Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2021
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 12th, 2021

የእውነት ሰው እንሁን | መሀመዳውያን + ጴንጤዎች + ዋቄፈታዎች ኦርቶዶክሶችን ከኢትዮጵያ አጥፍተው ብቻቸውን ሊኖሩባት? የማይሆን ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 12, 2021

❖❖❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፮]❖❖❖

“እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።”

❖❖❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፫፥፲፬፡፲፭]❖❖❖

እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።”

❖❖❖[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፴፫፥፩]❖❖❖

አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ በአንተም ላይ ወንጀል ሳይደረግ ወንጀል የምታደርግ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መወንጀልንም በተውህ ጊዜ ይወነጅሉሃል።”

________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

😈 የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ድሮን ፥ ጽዮናውያን ጽላተ ሙሴ አሏቸው❖

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 12, 2021

ከእርሱ ጋር ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ፤ ኪዳኑንም አረከሱ

በአውሎ ነፋሱ ሳቢያ ሕይወታቸው ላለፈው ነፍሳቸውን ይማርላቸው!✞

😈 የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ድሮን ፥ ጽዮናውያን ጽላተ ሙሴ አሏቸው❖

Mayfield Kentucky + Edwardsville, Illinois

አናግራሙ/Anagram = „AOC„ Ark of The Covenant

ጽላተ ሙሴ❖

ዛሬ በአውሮፓውያኑ 12/12/21 ነው። በስድስት የአሜሪካ ግዛቶች ያልተጠበቀ አውሎ ነፋስ ከፍተኛ ጥፋትና ውድመት አስከትሏል፤ በተለይ በ ሜይፊልድ ኬንታኪ ኤድዋርድስቪል ኢለኖይ።

ጽላተ ሙሴ ስራውን እየሠራ ነውን? የሚግርም ነው፤ አውሎ ነፋሱ የዓለማችን ቍ. ፪ ባለኃብት የሆነውን የአቶ ጄፍ ቢዞስን አማዞን የእቃ ግምጃ ቤት ሙሉም በሙሉ አውድሞታል። ሌላው የሚገርመው ደግሞ በየመንገዱ ፍርስራሾች ብዙ ዓለመታየታቸው ነው።

ባለፈው ሳምንት ላይ “ጽዮናውያን በም ዕራባውያን ከተሞች ጎዳናዎች ላይ የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ ይዘው ከመውጣት መቆጠብ አለባቸው፤ በሕዝባችን ላይ መቅሰፍት እያመጣ ነው።” ብዬ ነበር። ዛሬም እደግመዋለሁ፤ ጽዮናውያን ጽዮናዊ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ልብሳቸውን ለብሰው እና ጽላተ ሙሴን ተሸክመው በአሜሪካ ጎዳናዎች ምስጢራዊ በሆነ መልክ ድምጽ ሳያሰሙ በአክሱም ጽዮን ለምሕላ እንደሚያደርጉት ቢዘዋወሩ፤ ለአውሬው አሳልፋ የሰጠቻቸው ዓለም ተርበትብታ ትገዛላቸውና በዚህ የሕዝባችን ስቃይ እና ሰቆቃ በቀናት ውስጥ በተገታ ነበር። በዚህ ፻/100 እርግጠኛ ነኝ።

አቤቱ፥ ግፍንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይቼአለሁና አስጥማቸው እንደበታቸውንም ቍረጥ። በቀንና በሌሊት በቅጥርዋ ይከብቡአታል፤ ዓመፃና ድካም ኃጢአትም በመካከልዋ ነው፤ ተንኰልና ሽንገላ ከአደባባይዋ አይርቁም።

❖ ❖ ❖ [መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፶፬]❖ ❖ ❖

፩ አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ ልመናዬንም ቸል አትበል።

፪ ተመልከተኝ ስማኝም። በኀዘኔ ተቅበዘበዝሁ ተናወጥሁም፤

፫ ከጠላት ድምፅ ከዓመፀኛም ግፍ የተነሣ፤ ዓመፃን በላዬ ጥለውብኛልና፥ በቁጣም ጠልተውኛልና።

፬ ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ።

፭ ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ፥ ጨለማም ሸፈነኝ።

፮ በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ!

፯ እነሆ፥ ኰብልዬ በራቅሁ በምድረ በዳም በተቀመጥሁ፤

፰ ከዐውሎና ከብርቱ ንፋስ ሸሽቼ በፈጠንሁ አልሁ።

፱ አቤቱ፥ ግፍንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይቼአለሁና አስጥማቸው እንደበታቸውንም ቍረጥ።

፲ በቀንና በሌሊት በቅጥርዋ ይከብቡአታል፤ ዓመፃና ድካም ኃጢአትም በመካከልዋ ነው፤

፲፩ ተንኰልና ሽንገላ ከአደባባይዋ አይርቁም።

፲፪ ጠላትስ ቢሰድበኝ፥ በታገሥሁ ነበር፤ የሚጠላኝም ራሱን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ፥ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።

፲፫ አንተ ግን፥ እኩያዬ ሰው፥ ባልንጀራዬና የልቤ ወዳጅ፤

፲፬ መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ፤ በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን።

፲፭ ሞት ይምጣባቸው፤ በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ ክፋት በማደሪያቸውና በመካከላቸው ነውና።

፲፮ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እግዚአብሔርም ሰማኝ።

፲፯ በማታና በጥዋት በቀትርም እናገራለሁ እጮኽማለሁ፥ ቃሌንም ይሰማኛል።

፲፰ በእኔ ላይ ብዙ ነበሩና ከሚቃረቡኝ ነፍሴን በሰላም አድናት።

፲፱ ቤዛ የላቸውምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና ከጥንት ጀምሮ የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቍላቸዋል።

፳ ከእርሱ ጋር ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ፤ ኪዳኑንም አረከሱ።

፳፩ አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ፥ በልቡ ግን ሰልፍ ነበረ፤ ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ፥ እነርሱ ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።

፳፪ ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፤ ለጻድቁም ለዘላለም ሁከትን አይሰጠውም።

፳፫ አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ወደ ሞት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ የደም ሰዎችና ሸንጋዮች ዘመናቸው ግማሽ አይሞላም፤ እኔ ግን፥ አቤቱ፥ እታመንሃለሁ።

_______________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: