💭 በብሉይ ኪዳን ዘመናት የከነዓን/ የፍልስጥኤማውያን አምስት ከተማዎች፤ ጋዛ፣ አዛጦን፣ አስቀሎና፣ አቃሮን፣ ጌት ናቸው። በዘመነ ኦሪትም ብዙ ጊዜ አመጸኞቹ ፍልስጥኤማውያን ከእነዚህ ከተማዎች እስራኤልን ያጠቁ ነበር።
❖ የጽዮን ምርኮ ❖
💥 ታቦተ ጽዮን ዳጎንን ሰባበረችው[፩ኛ ሳሙ. ፭፥፩–፭]
ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ድል አድርገው ታቦተ ጽዮንን ወደ አዛጦን ወሰዱአት፡፡ በዚያም ከቤተ ጣዖታቸው አስገብተው ዳጎን የተባለውን ጣዖት ከፍ ባለ መቀመጫ አድርገው እርሷን ግን ከታች አስቀመጧት፡፡ ሲነጋም የአዛጦን ሰዎች ማልደው ለጣዖቱ ሊሰግዱ ቢሔዱ ዳጎንን በግምባሩ ወድቆ አገኙት፡፡ አንሥተው ወደ ቦታው መለሱት፤ በነጋ ጊዜ እንደልማዳቸው ቢሔዱም እነሆ ዳጎን በታቦተ ጽዮን ፊት በምድር ላይ ወድቆ ነበር፡፡ ራሱ፣ እጆቹም ተቈራርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ደረቱ ብቻውን ቀርቶ ነበር፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “ንጉሥ በመንግሥቱ ገበሬ በርስቱ እንደማይታገሥ እግዚአብሔርም በአምላክነቱ ከገቡበት አይታገሥም” እንዲሉ ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦተ ጽዮንን በጣዖት ቤት ከጣዖት እግር ሥር በማስቀመጣቸው እግዚአብሔር በቍጣ ተነሣባቸው፡፡ ኃይሉንም በታቦቱ ላይ አሳረፈ፤ ታቦተ ጽዮንም ዳጎንን ቀጠቀጠችው፤ ሰባበረችው፡፡
ይህ ታሪክ የሐዲስ ኪዳን የማዳን ሥራ ምሳሌነት አለው፡፡ ቀደም ብሎ እንዳየነው ታቦተ ጽዮን የወላዲተ አምላክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ ታቦተ ጽዮን ዳጎንን እንደ ሰባበረችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇን አዝላ ወደ ግብጽ በምታደርገው የስደት ጕዞ በምታቋርጣቸው መንገዶችና መንደሮች ዅሉ ያሉ ጣዖታት ይሰባበሩ ነበር፡፡ በግብጽ ያሉ ጣዖታት ማንም ሳይነካቸው ተሰባብረዋል፤ በውስጣቸው አድረው ሲመለኩ የነበሩ አጋንንትም በአምሳለ ሆባይ (ዝንጀሮ) እየወጡ ሲሔዱ ይታዩ ነበር /ነገረ ማርያም/፡፡ ዳጎን በታቦተ ጸዮን ፊት በግምባሩ እንደ ተደፋ እመቤታችንም በስደቷ በሲና በረሃ ስትጓዝ ያገኟት ሽፍቶች መዝረፋቸውን ትተው በፊቷ ሰግደው ሸኝተዋታል፡፡ ዳግመኛም በዕለተ ዕረፍቷ አስከሬኗን አቃጥላለሁ ብሎ የአልጋውን ሸንኮር የያዘው ታውፋንያ የተባለው አይሁዳዊ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እጁን በሰይፍ በቀጣው ጊዜ እመቤታችን ይቅር ትለውና ትፈውሰው ዘንድ ግምባሩን መሬት አስነክቶ ሰግዶላታል፡፡
እንደዚሁም ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታቦተ ጽዮን ይመሰላል፡፡ ዳጎን በታቦተ ጽዮን ፊት በግምባሩ ተደፍቶ እንደ ተገኘ ጌታችን በሥጋ ሰብእ ተገልጦ ወንጌለ መንግሥት በሚያስተምርበት ዘመንም አጋንንት “ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ጊዜያችን አታጥፋን” እያሉ ይሰግዱለት እንደ ነበር በቅዱስ ወንጌል በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ ሐዋርያው ያዕቆብም “አጋንንትኒ የአምኑ ቦቱ ወይደነግፁ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤” በማለት ተናግሯል /ያዕ. ፪፥፲፱/፡፡ ታቦተ ጽዮን ዳጎንን እንደ ቀጠቀጠችው (እንደ ሰባበረችው) ዅሉ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ቀጥቅጧቸዋል፡፡ ታቦተ ጸዮን የወርቅ ካሣ ተሰጥቷት ከምድረ ፍልስጥኤም እንደ ወጣች ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በወርቀ ደሙ ካሣነት የሲዖልን ነፍሳት ከሲዖል አውጥቷል፡፡
ጌታችን ለድኅነተ ዓለም በመስቀል ተሰቅሎ አዳምን ወክሎ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምንት ኀደገኒ)፤ አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” በማለት ሲጣራ ሰምቶ ዲያብሎስ “ሥጋውን ወደ መቃብር፣ ነፍሱን ወደ ሲዖል ላውርድ” ብሎ ቀረበ፡፡ የጌታ ጩኸትም አንድም ለአቅርቦተ ሰይጣን ነውና ሰይጣንን በአውታረ ነፋስ /ሥልጣነ መለኮት/ ወጥሮ ያዘው፤ ያን ጊዜ ዲያብሎስ “መኑ ውእቱ መኑ ውእቱ፤ ማነው ማነው” እያለ መለፍለፍ ጀመረ /ትምህርተ ኅቡአት/፡፡ ከብዙ መቀባጠር በኋላም “አቤቱ ጌታዬ በድዬሃለሁ፤ ነገረ ልደትህን የተናገሩትን ነቢያት እነ ኢሳይያስን በምናሴ አድሬ በመጋዝ አስተርትሬአለሁ፤ ለበደሌ የሚኾን ካሣ የለኝም፤ የሲዖልን ነፍሳት በሙሉ እንደ ካሣ አድርገህ ውሰድ፡፡ እኔንም ያለ ጊዜዬ አታጥፋኝ” በማለት አጥብቆ ለመነው፡፡ ጌታችንም ዲያብሎስን አስሮ ከአዳም ጀምሮ በሲዖል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ የሲዖል ኃይላት ተሰባበሩ፤ ከመለኮቱ ብርሃን የተነሣም የሲዖል ጨለማ ተወገደ፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን፣ ሊቃነ አጋንንትን፣ ሠራዊተ አጋንንትን፣ የሲዖልን ኃይላትን አጥፍቶልናልና ቅዱስ ዳዊት ከአንድ ሺሕ ዓመት በፊት “እስመ ሰበረ ኆኃተ ብርት ወቀጥቀጠ መናሥግተ ዘኀፂን፤ የናሱን ደጆች ሰብሯልና፡፡ የብረቱንም መወርወሪያ ቀጥቅጧል፤” በማለት ዘመረ /መዝ. ፻፮፥፲፮/፡፡ ነቢዩ አጋንንትን ኆኀተ ብርት (የነሐስ ደጆች) ብሎአቸዋል፡፡ የነሐስ መዝጊያ ጠንካራ እንደ ኾነ አጋንንትም በአዳምና ልጆቹ ላይ መከራ አንጽተውባቸው ነበር፡፡ የአጋንንት ክንድ በሰው ልጆች ላይ ከብዶ ነበርና ሊቃነ አጋንንትን መናሥግተ ኀፂን (የብርት መወርወሪያ ወይም ቍልፍ) ብሏቸዋል፡፡ ቤት በብርት መወርወሪያ (ቍልፍ) ከተዘጋ እንደማይከፈት ሲዖልም ለ፶፭፻ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ) ዘመን ተዘግታ የነፍሳት ወኅኒ ቤት ኾና ኖራለችና አዳሪውን በማደሪያው ጠራው፡፡ ከመዝጊያው መወርወሪያው(ቍልፉ) እንዲጠነክር ወይም መዝጊያ በቍልፍ እንዲጠነክር ከአጋንንት አለቆች (ሊቃነ አጋንንት) ይበረታሉና መናሥግተ ኀፂን (የብረት መወርወሪያ) አላቸው፡፡ አምስቱ የፍልስጥኤም ነገሥታት ሲሰግዱለት የነበረውን ዳጎንን ታቦተ ጽዮን እንደ ቀጠቀጠችው ዅሉ መድኀኒታችን ክርስቶስም ለ፶፭፻ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ) ዘመን የተደራጀውን የአጋንንት ኃይል በሥልጣኑ ሰባብሮታል፡፡
🔔[መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፭፥]🔔
፩ “ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፤ ከአቤንኤዘርም ወደ አዛጦን ይዘውት መጡ።”
፪ ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስደው ወደ ዳጎን ቤት አገቡት፥ በዳጎንም አጠገብ አኖሩት።
፫ በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፤ ዳጎንንም አንሥተው ወደ ስፍራው መለሱት።
፬ በነጋውም ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቈርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር፤ የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር።
፭ ስለዚህም የዳጎን ካህናት ወደ ዳጎንም ቤት የሚገቡት ሁሉ በአዛጦን ያለውን የዳጎንን መድረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይረግጡም።
፮ የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፥ አጠፋቸውም፥ አዛጦንንና ድንበራቸውንም በእባጭ መታቸው።
፯ የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ። እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አይቀመጥ አሉ።
፰ ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ወደ እነርሱ ሰበሰቡና። በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ? አሉ፤ እነርሱም። የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይዙር ብለው መለሱ። የእስራኤልንም አምላክ ታቦት ወደዚያ ተሸከሙት።
፱ ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማይቱ ላይ ሆነች፤ ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማይቱን ሰዎች መታ፥ እባጭም መጣባቸው።
፲ የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣ ጊዜ አስቀሎናውያን። እኛንና ሕዝባችንን ሊገድሉ የእስራኤልን አምላክ ታቦት አመጡብን ብለው ጮኹ።
፲፩ በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና፥ የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው። የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ፥ እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ።
፲፪ ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፤ የከተማይቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ።
👉 „IRAN + UAE That Have Used Drones to Exterminate Christians of Ethiopia, Now Hit by M6.5 Earthquake”
💭 የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ለማጥፋት የሞከሩት ኢራን + የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አሁን M6.5 የመሬት መንቀጥቀጥ ተመቱ።
💭 የጊዜ ጉዳይ ነው፤ በባቢሎን ዱባይ የሚገኘው የዓለማችን ረጅሙ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ“ቡርጅ ኻሊፋ” እንደ ቀዳማዊቷ ባቢሎን ግምብ + እንደ ኢሽታር በር ሲደረማመስ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።
🎺 ሰባተኛው መለከት
❖❖❖[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፩]❖❖❖
፲፭ ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም። የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል
፲፮ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው
፲፯ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ። ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
፲፰ አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።
፲፱ በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
💭 I believe this earthquake is The Almighty God-Egziabher’s wrath announcement-sign! The Ark of The Covenant is doing Its JOB! It’s just the beginning.
❖❖❖ [Revelation 11:15–19] ❖❖❖
🎺 The Seventh Trumpet
“Then the seventh angel blew his trumpet, and there were loud voices in heaven, saying, “The kingdom of the world has become the kingdom of our Lord and of his Christ, and she shall reign forever and ever.” And the twenty-four elders who sit on their thrones before God fell on their faces and worshiped God, saying, We give thanks to you, Lord God Almighty, who is and who was, for you have taken your great power and begun to reign. The nations raged, but your wrath came, and the time for the dead to be judged, and for rewarding your servants, the prophets and saints, and those who fear your name, both small and great, and for destroying the destroyers of the earth.” Then God’s temple in heaven was opened, and the ark of his covenant was seen within his temple. There were flashes of lightning, rumblings, peals of thunder, an earthquake, and heavy hail.”
_________________