False Banana: Ethiopia’s ENSET ‘Wondercrop’ is The Answer to Food Scarcity
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 27, 2022
😈 ከጦርነቱ መንፈሳዊና ስጋዊ ተልዕኮዎች መካከል፤
❖ እንሰትን + ጤፍን + እጣንን መውረስ ይገኝበታል
💭 A Crop Virtually Unknown Outside Ethiopia | False Banana
While climate change disrupts farming practices, a crop named false banana could be the answer to food scarcity issues. Scientists say that it has the potential to feed more than 100 million people.
💭 ከኢትዮጵያ ውጪ የማይታወቅ ሰብል ለምግብ እጥረት መልሱ | እንሰት
የአየር ንብረት ለውጥ የግብርና ተግባራትን ቢያስተጓጉልም፣ የውሸት ሙዝ የሚባል ሰብል ለምግብ እጥረት ችግሮች መፍትሄ ሊሆን ይችላል። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከ መቶ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የመመገብ አቅም አለው።
💭 የኢትዮጵያ እንሰት፡ በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተስፋን የፈነጠቀው ልዕለ ምግብ
ሳይንቲስቶች በኢትዮጵያ ከዋነኛ ተክሎች አንዱ የሆነው እንሰት በአየር ንብረት ለውጥ በርካታ ቀውሶችን እያስተናገደች ላለችው ዓለም ልዕለ ምግብ እንዲሁም ነፍስ አድን ሊሆን ይችላል እያሉ ነው።
ሙዝ መሳዩ ተክል እየሞቀች ባለችው ዓለም 100 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የመመገብ አቅም እንዳለው አንድ አዲስ ጥናት አመልክቷል።
እንሰት ከኢትዮጵያ ውጪ ባይታወቅም በገንፎና ቆጮ መልኩ ተሰርቶ ለምግብነት ይውላል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ተክሉ በአፍሪካ ሰፋ ባለ መጠን ሊበቅል ይችላል።
“ይህ ተክል የምግብ ዋስትናን እና የዘላቂ ልማት ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ነው” ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ዶክተር ወንዳወርቅ አበበ ይናገራሉ።
በተለምዶ “ፎልስ ባናና” ተብሎ የሚጠራው እንሰት ከሙዝ ዝርያ ጋር ቅርበት ያለው ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ለምግብነት የሚውለው በተወሰኑ ቦታዎች ነው።
የእንሰት ሙዝ የመሰለ ፍሬው ባይበላም በካርቦሃይድሬት የበለጸገው የተክሉ ዘለላዎች እንዲሁም ስሩ እርሾ በሚኖረው መልኩ ገንፎና ቆጮ ለመስራት አገልግሎት ላይ ይውላል።
እንሰት በኢትዮጵያ ውስጥ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕዝቦቿ ዋነኛ ምግብ ቢሆንም በሌሎች አገራት ግን ሲመረት አይታይም።

ከእንሰት ጋር ተመሳሳይ የሆኑና እንደ ምግብነት የማይቆጠሩ ተክሎች እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ መብቀላቸው ታይቷል። ይህም ተክሉ ሰፊ ክልልን በመሸፈን መቋቋም እንደሚችል የጠቆመ ነው።
ሳይንቲስቶች የግብርና ዳሰሳዎች እንዲሁም የተከላ ሥራ በመስራት እንሰት በሚቀጥሉት አራት አስርት ዓመታት ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን አቅም ተንብየዋል።
ሰብሉ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን መመገብ የሚችል ሲሆን በኢትዮጵያ እንዲሁም ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ ባሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራት የምግብ ዋስትናን እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል።
ሮያል ቦታኒክ ጋርደንስ፣ ኪው የተባለው ተቋም የጥናት ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ጄምስ ቦረል እንሰት በአስቸጋሪ ወቅት የምግብ ዋስትናን ለማሳደግ እንደ መከታ የሚጠቅም ሰብል እንደሆነም ያስረዳሉ።
“እንሰት ከሌሎች ሰብሎች ፍፁም ልዩ የሚያደርጉት አንዳንድ ያልተለመዱ ባህርያት አሉት” የሚሉት ዶክተር ጄምስ ይህንንም ሲያስረዱ “በማንኛውም ጊዜ መተከል፣ ምርቱን መሰብሰብና ለረዥም ጊዜ መቆየት ይችላል። ለዚያም ነው ፀረ-ረሃብ ተክል የሚል ስያሜ ያገኘው” ይላሉ።
ቡናን ጨምሮ የበርካታ ሰብሎች መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በአፍሪካም የእንሰት ሰብል መዳረሻ ናት።
የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ እና ከዚያ ባሻገር በምርታማነት እንዲሁም በዋና የምግብ ሰብሎች ስርጭት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ተተንብይዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ በጥቂት ሰብሎች ላይ ጥገኛ የሆነውን ዓለምን ለመመገብ አዳዲስ ሰብሎችን የመፈለግ ሁኔታው እየጨመረ ይገኛል።
ከምንመገባቸው ምግቦች ውስጥ ግማሽ የሚጠጋውን ካሎሪ የምናገኘው ከሦስት ሰብል ዝርያዎች ነው፤ እነዚህም ሩዝ፣ ስንዴና በቆሎ ናቸው።
“በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ሰብሎቻችን በጣት የሚቆጠሩ ስለሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምንጠቀምባቸውን ሰብሎች አይነት ማብዛት ይገባናል” ይላሉ ዶክተር ጄምስ ቦሬል።
👉 ይህ ጥናት ኢንቫይሮመንታል ሪሰርች ሌተርስ ላይ ታትሟል።
______________
Leave a Reply