Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2022
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 2nd, 2022

በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ | ፲፭ኛ ወር የአሕዛብ ፀረ-ጽዮናዊ ጂሃድ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 2, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 😇 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

🌞🌞🌞 ተክልዬ ፀሐይ የኢትዮጵያ ሲሳይ፤ “ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ፤ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ”🌞🌞🌞

መታሰብያቸው ለዘላለም ከሚኖረው ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላክን በአግባቡ ማምለክ ብናውቅብትና በተግባርም ለማሳየት ብንጥር ኖሮ እንደ አቡነ ተክለሐይማኖት ያሉትን ቅዱሳን አባቶችን ይዘን ከባዕዳውያን እስማኤላውያን ጋር አብሮ በአክሱም ጽዮን ላይ የዘመተውን አረመኔ ግራኝ አብዮት አህመድንና መንጋውን ሳንውል ሳናደር ተዋግተን ባስወገድነውና ሕዝባችንንም ከጨለማ ብሎም ከዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ የባርነት ቀንበር ነፃ አውጥተን ለብርሃኑ ባበቃነው ነበር።

✞✞✞

፲፭/15 ወራት ፀረጽዮናውያን የዘር ማጥፋት ወንጀል በሰሜን ኢትዮጵያ ፥ ግራኝና ጭፍሮቹ ዛሬም የጥፋት ዘመቻቸውን በድፍረት ቀጥለውበታል።

😈አረመኔው ግራኝ ልክ በተክለ ሐይማኖት ዕለት ጦርነቱን ጀመረው፣ ባለፈው መስከረም ልክ በተከለ ሐይማኖት ዕለት በሰይጣን ምራቅ ተቀባ ፥ ልክ ጂሃዱን በጀመረበት በአስራ አምስተኛው ወር ከአህዛብ እስማኤላውያን ጋር አብሮና ተደምሮ በጽዮናውያን ላይ ጭፍጨፋ ማካሄዱን ሳይወድ በግዱ አፉን ከፍቶ ይናዘዝ ዘንድ ተገደደ።😈

አሕዛብ በሠሩት ጕድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች”

የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝና አህዛብ እና መናፍቃን አጋሮቹ በአክሱም ጽዮን ልጆች ላይ፣ በቅዱስ ያሬድ ልጆች ላይ፣ በአቡነ አረጋዊ ልጆች ላይ፣ በአባ ዓቢየ እግዚእ ልጆች ላይ፣ በነገሥታት አፄ ካሌብ እና አፄ ዮሐንስ ልጆች እንዲሁም በፃድቁ አባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ልጆች ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋውን ከጀመሩ ልክ ዛሬ ፲፩ኛ ወሩ ነው። አዎ! ይህን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ጦርነቱን በአባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት ጀመረው። ለዋቄዮአላህሰይጣን የክርስቲያኖችን ደም የገበረበትን ዕለት እና ሥልጣኑን ለማደላደል በዓለ ንግሥናውንየሚያከብርበትን ዕለትም የመረጠው ሆን ብሎ በሰይጣናዊው ኢሬቻ ማግስት በብዚሁ ዕለተ አቡነ ተክለ ሐይማኖት ነው።

እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ ትግራይን ከኢትዮጵያ አባርረው፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ከፊል ሶማሌን እና ቤኒሻንጉል ጨፍልቀው በኢትዮጵያ ስም በዋቄዮአላህዲያብሎስ መንፈስ የምትመራዋና እስላማዊት ኦሮሚያ ካሊፋትን ለመመስረት በማለም ዛሬ በመጨፈር ላይ ያሉት እነ ግራኝ አብዮት አህመድም በእሳት እንደሚጠረጉ ለእነርሱ በቆመው ሕዝባቸውም ላይ እሳቱ እንደሚወርድባቸውና በፈርዖን ግብጽ የታዩት መቅሰፍቶች ሁሉ እንደሚመጡባቸው ምንም አልጠራጠርም። በእግዚአብሔር ፈቃድ እኛም የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን።

አዎ! የማይገባቸውን ያልማሉ፤ ዲያብሎሳዊ እቅዳቸውም ይሄ ነው፤ ነገር ግን በጭራሽ አይሳካላቸውም፤ የማይሳካላቸውም በተዋጊዎቹና በጦረኘኞቹ ኃይል አይደለም፤ እኛ ትክክለኛዎቹ ኢትዮጵያውያን የጽዮን ልጆች እስካለን ድረስ ምንም ነገር እንደማይሳካላቸው፣ እርስበርስ እንደሚተላለቁ፣ እንደማይሳካላቸውና አንድ በአንድ ከሃገረ እግዚአብሔር በእሳቱና በመቅሰፍቱ ተጠረራረገው ወደ ኤርታ አሌ እንደሚጣሉ በአባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ስም ቃል ልገባ እወዳለሁ።

✞✞✞ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን ፥ አዲስ አበባ ፥ በ፲፰፻፺፰ ዓ.ም ተመሠረተ✞✞✞

ሰባት ዓመት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሀገር፥ ለቤተክርስቲያን፥ ለምዕመናን እና ለዓለም ሁሉ የጸለዩት የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ረዲኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

✤✤✤ ተክለ ሐይማኖት ማለት “የሐይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ” ማለት ነው፡፡

ድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል

ፃድቁ አባታችን ብፁዕ አቡነ ተክለ ሐይማኖት በመልአኩ ትዕዛዝ ከደብረ ዳሞ ገዳም ወደሌላ ገዳም ለመሄድ ሲነሡ አበምኔቱ አባ ዮሐኒና መነኰሳቱ ሲሸኟቸው አቡነ ተክለ ሐይማኖት አርባ ክንድ ርዝመት ባለው ገመድ ገደሉን ለመውረድ እንደጀመሩ ገመዱን ሰይጣን ከካስማው ሥር ቆረጠባቸው። ቅዱስ አባታችን ግን በዚህ ጊዜ ስድስት የብርሃን ክንፎች ተሰጣቸውና እየበረሩ ክንፎቻቸውን እያማቱ ሦስት ምዕራፍ ሄደው ሲያርፉ አበምኔቱና መነኰሳቱ አይተዋቸው እጅግ ተደስተዋል። አባታችን ወደ ትግራይ ሄደው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ገብተው በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ከተቀበሉ በኋላ ተመልሰው ወደ ሐይቅ በመሄድ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ቆብና አስኬማን ሰጥተዋቸዋል። ከዚያም ወደ ዋሊ ገዳም ገብተው ከቅዱሳን ጋር ተገናኝተው በትሩፋት ላይ ትሩፋትን በገድል ላይ ገድልን ጨምረዋል።

ከ ፩ሺ፪፻፷፮ እስከ ፩ሺ፪፻፷፯ /1266-1267 ዓ.ም ለአንድ ዓመት ያህል የትግራይን ገዳማት በሙሉ በመጐብኘት ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ግብፅም በመሄድ በዚያ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ጎብኝተው መጥተዋል። ከዚህ በኋላ “ዳዳ” በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን ፸፭/75 ክንድ የሚረዝመውን ዘንዶ በጸሎት ኃይል በመስቀል ምልክት አማትበውበት በተአምራት ገድለውታል። በቦታው ላይ በአርባዕቱ እንስሳ ስም ቤተ ክርስቲያን አንጸው ታቦተ ሕግ አስገብተውላቸዋል። ከሴቶችና ከልጆች ሌላ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን አስተምረው መልሰው አጥምቀው አቊርበዋቸዋል። ✤✤✤

✤✤✤ የፃድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ጸሎታቸውና በረከታቸው ረድኤታቸውና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ፤ አሜን!✤✤✤

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ]✞✞✞

አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።

በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።

ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፥ ይሰናከላሉ ከፊትህም ይጠፋሉ።

ፍርዴንና በቀሌን አድርገህልኛልና፤ ጽድቅን እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።

አሕዛብን ገሠጽህ፥ ዝንጉዎችንም አጠፋህ፥ ስማቸውንም ለዘላለም ደመሰስህ።

ጠላቶች በጦር ለዘላለም ጠፉ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥ ዝክራቸውም በአንድነት ጠፋ።

እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ይኖራል፥ ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፤

እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።

እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው።

ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

፲፩ በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ፤

፲፪ ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።

፲፫ አቤቱ፥ እዘንልኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የምታደርገኝ፤

፲፬ ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፤ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ በማዳንህ ደስ ይለኛል።

፲፭ አሕዛብ በሠሩት ጕድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።

፲፮ እግዚአብሔር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው፤ ኃጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ።

፲፯ ኃጢአተኞች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም ሁሉ።

፲፰ ድሀ ለዘላለም አይረሳምና፥ የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘላለም አይጠፋም።

፲፱ አቤቱ፥ ተነሥ፤ ሰውም አይበርታ፥ አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።

አቤቱ፥ ፍርሃትን በላያቸው ጫንባቸው፤ አሕዛብ ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲]✞✞✞

በእግዚአብሔር ታመንሁ፤ ነፍሴን። እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሉአታላችሁ?

ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።

አንተ የሠራኸውን እነሆ እነርሱ አፍርሰዋልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደረገ?

እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዓይኖቹ ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።

እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል፤ ዓመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል።

ወጥመድ በኅጥኣን ላይ ያዘንባል እሳትና ዲን ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።

፯ እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: