Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2022
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 26th, 2022

የቅዱስ ጊዮርጊስ ጠላት ዘንዶዋ ቱርክ እየሞተች ነው | ከባድ በረዶው መጣሉን ቀጥሏል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 26, 2022

💭 በእውነት ይህ በጣም ድንቅ ነው!

😇 ቅዱስ ጊዮርጊስ በ፫/3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በቀጰዶቅያ/ጎሬሜ (በአሁኗ ቱርክ) ተወለደ።

😈 አምና ላይ ፀረክርስቶስ ቱርክ ይህን ጥንታዊ የቅድስት ሶፊያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ✞ ወደ መስጊድ ለወጠችው። ቱርክ የቁስጥንጥንያውን የቅድስት ሃጊያ ሶፊያ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ወደ ጣዖት ማምለኪያ መስጊድ 🐍 መለወጧ ከባድ ወንጀል ነው።

👉 አዎ! በትግራይ ላይ፣ በአክሱም ጽዮን ተራሮች ላይ ያመጸ ሁሉ ከክርስቶስ ተቃዋሚ ጎን ሆኖ የክርስቶስን ልጆች የሚጠላ፣ የሚያሳድድና የሚዋጋ እራሱን ለገሃነም እሳት አሳልፎ የሚሰጥ ከንቱ አህዛብ ብቻ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይለናልና ይወቁት፤

በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ። ታላቅ እሆናለሁ እቀደስማለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”

✞✞✞[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፴፰]✞✞✞

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።

የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት፥

እንዲህም በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የሞሳሕና የቶቢል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።

እመልስህማለሁ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህንም ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን ሰይፍንም ያያዙትን ሁሉ፥ ታላቁን ወገን አወጣለሁ፥

ፋርስንና ኢትዮጵያን ፉጥንም ከእነርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ፥

ጋሜርንና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤትና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎችንም ሕዝቦች ከአንተ ጋር አወጣለሁ።

አንተና ወደ አንተ የተሰበሰቡ ወገኖችህ ሁሉ ተዘጋጁ፥ አንተም ራስህን አዘጋጅተህ አለቃ ሁናቸው።

ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘላለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርስዋም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።

አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ፤ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድርን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገባል፥

፲፩ ክፉ አሳብንም ታስባለህ፥ እንዲህም ትላለህ። ቅጥርን ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ፤ ተዘልለው ወደሚኖሩ፥ ሁላቸው ሳይፈሩ ያለ ቅጥርና ያለ መወርወሪያ ያለ መዝጊያም ወደሚቀመጡ እገባለሁ፤

፲፪ ምርኮን ትማርክ ዘንድ ብዝበዛንም ትበዘብዝ ዘንድ፥ ባድማም በነበሩ አሁንም ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከአሕዛብም በተሰበሰበ፥ ከብትና ዕቃንም ባገኘ፥ በምድርም መካከል በተቀመጠ ሕዝብ ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ።

፲፫ ሳባና ድዳን የተርሴስም ነጋዴዎች መንደሮችዋም ሁሉ። ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? ይሉሃል።

፲፬ አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለዚህ ትንቢት ተናገር ጎግንም እንዲህ በለው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ሳይፈራ በተቀመጠ ጊዜ አንተ አታውቀውምን?

፲፭ አንተም፥ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላቸው በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ታላቅ ወገንና ብርቱ ሠራዊት፥ ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ።

፲፮ ምድርንም ትሸፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። በኋለኛው ዘመን ይሆናል፥ ጎግ ሆይ፥ በዓይናቸው ፊት በተቀደስሁብህ ጊዜ አሕዛብ ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።

፲፯ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያቶች በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ ነህን?

፲፰ በዚያም ቀን ጎግ በእስራኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅሠፍቴ በመዓቴ ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

፲፱ በቅንዓቴና በመዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ። በእርግጥ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ መናወጥ ይሆናል፤

ከፊቴም የተነሣ የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች የምድረ በዳም አራዊት በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፥ ተራሮችም ይገለባበጣሉ ገደላገደሎችም ይወድቃሉ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።

፳፩ በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

፳፪ በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።

፳፫ ታላቅ እሆናለሁ እቀደስማለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አጽም መታሰቢያ | ሃገርንና የቤተ ክርስቲያንን ክብር ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ ትውልድ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 26, 2022

✞ …ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉሥ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ ፤ በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ ፤ ከዚህም በኃላ እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አወጡት ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ፤አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ እንዲሁ አደረጉበት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች የሰማዕቱን ሥጋ አቃጠሉት ፈጩት አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው ወታደሮቹ የታዘዙትን ፈጽመው ተመለሱ። ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሠረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በብሩህ ደመና ወረደ በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማዕቱን ሥጋ እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ፤ ከዚህ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው ህልቶን፤አግሎሲስ፤ሶሪስና አስፎሪስ ነው፤ ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፤ በኃላም በሰማዕትነት ሞተዋል፤ ይህ የሆነው ጥር 18 በዛሬዋ ቀን ነው ይህንንም ቀን ” ዝርዎተ አጽሙ ” ስትል ቤተክርስቲያን ሰማዕቱን አዘክራ ትውላለች፤ በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል። አራዳ ጊዮርጊስን የተከሉት ደጉ ንጉሥ እምዬ ምኒልክ ናቸው ታዲያ የዚህን ታላቅ ደብር መሠረቱን ሲጥሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ከሚገኝበት ቦታ አፈሩን በመርከብ አጓጉዘው በበቅሎ በፈረስ አስጭነው መሠረት አድርገውታል፤ ይህንን ከአባቶቻችን የሰማነው ነው፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን። [ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምዕራፍ ፮፥፲፭፡፲፰]

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

ከኢትዮጵያ ጠባቂ እረኞች አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው

የጊዮርጊስ ወዳጂ የት ነው የሚገኘው

በመሃል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው

ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው፡፡

ይነሳ ጊዮርጊስ ይመስክር ምስጢር

የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ‘ኮከብ ክብር’ የተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፯ (ሰብዓ) ነገሥታትን ደምስሰው እንዳጠፏቸው፡ የተነሱብንን የጽዮንን ተቃዋሚዎች፣ የኔንም/የኛንም ጠላቶች ሁሉ ይደመስሱልን ዘንድ እማፀናለሁ። አሜን! አሜን! አሜን! ❖

_______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: