Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2022
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Solemn Christmas Celebration for Ethiopian Orthodox Christian Refugees in Sudan

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 6, 2022

🔔 For thousands of Ethiopians who have fled fighting in the Tigray region to Sudan, this year’s Orthodox Tewahedo Christmas on January 7 is a sombre celebration. There will be little feasting for those living hand-to-mouth in the crowded Um Raquba refugee camp.

👉 ልክ ዓምና በዛሬው ዕለት ያቀረብኩት ጽሑፍ

💭 የልደት በዓል በስደተኞች ካምፕ | Ethiopian Refugees at Christmas Mass Pray for Return Home

ጌታችን በበረት ተወልዷል፣ በደሃ ቤት አድሯል፣ ከብርድ መከለያ ጨርቅን ፈልጓል፣ ፍጥረትን የሚመግብ እርሱ ከእናቱ የድንግልናዋን ወተት ለምኖ አልቅሷል፣ በእመቤታችን ዕቅፍ ሆኖ ወደ ግብጽ ተሰድዷል፣ እንደ ሕፃናት በጉልበቱ ድኋል፣ ለእናቱ እየታዘዛት ጥቂት በጥቂት አድጓል። ከአደገም በኋላ ራሱን የሚሰውርበት ጎጆ ሳይኖረው በተራራ ተንከራቷል፣ ተርቧል፣ ከኃጢአተኞች በደረሰበት ተቃውሞ ተሰድቧል፣ ተገፍቷል። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ሆኗል።

ጌታችን ከእኛ ጋር ለመሆን ብቻ ሳይሆን በእኛ ውስጥ ለመኖር በእለተ አርብ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ተሰጥቶናል። እኛስ ወደ እርሱ ሊያቀርበን ይህን ሁሉ ከሆነልን አምላክ ጋር ለመኖር ምን አደረግን? ስንቶቻችን ነን ከትግራይ ለመሰደድ ስለተገደዱትና በሃገራቸው በመሰቃየት ላይ ስላሉት ወገኖቻችን ያሰብን? ስንቶቻችን ነን ልደቱን ከእነዚህ ወገኖቻችን ጋር ለማክበር ፈቃደኘነታችንን ያሳያን? ንስሐ ገባን? ሥጋ ወደሙን ተቀበልን?

አሜሪካንን በአውሎ ነፋስ የሚያናውጣት እስትንፋስ ከየት አካባቢ እንደሚነሳ ደርሰውበታል፤ በአሜሪካ እየተካሄደ ያለውን ነውጥ የሚቀሰቅሰው ኃይል ከየት በኩልም እንደሚመነጭ ያውቁታል። የዚህ በትግራይ ላይ የታወጀው ጦርነትም አንዱ ምክኒያትም ይህ ነው። ጦርነቱ ለእኛ ለግብዞቹ የማይታየንና የማናውቀው የዋናው የመንፈሳዊ ውጊያ አንዱ አካል ነው። አምላካችንን እንዳልቻሉትና እንደማይችሉት አውቀዋል፤ ስለዚህ በስጋዊ የበቀል ጥቃት የእግዚአብሔርን ልጆች በዚህ መልክ ማጥቃት ነበረባቸው። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ “የአውሎ ነፋሱን መንሻ በኑክሌር ብንመታውስ?” ወይንም “ግብጽ የሕዳሴውን ግድብ በቦንብ ትመታዋለች ወዘተ” ማለታቸው እኮ ዝም ብለው አልነበረም፤ የጦርነቱን መምጣት እየጠቆሙን እንጂ። ለአሜሪካ የሚበጃት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ነበሩ፤ ነገር ግን አሜሪካ ወንጀሏ በጣም ስለበዛ አብዮት አህመድ ወኪሏ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት በጀመረበት ዕለት ምርጫውን አካሄዳና ሌቦቹ ዲሞክራቶች ምርጫውን አጭበርብረው (የእነ ኦባማና ጆርጅ ሶሮስ እጅ አለበት)ያው ዛሬ ህፃናት ደፋሪውን፣ አስወራጁንና የሰዶማውያኑን እንቅስቃሴ ደጋፊው ወስላታ ጆ ባይደንን ስልጣን ላይ አወጡት። ከዚህ በፊትም እንዳወሳሁት ጆ ባይደን ስልጣን ላይ ብዙ የሚቆይ አይመስለኝም፤ ዙፋኑ የተዘጋጀው ከሂላሪ ክሊንተን ቀጥላ በኤልዛቤል መንፈስ ከሁሉም በልጣ ለተጠመቀችው ለመጪዋ ምክትል ፕሬዚደንት ለአመንዛሪዋ ካማላ ሃሪስ ነው። አሜሪካ አብቅቶላታል!

ወደ ሃገራችን ስንመለስ፤ እየተፈጸመ ካለው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ዓለም ስለ ኢሳያስ አፈቆርኪ በጦርነቱ ስለመሳተፉ ማጉረምረም ሲጀምርና “ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚለውን አልማር ባይ ከንቱ መልሶ ለማስተኛት እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ “የህወሃትን አመራሮች ያዝኩ፤ ገደልኩ” ይላል። በነገራችን ላይ ውጭ ከወጡት በቀር በትግራይ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም አመራሮች ከያዟቸው ከወር በላይ ሆኗቸዋል፤ ግን ዋናው ዓላማቸው በንጹሐን ትግሬዎች ላይ የሚካሄደውን ጭፍጨፋ ማካሄድ ነውና ይህን ጭፍጨፋ ስልታዊ በሆነ መንገድ ለመቀጠል ሲሉና ፀረትግሬ የሆኑትን ጋሎችና ጋላማራ መንጋዎቻቸውን ለማስደስት ሲባል አስፈላጊ በሆነበት ቀን እያወጡ “እንትናን ያዝንላችሁ ገደልንላችሁ!” ይላሉ። ጭፍጨፋውን በአጭር ጊዜ አገባድደው መፈጸም አይፈልጉም። ቀስ በቀስ ነው፤ እስከ ስድስት ሚሊየን ትግሬዎችን የመጨፍጨፍ ዕቅድ ነው ያላቸው። ስድስት ሚሊየን አይሁድ ፥ ስድስት ሚሊየን ትግሬ። ይህን ዕቅድ የማጨናገፍ ችሎታ፣ ብቃትና ግዴታ ያለብን እኛ ኢትዮጵያውያን መሆን ነበረብን፤ ያለፍት ቀናት፣ ሳምንታት እና ወራት እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከተሞች ለሰላምና ፍቅር የሚጮኹ ዜጎች በመስቀል አደባባይ ወጥተው “ጦርነቱ እና ጭፍጨፋው ይቁም!” እያሉ ጩኸታቸውን የሚያሰሙባቸው መሆን ነበረባቸው። አለመታደል ሆኖ በጣም የተረገመ ትውልድ ስላለን ከገዳዩ ጋር እንጂ ከተገዳዩ ጋይ የማይቆም፣ በብርሃን ፋንታ ጨለማን የሚሻ፣ በሕይወት ፈንታ ሞትን የሚመርጥ፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን የሚፈልግ በመሆኑ መከራውና ሰቆቃው ለሁሉም እስኪዳረስ ድረስ ይቀጥላል። ግራኝ አብዮት አህመድን የሚደፋና ኢትዮጵያን ከሞትና ባርነት መንፈስ ነፃ የሚያወጣ አንድ ጀግና ኢትዮጵያዊ እንኳን መጥፋቱ በጣም ያሳዝናል። እስኪ ይታየን ከውጭ ሃገራት ጋር ሆኑ በኢትዮጵያውያን ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመ መሆኑ በይፋ ታውቆ እንኳን ዛሬም የስልጣን ወንበር ላይ ቁጭ ብሏል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴት? እንዴት? እንዴት?

በትግራይ እየተፈጸመ ያለው ጭካኔ ግን በዓለማችን ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ዓይነት ጭፍጨፋ ነው። ሃያላኑን ሃገራት፣ የተባበሩት መንግስታትን፣ የኖርዌየን የኖቤል ሰላም ሽልማት ኮሚቴ ሁሉንም አስደንግጧቸዋል፤ ስለዚህ እንዳላዩ፣ እንዳልሰሙና እንደማያውቁ ጸጥ በማለት ወደ ቀጣዩ የቤት ስራቸው ዞረዋል። ዛሬ ሉሲፈራውያኑ የአውሬውን ክትባት ለኮሮና ነው ብለው በአውሬው ወኪላቸው በግራኝ አብዮት አህመድ በኩል በጅምላ ለምስጠት በመዘጋጀት ላይ ናቸው። አምላካችን ግን ከእነርሱ ጋር ነው! እኛስ ከማን ጋር ነን? ከሚታየው ወይንስ ከማይታየው ጋር? ከዚህ ዓለም ጋር ወይንስ ከወዲያኛው ዓለም ጋር? አቤት የሚጠብቀን ፍርድ! አባ ዘ-ወንጌል ፲/10% የሚሆኑት ተዋሕዷውያን ብቻ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማየት እንደሚተርፉ ሲነግሩን ፀረ-ትግሬ ያልሆኑትን ኢትዮጵያውያን ብቻ ማለታቸው እንደሆነ እነዚህ ቀናት እያሳዩን ነው።

____________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: