❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፪]❖❖❖
፱ እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።
፲ ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።
፲፩ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣ ጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
የቤተልሔም ኮከብ በመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን መሠረት ሦስቱን ጠቢባን ከምሥራቅ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ስፍራ የመራቸው ኮከብ ነው።
የቤተልሔም ኮከብ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስን ልደት ያመለክታል. በዚህ ምክንያት ነው ፣ በገና ወቅት ፣ ይህ ክስተት ሲዘከር ፣ የቤተልሔም ባህርይ ኮከብ በተለያየ መልክ ይታያል።
የቤተልሔም ኮከብ ለክርስቲያኖች እንደ አማኝ ሕይወታቸውን የሚመራ ብርሃን ፣ ተስፋ እና እምነት ይወክላል፣ ዝነኞቹን ሶስት ጠቢባን ሰዎች እንደመሩት ፡፡ ለዚህም ነው ለገና በዓል አከባበር እና መታሰቢያ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ምልክቶች አንዱ የሆነው፡፡
☆ በኢትዮጵያ የክልሎች (ትግራይና አማራ) ባንዲራዎች ላይ ያረፈው የሉሲፈር ኮከብ ግን የክርስቶስ ተቃዋሚው ኮከብ ነው። ይህ መቅሰፍተኛ ኮከብ ከትግራይና መላዋ ኢትዮጵያ መወገድ አለበት።
🔔 አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ / አቦ ሳሪስ ቤተ ክርስቲያን 🔔
ጥር ፭/5 – ልደቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተወለዱት ታህሳስ ፳፱/29 በዛሬው የትጌታችን ልደት ነው። ነገር ግን ዕለቱ ትልቅ ሚስጥር የያዘ ነውና አባቶቻችን የጌታ ልደት ዘምረው ጣዕሙ ሳያልቅ ቅዳሴ ይገባሉ። ስለዚህ የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ከሚቀር ልደታቸው ጥር 5 እንዲከበር ስርዓት ሰርተዋል።
“እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡“ (እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“” መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ፡ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው ፴/30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ በዚሁ መሰረት አባታችን መጋቢት ፳፱/29 ተጸንሰው ታህሳስ ፳፱/29 ተወለዱ፡፡ ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው “ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽ ልመት ውስተ ብረሃን” ብለው በማመስገናቸው ኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ።
ሦስት ዓመት ሲሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት አበ ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው፡፡ አባ ዘመደ ብርሃን አሳድጎ አስተምሮ ከመዓርገ ምንኩስና አድርሷቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ “ሀብተ ፈውስ” ተሰቷቸዋል፡፡ በአንድ ቀን እልፍ እውራንንና አንካሳን ፈውሷል፡፡ ኋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳቱ ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ የጸሎት ግብር የሚያስፈቷቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል በክንፉ ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው፡፡ በገድልህ በትሩፋትህ ከሞተ ነፍስ ከርደተ ገሃነም የሚድኑ ብዙ ነፍሳት አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ፡፡ ኑሮህም ከ፷/60 አናብስተና ከ፷/60 አናምርት ጋር ይሁን አላቸው፡፡ ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ? ብለው ጌታን ጠየቁት፡፡ “ዘኬድከ ጸበለ–እገሪከ ይልህሱ ወበውእቱ ይጸግቡ…” የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያው ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ፡፡ ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና አናምርት ጋር ይኖሩ ጀመር።
ዳንኤል በአናብስት ጉድጓድ በጣለ ጊዜ አናብርቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ የረገጡትን ትቢያ ይልሱ ይታዘዟቸውም ነበር፡፡ በዚህ መልኩ መልአኩ ፴/30 ዓመት ከቆዩ በኋላ ጌታ ባንድነት በሦስትነት ተገልጾ “ምን ላድርግልህ ትሻለህ?” አላቸው፡፡ መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድረ ጋቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት፡፡ ፫ሺህ/3000 ኃጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል።
“ሑር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህየኒ ሀላዉከ ነፍሳት ዘታወጽኦሙ – ወደ ኢትዮጵያ ሂድ” አላቸው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፋስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል፡፡ ዳግመኛም ወደ ዝቋላ ደብር ቅዱስ ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጽሐ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሃጢአት አይተው ከባሕሩ በራሳቸው ቆመው ይጸልዩ ጀመር፡፡ አርባ ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ “ዘገብረ ተዝካረከ ወዘጸውዐ ስመከ እምሕር ለከ ብሎሀል” አላቸው፡፡ መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ አልወጣም ብለው መቶ አመት ሲጸልዩ ኑረዋል፡፡ ከመቶ አመት በዃላ ጌታ “ተንስእ ወጻእ መሐርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ምሬለሃለሁ ውጣ” ብሏቸው ወጥተዋል።
ከዚህ በኋላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው ሰባት ዓመት እንደ ትኩል ዓምድ ሆነው ዓይናቸውን ሳይከድኑ ሰባት ዓመት ቆመው ጸልየዋል፡፡ ሰይጣንም በምቀኝነት ተነሳስቶ ቁራን መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው፡፡ ሁለት ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍ ብሏቸው አድነዋቸዋል፡፡ ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቋላ ሲሄዱ ን በአምሳለ አረጋውያን ከጥላ ስር አርፈው አገኟቸው፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነናል አዝለህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን አሏቸው፡፡ አዝለው ከሸኙአቸው በኋላ በአንድነት በሦስትነት ሆኖ ታያቸው ደንግጠው ወደቁ፡፡ አንስተው ዝቋላ ወርደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አሏቸው፡፡በዘባነ መብረቅ ደርሰው ሰባቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አርድገው እልፍ አዕላፍ አጋንንትን በማጭድ አጭደዋል፡፡ እንዲህ ለሰሚዕ እፁብ በሆነ ግብር ዓመት በኢትዮጵያ ፪፻፷፪/262 ኖረው በ፭፻፷፪/562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል።
መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡ [ሮሜ 12፡12፣ 15፡30፣ያዕ5፡16፣ መዝ.88፡3፣111፡6 ምሳ.10፡7 ማቴ10፡40-42]
ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግስት መሆኑ ስለሚታወቅ ከ፱/9- ፲፬/14ኛው ም/ዓ ድ/ል/ክ መሆኑ ነው፡፡
__________________