የካ ሚካኤል | “ገና እንዘምራለን!” | የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ “ፖሊሶች” ምዕመናኑን ሲተናኮሏቸው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 20, 2022
❖❖❖የአንጋፋው ቀደምት እና ባለ ታሪክ የካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ዋሻ ቤተክርስቲያን ታሪክ ❖❖❖
ዋሻ ሚካኤል ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ በኩል የካ ከፍለ ከተማ ውስጥ ያለ ጥንታዊ እና በከፊል ወጥ ከሆነ ዓለት ተፈልፍሎ የተሰራ ቤተ-ክርስቲያን ነው። አዲስ አበባ ከሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ በስተጀርባ ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ከፍታማ ቦታ ላይ ይገኛል። ምንም እንኳ የአካባቢው የቀደሙት ካህናት በ፬/4ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ቢናገሩም በአብዛኛው ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚገመተው ግን በ፲፪/12ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ነው።
👉 ታሪካዊ ተደራሽነቱ
የአክሱም መንግስትና የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን:- አብርሃና አጽብሃ የአክሱም መንግስትን በጋራ ይገዙ እንደነበር የተለያዩ መጽሃፍት ይገልፃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጽሁፍም ይሄንን በተለያዩ መረጃዎች ይጠቅሳል፡፡ ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላ እንደተፃፈ በሚነገረው የድንጋይ ላይ ፅሁፍ አብርሃና አፅብሃ የሚያስተዳድሩት አገር ግዛት ዝርዝር ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ዝርዝር እንደምንረዳው ግዛታቸው ሳባን /የመንን/፣ ኑባ /ሱዳንን/ እና ቤጃ /ደቡብ ግብጽ/ ድረስ ይደርሳሉ፡፡ ይህም እጅግ ሰፊ ግዛት እንዳላቸው ያስረዳል፡፡ ከየካ ሚካኤል የተገኘው /ያልታተመ/ መረጃ ይህንን ሀሳብ እንደሚከተለው ያጠናክራል።
“በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ወሰን በጣም ሰፊ ስለነበር ሁሉቱ ወንድማማቾች አክሱም ላይ ሆነው ሕዝባቸውን በቅርብ ለማስተዳደር ስለተቸገሩ እጣ ተጣጥለው ንጉስ አብርሃ አክሱም ላይ በመሆን ሰሜን ኢትዮጵያን፣ ንጉስ አጽብሃ ደግሞ ደቡብ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ሸዋ ውስጥ የረር ተራራ ላይ ቤተ መንግሥቱን ሰራ፡፡ በወቅቱ ቤተመንግሥቱን ለመሥራት ሲመጣ ማዕቀበ እግዚእ በሚባል ካህን ታቦት ሚካኤልን አሸክሞ አስመጥቶ ነበር፡፡ ይህንን አሸክሞ ያስመጣውን ታቦት ከየረር ተራራ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ባስፈለፈለው ዋሻ ውስጥ እንዳስገባው ይገልፃል፡፡”
በትግራይ ክልል በአብርሃና አፅብሃ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ከጅማ የአፅብሃ ሬሳ የመጣበት ነው የሚባለው የጠፍር አልጋ ይገኛል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ደቡብ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው አፅብሃ እስከ ጅማ መድረሱን ነው፡፡ ውቅር ቢተክርስቲያን መስራት ለአጽብሃ አዲስ አይደለም፡፡ በትግራይ ከውቁሮ ከተማ ፳/20 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ገረአልታ ውስጥ ገማድ በተባለ ስፍራ አብርሃና አጽብሃ ያሰሩት ነው የሚባል አብርሃ አጽብሃ በመባል የሚታወቅ ውቅር ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያኑ ገዳም ነው፡፡
ከየካ ሚካኤል የተገኘው /ያልታተመ/ መረጃ እንደሚገልፀው በትግራይ ውቅሮ አካባቢ የሚገኘው የአብርሃና አፅብሃ ውቅር ቤተክርስቲያን ከዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው በመግለጽ ታሪኩን እንደሚከተለው ዘርዝሯል፡-
“ከንጉስ አጽብሃ ጋር የመጣው ታቦት የገባበት ዋሻ የተፈጥሮ ዋሻ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ እንደሚገኙት ከአንድ ቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍለው ከታነፁት ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ዓይነት በኢትዮጵያ ፊደል “ሀ” ቅርጽ የታነፁ ሲሆን በቤተክርስቲያን የፊደል ትርጉም “ሀ” ማለት “ህልዎቱ ለአብ እምቅድም ይትፈጠር ዓለም” ወይም “የአብ መኖር ከአለም አስቀድሞ ነው” ማለት ነው የሚለውን አባባል ለማስረዳት ተብሎ የታነፀ ነው ይላል፡፡” በሌላ በኩል አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን በደቡብ ሸዋ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ በአለምገና ቡታጅራ መንገድ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ ፷፮/66 ኪሎ ሜትር አካባቢ ከምትገኘው አዳዲ ማሪያም ውቅር አብያተ ክርስቲያን ጋር በመመሣሠሉና ይህ ደግሞ በንጉስ ላሊበላ ዘመን እንደ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዚያ ዘመን የተሰራ ነው ይላሉ፡፡
________________
Leave a Reply