የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ አይታው በማታወቀው ከባድ የበረዶ ማዕበል ሽባ ሆነች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 25, 2022
💭 የቱርክ ሕዝብ ዛሬ የመጽሐፍ ቅዱሳዊው የኤሳው ወይም የኤዶም ዘሮች እንደሆነ ይታወቃል። ስለ ዘመናዊቷ ቱርክ ተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎች ቴማን (የዔሳው ዘር)፣ ኤዶም/ኢዶምያስ፣ ባሲራ (የጥንቷ የኤሳው ዋና ከተማ) እና ሴይር [ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፴፮፥፳፡፴](ከኢያሱ ፳፬፥፬ ጋር እናነጻጽረው) ናቸው።
😈 የዛሬዋ ኤሳው–ቱርክ – በመጨረሻው ዘመን ላይ ከባድ ቅጣት ይደርስባታል።
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፥፰ / መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፰፥፱]
“ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እዘረጋለሁ፤ ፍልስጥኤም ይገዙልኛል።”
[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፴፪፥፳፱]
“ኤዶምያስና ነገሥታቶችዋ አለቆችዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ በሰይፍ ከተገደሉት ጋር በኃይላቸው ተኝተዋል፤ ካልተገረዙትና ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ይተኛሉ።”
[ትንቢተ ሚልክያ ምዕራፍ ፩፥፬]
“ኤዶምያስ። እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ በሰዎችም ዘንድ። የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።”
[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፴፬፥፭፡፮]
“ሰይፌ በሰማይ ሆና እስክትረካ ድረስ ጠጥታለች፤ እነሆ፥ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ ለፍርድ ትወርዳለች። እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፥ በስብም፥ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኵላሊት ስብ ወፍራለች።”
[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፰]
፰ አውራውም ፍየል ራሱን እጅግ ታላቅ አደረገ፤ በበረታም ጊዜ ታላቁ ቀንዱ ተሰበረ፥ ወደ አራቱም የሰማይ ነፋሳት የሚመለከቱ አራት ቀንዶች ከበታቹ ወጡ።
፱ ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ።
፲ እስከ ሰማይም ሠራዊት ድረስ ከፍ አለ፤ ከሠራዊትና ከከዋክብትም አያሌዎችን ወደ ምድር ጣለ፥ ረገጣቸውም።
፲፩ እስከ ሠራዊትም አለቃ ድረስ ራሱን ታላቅ አደረገ፤ ከእርሱም የተነሣ የዘወትሩ መሥዋዕት ተሻረ፥ የመቅደሱም ስፍራ ፈረሰ።
_______________
Leave a Reply