚአብሔር የተጸየፈው ተግባራቸው ነው በተለይ “አማራ ነን፣ ምኒልክ እምዬ” በማለት ተታልሎ እና እራሱንም በዋቄዮአላህ የማታላያ መንፈስ አስገዝቶ ነው ዛሬ ለምናየው የትውልድ እርግማን የተጋለጠው። ይህ ከትውልድ ወርዶ የመጣው መርገም ስላሠረው ነው ዛሬ ከታች እስከ ላይ “ተዋሕዶ ክርስቲያን ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚለው “አማራ” ሁሉ (/90%) በስጋ ምኞቱ የዲቃላ እና ቃኤላዊ ማንነትን በመያዝ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያልተጠበቀና ዓለምን ሁሉ ያስገረመ ጥላቻ በማሳየት ላይ ያለው። ዛሬ ዓለም ከሚመስለው ሕዝብ ጋር በመቀራረብና በማበር(ፈረንጁ ከፈረንጁ ጋር ሕብረት ፈጥሯል፣ አህዛብ በመላው ዓለም ካሉ መሀመዳውያን ጋር ሕብረትን እየፈጠሩ ነው፣ ምስራቅ እስያውያን በመላው ዓለም ከሚገኙ እስያውያን ጋር አንድነት በመፍጠር ላይ ናቸው)“ከባባድ ጠላቶቼ ናቸው ከሚላቸው ሕዝቦች (ለነጩ/ኤዶማዊ፣ ጥቁሮችና ቢጫዎች ጠላቶቹ ናቸው፣ ለአህዛብ/እስማኤላዊ ክርስቲያኖች ዋና ጠላቶቹ ናቸው፣ ለምስራቅ እስያዊ ነጩ/ኤዶማዊ + ጥቁሩ/አፍሪቃዊ + አህዛብ/እስማኤላዊ ጠላቶቹ ናቸው)ጋር ለመፋለም በወሰነበት በዚህ ዘመን ደጀን የሚሆነውን የትግራይን ተዋሕዶ ክርስቲያን ሕዝብ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ እንዲሁም እራሱን ከሚጨፈጭፉት ኦሮሞዎች ጋር አብሮ ይጨፈጭፈዋል፣ ያፈናቅለዋል፣ ይደፍረዋል፣ በረሃብ ለመፍጀት፣ የምግብ እርዳታ እንዳያልፍ ያግዳል፣ ድልድይ ያፈርሳል። አማራው ልክ በምኒልክ አቴቴ መንፈስ አታሎ እንዳሰረው እንደ ኦሮሞው ልቡም ህልኒናውም ምን ያህል እንደጨለመበትና የዚህ እርኩስ መንፈስ ሰለባ ሆኖ በጣም ጥልቅ የሆነ ዲያብሎሳዊ አረመኔነት ውስጥ መግባቱን እነዚህ ቀናት በግልጽ እያሳዩን ነው። በጣም በጣም ያሳዝናል። እስኪ መጀመሪያ ከአፄ ምኒልክ ይፋቱ! እሳቸውን ማምለኩን ያቁሙ፤ ልክ መሀመዳውያኑ መሀመድን ከአላሃቸው አብልጠው እንደሚያመልክቱ አማራዎችም ምኒልክን ከክርስቶስ አብልጠው በማምለክ ላይ ናቸው። እንግዲህ ሁሉም እግዚአብሔር አጥብቆ የሚጠላውን ኃጢዓት በመስራታቸው ተጸጽተው ለንስሐ እራሳቸውን ያዘጋጁ!

አፄ ምኒልክ ከእግዚአብሔር በመራቅ፣ ሰሜን ኢትዮጵያውያንንና ለአደዋው ድል ያበቃቸውን አምላካቸውን ክደው የአህዛብን ዕውቅትና ጥበብ ለመቀበል በመወሰናቸው ታሪካዊታዊቷን ኢትዮጵያ ለስደት አበቋት። ምኒልክ እና እስከ ዛሬ ድረስ የዘለቀው አራተኛው፣ የመጨረሻውና ጠፊው ትውልዳቸው አገር ማለት የምድር አፈር ሕግ ማለትም አንድ ማንነትና ምንነት፣ አንድ ስምና ክብር እንደሆነ በጥልቀት አለማወቃቸው ለዚህች ቅድስት ምድር ማለትም ነብዩ ሙሴ አርባ ዓመት ለኖረባት፣ ጌታችን እና ቅድስት እናቱ በቅዱስ ኡራኤል መሪነት የመጡባት፣ እነ ቅዱስ ማቴዎስ ለሰማዕትነት የበቁባት፣ እንደ እነ አቡነ አረጋዊ ያሉ የመላው ዓለም ቅዱሳን ያረፉባት ለትክክለኛዋ ኢትዮጵያ ማንነትና ምንነት ሞትንና ጥፋትን አስከትሏል፤ አእምሮ የጎደለው ስጋዊ ምኞት ነበርና።

የዲያብሎስ መንግስታዊ ሕግ የ “መቀላቀል” ሕግ ሲሆን የእግዚአብሔር መንግስታዊ ሕግ ደግሞ የ “መለየት” ሕግ ነው። ምኒልክም የዛሬዋን የአብዛኛውን የዚህ ከንቱ ትውልድ ኢትዮጵያ የመሰረቷት በመቀላቀል ሕግ ነው። ይህን የተቀላቀለ “ዲቃላ” ማንነትና ምንነት ነው ልክ አፄ ዮሐንስ የሰጡንን ሰንደቅ ሠርቀው በመገለባበጥ እንዳቆዩት፣ ኢትዮጵያዊነትንም የዲቃላ ማንነትና ምንነት መገለጫ በማድረግ በከባድ ስህተት፣ በትልቅ ዲያብሎሳዊ ወንጀል ዛሬ “ኢትዮጵያዊ” የምንለውን የማንነትና ምንነት መገለጫ ያለምንም ፍተሻ እንቀበለው ዘንድ ተገደድን፣ የስጋ ስምና ክብር ነገሠ። ስለ ኃይማኖት ማለትም ስለ ሕይወት ሕግና ሥርዓት ብቻ እንጂ ስለ ቁንቋ፣ ስለ ቀለም፣ ስለ ባሕል፣ ስለ ዘር ማለቴ አይደለም። የስጋን ማንነትና ምንነት ከመንፈስ ጋር በማዋሃድና በማጣመር አንድ አገር ለመፍጠር ከተሞከረ መንግስቱ ቀስ በቀስ የፖለቲካውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ለአጥፊው ማንነትና ምንነት አሳልፎ ለመስጠት ይገደዳል። ቀስ በቀስም ቢሆን የሚነሠውና ሙሉ በሙሉ የመንግስቱን ሥልጣን የሚቆጣጠረው ያ የስጋ አካል (ማንነትና ምንነት) ይሆናል።

የምኒልክ ተከታዮች የሆኑት ዲቃላዎቹ ኦሮሞዎች አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ መንግስቱ ኃይለ ማርያም እና አብዮት አህመድ ሰሜኑን በመከፋፈል፣ በሰሜኑ ላይ ጦርነት በማካሄድ (ከ፳፯/27 ጦርነቶች በትግራይ) በማውደም፣ የሕዝቡን መንፈሳዊ ስብጥር ለማናጋት እስከ ሴቶችን አስገድዶ በመድፈር ሕዝቡን በመደቀል የስጋ አካል (ማንነትና ምንነት) ለሳጥናኤል እንዲነግስ ላለፉት ፻፴/130ተሰርቶበታል። የምኒልክ በኦሮሞዎች በኩል የግዛት ማስፋፋት ፖሊሲ ተግባራዊ የተደረገበት የብሔር ብሔረሰብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የትክክለኛው ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊው ማንነትና ምንነት ለስጋ ሕግ ለዘመናት ባሪያ እንዲሆን አድርጎት አልፏል።

ግዛት አስፋፊው የኦሮሞ ሞጋሳ ሥርዓት ከእስልምናው የአረብ ሻሪያ ኢምፔሪያሊዝም ጋር በጣም የሚቀራረብ ነው!መንፈሳዊ ማንነትና ምንነት የነበራቸው አርቆ አሳቢውና ትክክለኛው ኢትዮጵያዊ አፄ ዮሐንስ ስጋዊ ማንነትና ምንነት ለነበራቸው ለአፄ ምኒልክ የጋልኛ ስም የተሰጣቸውን የቦታ መጠሪያ ስሞችን በመቀየር መንፈሳዊ ሕይወትን አንቀበልም የሚሉትን ጋሎች ቀስበቀስ ከቅድስት ኢትዮጵያ ምድር እንዲያስወጧቸው መክረዋቸው ነበር፤ አፄ ምኒልክ ግን ዲቃላዊ ማንነታቸውና ምንነታቸው ስላሸነፋቸው ይህን ሊያደርጉት አልፈለጉም ነበር፤ ይህን ባለማድረጋቸው ትልቅ ስህተት እንደሆነ አሁን በግልጽ እያየነው ነው!

በተለይ የቤተ ክህተንት አባቶችና መምህራን የፖለቲከኞችን ፈለግ በመከተል ፈንታ ለመንፈሳዊቷ ኢትዮጵያ ዋና ጠላት የሆነውን የጋላን ስጋዊ ማንነትና ምንነት በግልጽ በማሳወቅና እነርሱም የሚድኑበት መንገድ አንድ እና አንድ ብቻ እሱም በክርስቶስ ብቻ መሆኑን ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የማስተማር ግዴታ ነበረባቸው፤ በተለይ በዚህ ዘመን።

ታሪክ የዛሬውና የወደፊቱ መስተዋት ነው። የስጋ ማንነት ያላቸው ኦሮሞዎች በጋላስም መጨፍጨፍ የቻሉትን ሰው ሁሉ ከጨፈጨፉ በኋላ ትንሽ ቆየት ብለው ኦሮሞ ነንአሉ፤ አሁን በኦሮሞነታቸው በቂ ሰው ከጨፈጨፉ በኋላ አለፍ ብለው ደግሞ ኦሮማራ ነንብለው ይመጡና የተጠሩበትን የጭፍጨፋ ተልዕኳቸውን ማንነታቸውና ምንነታቸው በሚፈቅድላቸው ተፈጥሯዊ መልክ ይቀጥሉበታል።

ፈረንጆቹ የኦሮሞዎችን ማንነትና ምንነት ገና ከ፬፻/400 ዓመታት በፊት አጠንቅቀው ስላወቁት ነው ለፀረኢትዮጵያና ፀረተዋሕዶ ተልዕኮዎቻቸው የሚጠቀሙባቸው። ሞኙ የምኒልክ ኢትዮጵያዊ ግን ፍልውሃ ላይ ቁጭ ብሎ ሁላችንም አንድ ነን! አዲስ አበባን ፊንፊኔ ብንላት ክፋቱ ምኑ ነው?” እያለ ይጃጃላል። የአክሱም ግዛት የነበረውአማራ ሳይንትበምኒልክ ተንኮል ወሎ ሆኖ በመቅረቱ ዛሬ “ወሎ ኬኛ!” መባልና ከተሞችንም ማቃጠል ተጀምሯል።

በሞጋሳ ሥርዓት ተገድደው ጋላ ለመሆን የበቁትን ወገኖቻችንን ከዚህ አስከፊ የሞትና ባርነት ማንነትና ምንነት ነፃ የሚወጡበትን ስልት (በግድም ቢሆን) መፍጠር አለብን። ፸/70% የሚሆኑት ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ጋሎች አይደሉምና!

መንፈሳዊ የሆኑት ኢትዮጵያውያን የክፍለ ሃገራትን፣ የከተማዎችንና የአውራጃ መጠሪያዎችን በቆራጥነት ከአጋንንታዊ የጋልኛ መጠሪያ ስሞቻቸው ወደ ኢትዮጵያኛ መጠሪያ ስሞች መቀየር መጀመር አለባቸው ፥ ምናባዊ በሆነ መልክም ቢሆን።

________________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ኡራኤል ከ፯/7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ፣ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነዉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 30, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 🌞 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፮፥፪] ፣ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። ፟[መጽሐፈ ሔኖክ ፳፰፥፲፫]

________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጥር ፳፪/22 | ቅዱስ ኡራኤል ቃል ኪዳን የተቀበለበትና የተሾመበት ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 30, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 🌞 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

❖❖❖ ድርሳነ ዑራኤል ❖❖❖

ምድረ ኢትዮጵያ ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍና ሰሎሜ በደመና ተጭነው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ። በናግራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ። ከቀኝ ጎኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች ሀገር ይፈሳል ወይም ይረጫል። እናቱንም እንዲህ አላት አንቺ በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ በእኔም የሚያምኑ ብዙ የተቀደሱ ሰዎች በዚህ ሀገር ይወለዳሉ። ከናግራን ተነስተው ለትግራይ ትይዩ ከሚሆን ሐማሴን ከሚባለው ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ። ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እናቱን እንዲህ አላት ይቺ ተራራ ምስጋናሽ የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች። የተራራዋም ስም ደብረ ሃሌ ሉያ ወይም ደብረ ዳሞ ይባላል። ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ የመስቀሉ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም አደባባይ ማለት ነው።ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደምትኖርበት ወደ አክሱም ደረሱ። ታቦተ ጽዮን ባለችበት ቦታ ሳሉ ባዚን የተባለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ። የካህናቱ አለቃ አኪን ለንጉሡ የኢሳይያስን መጽሐፍ አነበበለት። የተነበበውም የመጽሐፍ ክፍል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች የሚል ነበር። ስደተኞቹ ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገለጡ የመጽሐፉን ቃል ከሰሙ በኋላ በደመና ተጭነው ወደ ደብረ ዐባይ ሄዱ ። ጌታም እናቱን እንዲህ አላት ይህች ሀገር እንደአክሱም ለስምሽ መጠሪያ ርስት ትሁን በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንቺን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩባታል። ከዚያም በኋላ ከደብረ ዐባይ ተነስተው ዋሊ ወደ ሚባለው ገዳም /ወደ ዋልድባ / ሄዱ። በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ ብትር የአንዱን ዕንጨት ስር ቆፈረ። ሦስት መቶ አስራ ስምንት ስሮችን አወጣና ለእናቱ ብይ ብሎ ሰጣት። እናቱም ይህን የሚመር ዕንጨት አልበላም አለችው። ጌታም በኋላ ዘመን ስምሺን የሚጠሩ አንቺን የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ። ዕንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል አላት። ከዚህ በኋላ በደመና ተጭነው ከዋልድባ ወደ ጣና የባሕር ወደብ ሄዱ። በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው ሦስት ወር ከአስር ቀን ተቀመጡ። የኢትዮጵያ ሰዎች በደስታ ተቀብለዋቸዋል እንደ ግብፃውያን አላሰቃዩአቸውም ። በጥር አስራ ስምንት /18/ ቀን ዑራኤል መጥቶ የሄሮድስን መሞት ነገራቸው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በደመና ከተጫኑ በኋላ ጌታ እናቱን እንዲህ አላት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስምሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለሁ ። ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎችን ሜዳዎችን ኮረብታዎችን አሳያት። እመቤታችን ሁሉንም ቦታዎች እየተዘዋወረች እንድታይ ልጅዋን ጠየቀችው። ልጅዋም የሚመለሱበት ጊዜ እንደደረሰ ነገራት። በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው ክፍላተ አህጉር እየተዘዋወሩ ተራራዎችን ወንዞቸን አስጐበኛት የኢትዮጵያን ምድር ከጐበኙ በኋላ በደመና ተጭነው ጥር 29 ቀን ምድረ ግብፅ ደረሱ። ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው። ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ታሪክ በድርሳነ ዑራኤል ላይ በስፋት ተጽፏል።

የቅዱስ ኡራኤል በረከት ረድኤቱ ይደርብን ! ምልጃ ጥበቃዉ አይለየን!

❖❖❖ ቅዱስ ኡራኤል ኢትዮጵያን የጽዮንን ልጆችን አደራ፤ በእሳት ሰረገላ በነበልባል ታጅበህ ለተልዕኮ የምትፋጠን የአምላካችን አገልጋይ ወራዙተ ኢትዮጵያን በብርሐናዊ ክንፍህ ሸፍነህ ከመርዘኞች የሞት ቀስት ከቀሳፊ ነገር ሁሉ ሰውረን! ❖❖❖

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፰]✞✞✞

፩ አምላክ ሆይ፥ ምሥጋናዬን ዝም አትበል፥

፪ የኃጢአተኛ አፍና የተንኰለኛ አፍ በላዬ ተላቅቀውብኛልና፤ በሽንገላ አንደበትም በላዬ ተናገሩ፤

፫ በጥል ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተሰለፉብኝ።

፬ በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።

፭ በመልካም ፋንታ ክፉን በወደድኋቸውም ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ።

፮ በላዩ ኃጢአተኛን ሹም፤ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም።

፯ በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፤ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት።

፰ ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።

፱ ልጆቹም ድሀ አደግ ይሁኑ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን።

፲ ልጆቹም ተናውጠው ይቅበዝበዙ ይለምኑም፥ ከስፍራቸውም ይባረሩ።

፲፩ ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥ እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት።

፲፪ የሚያግዘውንም አያግኝ። ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።

፲፫ ልጆቹ ይጥፉ፤ በአንድ ትውልድ ስሙ ይደምሰስ።

፲፬ የአባቶቹ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ትታሰብ፤ የእናቱም ኃጢአት አትደምሰስ።

፲፭ በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፤ መታሰቢያቸው ከምድር ይጥፋ።

፲፮ ምሕረትን ያደርግ ዘንድ አላሰበምና ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ሰው ይገድል ዘንድ አሳደደ።

፲፯ መርገምን ወደደ ወደ እርሱም መጣች፤ በረከትንም አልመረጠም ከእርሱም ራቀች።

፲፰ መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።

፲፱ እንደሚለብሰው ልብስ። ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ይሁነው።

፳ ይህ ሥራ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚያጣሉኝ በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ነው።

፳፩ አንተ ግን አቤቱ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕረትህን በእኔ ላይ አድርግ፤ ምሕረትህ መልካም ናትና አድነኝ።

፳፪ እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።

፳፫ እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥ እንደ አንበጣም እረገፍሁ።

፳፬ ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።

፳፭ እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንሁ፤ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ።

፳፮ አቤቱ አምላኬ፥ እርዳኝ፥ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።

፳፯ አቤቱ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች፥ አንተም ይህችን እንዳደረግህ ይወቁ።

፳፰ እነርሱ ይራገማሉ አንተ ግን ባርክ፤ በእኔ ላይ የሚነሡ ይፈሩ፥ ባሪያህ ግን ደስ ይበለው።

፳፱ የሚያጣሉኝ እፍረትን ይልበሱ፤ እፍረታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት።

፴ እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ። በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ፤

፴፩ ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ በድሀ ቀኝ ቆሞአልና።

_______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: