አምኖ ያልተጠመቀ አይድንም | በአክሱም ጽዮን ላይ የዘመተ ሁሉ እንደ አህዛብ አልዳንም
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 18, 2022
💭 አንድ ጌታ፣ አንድ ሐይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት | ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው የተጠመቀ ብቻ ነው
✞✞✞[ኤፌ. ፬ ፥ ፭]✞✞✞
በጥምቀት-ያልተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስምና
❖[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]
“ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።”
💭 በእነዚህ ቀናት ቀንደኛው የኢትዮጵያ፣ የተዋሕዶ ክርስትናዋ እና የጥምቀቱ ጠላት ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ጥምቀቱን ከኢትዮጵያዊው ለማራቅና ለመንጠቅ ብዙ ዲያብሎሳዊ ተንኮሎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። እንደተለመደው በመቀበጣጠር፣ “ጽዮናዊውን የአጼ ዮሐንስን ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ሰንደቅ መያዝ ክልክል ነው! ወዘተ” በማለት፤ እንዲሁም የአሜሪካ ልዑካንን ወደ አዲስ አበባ በመጋበዝ።
ልብ እንበል፤ ባለፈው የጌታችን ልደት ዕለት አሰቃቂ የድሮን ጭፍጨፋዎችን በትግራይ ያካሄደው የአሜሪካ ልዑካን ከአዲስ አበባ በተመለሱ እና ግራኝ ከፕሬዚደንት ባይድን ጋር በስልክ በተነጋገረበት ማግስት ነው? አሁንስ ጽዮናውያንን በኢትዮጵያዊነታቸው ተስፋ ቆርጠው እንዲገነጠሉና የኦሮሚያ እስላማዊት ካሊፋት ምስረታ ሕልሙን ለማሳካት በወገኖቼ ላይ የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮኖችን በመጠቀምን ጭፍጨፋውን ይቀጥልበት ይሆን?
እንኳን ለጥምቀቱ አደረሰን!
__________________
Leave a Reply