መድኃኔ ዓለም | ስሙ የጣፈጠ መድኃኒታችን እሱ ጽላት ነው፤ እናቱም ማዕጠንት ናት መስቀሉ ዙፋን ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2021
✞✞✞
👉ገብርኤል 👉ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 😇መድኃኔ ዓለም
መድኃኔ ዓለም ማለት፦ የ መድኃኑት ማለት ነው። በእርሱ አለም ስለዳነ (በሞቱ አለምን ስላዳነ) መድኃኔ የዓለም መድሃኒት እንለዋለን። ሉቃስ 2፥11 ላይ እኔሆ ለሕዝብ ሁሉ የምሆን መድኃኒት እንዳላለ ሉቃስ፤ ዮሐ.ወ ፩፥፳፱ ላይ መጥምቁ ዮሐንስ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የምያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” እንዳለው እንደገና በሮሜ ፭፥፲፪፡፳፩ ስናነብ በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት ሞት ወደ አለም እንደመጣ ሁሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትም አለም እንደዳነ ይናገራል…………..
እኛ ኦርቶዶክሳዊያን በነዚህ ስሞች አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችንን እናከብረዋለን እንጠራዋለን እናመልከዋለን ። “ኢየሱስ ብቻ ስሙ ነው ሌሎችን ከየት አመጣችሁ ለምን ባለወልድ አማኑኤል መድኃኔ ዓለም እያላቹ ትጠሩታላችሁ ኢየሱስ ማለት ብቻ እንጅ” የምሉ ወገኖቻችን አሉና እነዚህን ስሞችን እኛ ኦርቶዶክሶች ፈጥረንለት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሱ እራሱ እንደምጠራው መገናዘብ ይገባናል። ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይድረሰው የእኛ ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ። ክብር ለወለደችው ለድንግል!!!
_________________
Leave a Reply