በአክሱም ጽዮን ላይ የዘመቱትን እበቀላለሁ | በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 9, 2022
✞ ጥንታዊው ደንገላት ቅድስት ማርያም ገዳም + አክሱም ጽዮን ማርያም ✞
አዎ! አሁን የዘመናችንን አማሌቃውያን አህዛብን በያለንበትና ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ የመበቀል ግዴት አለብን! ከእግዚአብሔር መላእክት ጋር በማበር አሳድደን እንበቀላቸዋለን!
ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ”ዲያቢሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዷልና” ብሎ ስለነገረን ወደ ሕይወታችን በቅናት ቁጣ እየመጣ የሚያመሰቃቅለንን፣ ግራ የሚያጋባንን፣ የሚያባክነንን፣ የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል። [ራዕ. ፲፪÷፲፪]
ሰሜን ኢትዮጵያውያን በተለይ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ዲያብሎስ የእናንተ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን፣ ተዋሕዶ ክርስትናን፣ የጽዮንን ሰንደቅን፣ እና ግዕዝ ቋንቋን ብሎም ድንግል ነፍሳችሁን ሊነጥቃቸው ዳርዳር በማለት ላይ ነውና ዋ! በጣም ተጠንቀቁ! እንጠንቀቅ! ተዘጋጁ! እንዘጋጅ! በተዋሕዶ ክርስቲያን ሕዝባችን ላይ ማን ጦርነት እንዳወጀበት፣ ማን በሕዝባችን ላይ በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቀውን ግፍ እየሠራ እንደሆነ፣ የዚህን ግፍ ፈጻሚዎችንና ተባባሪዎቻቸውን አንድ በአንድ እንመዘግባችዋለን እናሳድዳቸዋለን። አሁን ለጊዜው ወደ መኝታ ስንሄድ በቁጣ እንተኛለን፤ የእግዚአብሔር ተዋጊ መላዕክት ሥራዎቻቸውን ይሠሩልናል።
የበቀል ጊዜው ሩቅ አይደለምና ጦርነት አውጀው በሕዝባችን ላይ ግፍ የሚሠሩትን የዘመናችንን ከንቱ ምስጋና-ቢስ አማሌቃውያን አህዛብን ከእግዚአብሔር መላእክት ጋር ሆነን ከቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ጠራርገን እናጠፋቸዋለን፤ በቃ! የመለሳለሻው ጊዜ አክትሟል! ሌላ ነገር ሊኖር አይችልም።
❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ከምዕራፍ ፲፯ – ፳]❖❖❖
አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል።
❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፯]❖❖❖
፩ አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።
፪ እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።
፫ ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
፬ የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፤
፭ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።
፮ በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
፯ ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።
፰ ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።
፱ ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ።
፲ በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ።
፲፩ መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም ድንኳኑ፤ በደመናት ውስጥ የጨለማ ውኃ ነበረ።
፲፪ በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።
፲፫ እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።
፲፬ ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።
፲፭ አቤቱ፥ ከዘለፋህ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የ መሠረቶችም ተገለጡ።
፲፮ ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።
፲፯ ከብርቱዎች ጠላቶቼ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።
፲፰ በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ።
፲፱ ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።
፳ እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል።
፳፩ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁም።
፳፪ ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ሥርዓቱንም ከፊቴ አላራቅሁም።
፳፫ በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ።
፳፬ እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።
፳፭ ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤
፳፮ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።
፳፯ አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።
፳፰ አንተ መብራቴን ታበራለህና፤ እግዚአብሔር አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።
፳፱ በአንተ ከጥፋት እድናለሁና በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።
፴ የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።
፴፩ ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?
፴፪ ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥
፴፫ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።
፴፬ እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።
፴፭ ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።
፴፮ አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
፴፯ ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።
፴፰ አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ።
፴፱ ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።
፵ የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።
፵፩ ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ አልሰማቸውም።
፵፪ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥ እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ።
፵፫ ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።
፵፬ በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤ የባዕድ ልጆች ደለሉኝ።
፵፭ የባዕድ ልጆች አረጁ፥ በመንገዳቸውም ተሰናከሉ።
፵፮ እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ አምላኬም ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።
፵፯ በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል።
፵፰ ከጠላቶቼ የሚታደገኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።
፵፱ አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ።
፶ የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይሰጣል።
____________________
Leave a Reply