Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2021
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    2930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 21st, 2021

ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤ ማን ይሰማል? ይላሉ። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2021

ዓምባ ቅዱስ ሚካኤል ውቖሮ

✞ ✞ ✞አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፤ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ። ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ። እነሆ፥ ነፍሴን ሸምቀውባታልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ። አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም። እነሆ፥ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ፤ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤ ማን ይሰማል? ይላሉ። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ

ድል አድራጊው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ያ የቀድሞ አመፀኛው አውሬ (ዲያብሎስ) የጥንት ተንኰሉ ሊተወው አልቻለምና፤ የጦር መሣሪያህን ታጥቀህ መጥትህ ድምጥማጡን አጥፋው። ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አውሬው ዲያብሎስ በመሀመድ በኩል መጥቶ በሃገረ ኢትዮጵያ፤ በውቅሮ ውስጥ(አል-ነጃሺ)ችግኙን ተክሏልና ከነችግኙ ነቃቅለህ የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ውስጥ ጨምረው። አሜን!✞ ✞ ✞

✞ ✞ ✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፶፰]✞ ✞ ✞

፩ አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፤ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።

፪ ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ።

፫ እነሆ፥ ነፍሴን ሸምቀውባታልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ። አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም።

፬ ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፤ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።

፭ አንተም አቤቱ፥ የኃያላን አምላክ፥ የእስራኤል አምላክ፥ አሕዛብን ሁሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ፤ ዓመፅ የሚያደርጉትን ሁሉ አትማራቸው።

፮ ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።

፯ እነሆ፥ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ፤ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤ ማን ይሰማል? ይላሉ።

፰ አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ።

፱ እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።

፲ የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል።

፲፩ ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፤ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።

፲፪ ስለ አፋቸው ኃጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥ መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ፥ በትዕቢታቸው ይጠመዱ።

፲፫ በቍጣ አጥፋቸው፥ እንዳይኖሩም አጥፋቸው፤ የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንዲገዛ ይወቁ።

፲፬ ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።

፲፭ እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ፤ ያልጠገቡ እንደ ሆነም ያንጐረጕራሉ።

፲፮ እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፤ በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፤ በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።

፲፯ ረዳቴ ሆይ፥ ለአንተ ለአምላኬ እዘምራለሁ፤ አንተ፥ አምላኬ፥ መጠጊያዬ ምሕረቴም ነህና።

______________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አሸባሪውን አብዮት አህመድ አሊን እና የፋሺስት ኦሮሞ አገዛዙን በአንዲት ሌሊት በእሳት ሰይፉ ፈጅቷቸው ይደር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2021

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወርዶ አሸባሪውን አብዮት አህመድ አሊን እና የፋሺስት ኦሮሞ አገዛዙን ሠራዊት ባፋጣኝና በአንዲት ሌሊት በእሳት ሰይፉ ፈጅቷቸው ይደር! የገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው አይለየን፣ በጸሎቱ ይማረን።

አዎ! ግራኝ አህመድ ቀዳማዊ በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ እርዳታ የአውሬ ተግባር ከመፈጸሙ በፊት ገናና እና ኃያል በአውሮፓውያኑ ዘንድ በጣም የሚከበሩና የሚፈሩ ኢትዮጵያውያን ነገሥታት ነበሩ። 😈 ጂኒው ግራኝ አብዮት አህመድ ዳግማዊ ከመምጣቱ ከሦስት ዓመታት በፊት ካዛሬው ውዳቂ የኦሮሞ አገዛዝ የተሻሉትና የአክሱምን ነገሥታት እንደገና ለማንሰራራት አስተዋጽኦ ለማበርከት ጥሩ ዕድል የነበራቸው የሰሜን ሰዎች ኢትዮጵያን ተረክብዋት ነበር። አለመታደል ነው፤ መቼስ ትንቢት ሊፈጸም ግድ ስለሆነ ቅድስት ሃገራችን በግራኝ እጅ በድጋሚ ወደቀች። አረመኔውን ኦሮሞ ግራኝ አብዮት አህመድን የዲፕሎማሲን ሀ ሁ ቆጥሮ ለመረዳት የዛሬዎቹ አውሮፓውያን የሸለሙት የኖቤል ሰላም ሽልማት እንኳን ሊረዳው አልቻለም። ይህን ያህል ነው ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱ። ሰሜን ኢትዮጵያውያን አዋርዶና አድቅቆ ኦሮሚያን ለመመስረት ያለውን ህልም ወደ አሰፈሪ ቅዠት እንለውጠዋለን፤ በቅዱስ ሚካኤል አጋዥነት በእሳት ግራኝን እና መንጋውን በእሳት የምንጠርግበት ጊዜ ሩቅ አይሆንምና።

❖የኅዳር ሚካኤል

“ወኲሉ መጽሐፍ ዘበመንፈሰ እግዚአብሔር ተጽሕፈ ይበቊዕ ለኲሉ ትምህርት ወተግሣጽ ወአርትዖ ወጥበብ ወጽድቅ ከመ ይትገሠጽ ብእሴ እግዚአብሔር ውስተ ኲሉ ምግባረ ሠናይ”

የእግዚአብሔር ሰው ፍጹም እና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርት ለተግሣጽ ልብን ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2ኛ.ጢሞ 3፥16-17 በማለት በታዘዝነው መሠረት የኅዳር ሚካኤልን የምናከብርበትን ምክንያት ከዚህ ቀጥለን እናቀርባለን።

ዘምስለ ዮሴፍ ተሰይጠ ከመ ይስፍር ሲሣዮ ለሕዝብ፡፡

ለሕዝበ እስራኤል ምግባቸውን ያዘጋጅ ዘንድ ከዮሴፍ ጋር ተሸጠ

(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ ሰዓታት)

የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸውን ዮሴፍን ለእስማኤላውያን ሽጠውት ሳለ እስማኤላውያን ለጲጥፋራ ሸጡት፡፡ ከጲጥፋራ ቤት ገብቶ ሲኖር ከዕለታት አንድ ቀን የጲጥፋራ ሚስት ሩካቤ ሥጋ እናድርግ አለችው፡፡ እሱም ጌታየ በሁሉ ቢያሰለጥነኝ በዚህ በአንች ላይ አላሰለጠነኝም አይሆንም አላት፡፡ እሷም አውቃ ልብሷን ከፊቷ ቀዳ አውልቃ ሰው ባርያ ሲገዛ መልከ ክፉውን ፀጉረ ከርዳዳውን ይገዛል እንጂ መልከ መልካሙን ገዝቶ ልድፈርሽ አለኝ አለች፡፡ አሕዛብም ዮሴፍን ወህኒ ቤት አገቡት፡፡ ዮሴፍም ከወህኒ ቤት ገብቶ ሳለ የፈርዖን ጠጅ አሳላፊውና እንጀራ አሳላፊው ተጣልተው ወህኒ ቤት ገብተው ሲኖሩ ከዕለታት አንድ ቀን እየራሳቸው ሕልም አይተው ነበርና ሕልማቸውን ለዮሴፍ ነግረውት ዮሴፍም እንደሕልማቸው ፈታላቸው፡፡ የጠጅ አሳላፊውን እንደነበርክ ትሆናለህ አለው፡፡ የእንጀራ አሳለፊው ዮሴፍ እንደነገረው ተሰቀለ፡፡ ዮሴፍም የጠጅ አሳላፊውን እንዳትረሳኝ አለው፡፡ከዕለታት አንድ ቀን ፈርዖን ሕልም ያያል፡፡ ሕልሙም ትርጓሜውም ይጠፋዋል፡፡ ሕልሙም እንዲህ ነው፡፡

ከወንዝ ውኃ ሲጠጡ ሰባት የከሱ ላሞች ሰባቱን ያልከሱትን የወፈሩትን ላሞች ሲውጧቸው አየ፡፡ ሕልሙንም የሚፈታለት አላገኘም፡፡ የጠጅ አሳላፊውም የሴፍ ያነን አትርሳኝ ያለው ነውና ዮሴፍም የሚባል ሕልም የሚፈታ አለ ብሎ ለንጉሡ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን ከወህኒ ቤት አስመጣው፡፡ ሕልሙንም ሰባት ዓመት ረኃብ ችግር ይሆናል አለው፡፡ ታዲያ ምን ላድርግ አለው፡፡ ለሰባት ዓመት የሚበቃ እህል አሰብስብ አለው፡፡ ያን ጊዜ ዮሴፍን ሾመው፡፡ ዮሴፍም ለሕዝቡ የሚበቃ እህል ሰበሰበ፡፡

በእየሀገሩ ረኃብ ጸና፡፡ ረኃብ ኮነ በበብሔሩ ወፈድፋደሰ በከነዓን ጸና ይላል፡፡ እህልም በከነዓን ጠፋ፡፡ የእየሩሳሌም ሰዎች እስራኤል ከግብጽ ሰዎች ውስጥ ዮሴፍ የሚባል የሰበሰበውን እህል ያቀና ነበርና ሸምቶ ለመብላት ወደግብጽ ተሰደዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ዮሴፍን የሾመው ሞቶ ሌላ ፈርዖን የሚባል ክፉ ንጉሥ ነገሠ፡፡ የእስራኤልን ብልሀትና ብዛት አይቶ ከእስራኤል ወገን ወንድ ልጅ ሲወለድ በሰይፍ ይቆረጥ ብሎ አዋጅ ነገረ፡፡ ሙሴ በዚያን ጊዜ ሲወለድ ከግንባሩ ላያ ብርሃን ተስሎበት፤ ተጽፎበት ተወለደ፡፡ እኅቱና እናቱ ፈርዖንን በመፍራት ከወንዝ ዳር በሳጥን ውስጥ አርገው ጥለውት እኅቱ ማርያም በጎዳና ሆና ትጠባበቀውና ታየው ነበር፡፡ አንዲት ሴት ልብስ ልታጥብ ወደ ወንዝ ስትሄድ ሳጥን አግኝታ ብትከፍተው ሙሴን አገኘችው፡፡ የንጉሡ ልጅ ሰውነቷን ልትታጠብ ሂዳ አገኘችውም ይላሉ፡፡ እኅቱ ማርያምም አውቃ ከእስራኤል ወገን ልጅ የሞተባት አንዲት ሴት አለችና ታሳድገው አለቻት፡፡ አምጫት አለቻት፡፡ ለእንበረም ሚስት ለዮካብድ ሰጠቻት፡፡ ዮካብድም ከቤት ወስዳ ሙሴን ሦስት ዓመት አሳደገችው፡፡ ከዚህ በኋላ ሙሴ ከፈርዖን ቤት አደገ፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ፈርዖን በእስራኤል ላይ ፍርድ ሲያጣምም አየው፡ ከአየው በኋላ ሙሴ ፈርዖንን በጥፊ መታው፡፡ ፈርዖንም ተናዶ ሊገድለው ሲል መካሮቹ/አማካሪዎቹ ንጉሥ ሆይ ሕፃን ምን ያውቃል እሳትና ፍትፍት ቢያቀርቡለት ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን ይጎርሳል አሉት፡፡ እስኪ አቅርቡለት አላቸው፡፡ ቢያአቀርቡለት ሙሴ ወደ ፍትፍቱ እጁን ሊሰድ ሲል መልአኩ በረቂቅ ነገር ወደ እሳቱ መለሰው፡፡ ሙሴ ልቱት (ኮልታፋ) የሆነበት ምክንያት ይህ ነው። ስለዚህ ፈርዖን ከመግደል ተወው፡፡ እንዲህ እያለ ከአደገ በኋላ ከዕለታት አንድ ቀን ግብጻዊና ዕብራዊ በልብስ ማጠቢያ ተጣልተው ሳለ ለዕብራዊው አድልቶና ተረድቶ ግብጻዊውን ገድሎ አሸዋ አለበሰው፡፡ ይህ ነገር በፈርዖን ዘንድ አልተሰማም ነበር፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ደግሞ ግብጻዊና ዕብራዊ ተጣልተው ሙሴ ሊገድል ቀርቦ ሳለ ግብጻዊው አንስቶ ከዚህ ቀደም ቢጣሉ ግብጻዊውን ገደልክ ሳይሰማብህ ቀረ ቢለው ያን ጊዜ ሙሴ ፈርቶ ወደምድረ ምድያም ተሰደደ፡፡ ከዚህ በኋላ የዮቶር ልጆች በጎቻቸውን ሲያጠጡ የሀገራቸው ውኃ ለሀምሳ ሰው የሚፈነቀል ድንጋይ ተገጥሞ ነበር፡፡ ሙሴን ከዚያ አግኝተው ፈንቅልልን አሉት፡፡ መጥቶ ለሀምሳ የሚፈነቀለውን ድንጋይ ብቻውን ፈንቅሎ በጎቻቸውን አጠጥቶላቸዋል፡፡ ፈጥነውም ወደቤታቸው ተመልሰዋል፡፡ አባታቸውም ዮቶር ፈጥናችሁ መጣችሁ አላቸው፡፡ እነሱም አንድ ሰው አግኝተን ብቻውን ፈንቅሎ አጠጥቶልን ፈጥነን መጣን አሉት፡፡ ዮቶርም እንዲህ ያለውን ሰው ለምን ትታችሁት መጣችሁ አሁንም ሂዱና አምጡት አላቸው፡፡ እነሱም ሂደው አመጡት፡፡ ሙሴም ከዮቶር ቤት አደረ፡፡ ዮቶርም ልጁን አጋባው፡፡ ሙሴም ከዮቶር ቤት በግ ሲጠብቅ ኖረ፡፡

ኢሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ እስራኤል/ የእስራኤል አምላክ በዚህ ሰማይ የለምን?

እስራኤል ከግብጽ ውስጥ ሲኖሩ ንጉሡ ፈርዖን በጣም ያሰቃያቸው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ራሄል የምትባል ርጉዝ ሴት ባሏ ሞቶ በባሏ ምትክ ኖራ እርገጭ ተብላ ኖራ የምትረግጥ ነበረች፡፡ ፈርዖን ለሕንጻ ጭቃ ሲያስቦካት ከዚያ ገብታ ጭቃ ስታቦካ ምጥ መጣባት፡፡ በዚያን ጊዜ ለፈርዖን ብታመለክት ከዚያው አብረሽ ርገጭው የሰው ደም ሕንፃ ያጠብቃል፤ያጸናል አላት፡፡ ከዚህ በኋላ ራሄል ከዚያው መንታ ልጆች ወልዳ ከጭቃው ላይ አብራ ረግጣቸዋለች፡፡ በዚያን ጊዜ ምርር ብላ ኢሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ እስራኤል/ የእስራኤል አምላክ በዚህ ሰማይ የለምን? ብላ ብታለቅስና እንባዋንም ወደ ላይ ብትረጨው ቅድመ እግዚአብሔር ከመንበረ ጸባዖት ደርሷል፡፡

ሰማዕኩ ገዓሮሙ ለሕዝብየ ወወረድኩ ከመ አድኅኖሙ/ የሕዝቤን ጩኸት ሰምቻለሁና አድናቸው ዘንድ ወረድኩ !

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የራሄልን ጩኸቷንና ግፏን በመመልከት ከዕለታት አንድ ቀን በደብረ ሲና ዕፀ ጳጦስ ከምትባል እንጨት ሥር ጌታ ለሙሴ ተገልጾ የሕዝቤን ጩኸት ሰምቻለሁና ሂደህ ፈርዖንን ሕዝቤን ልቀቅ በለው አለው፡፡ ሙሴም ምን ምልክት አለኝ አለው፡፡

፩ኛ. በትርህን ከመሬት ጣላት አለው ቢጥላት እባብ ሁናለች፡፡ ፈርቶ ሸሸ፡፡ ጅራቷን ይዘህ አንሳት አለው፡፡ ቢያነሳት ደህና ሁናለች፡፡

፪ኛ. እጅህን ከብብትህ አግብተህ አውጣው አለው፡፡ አግብቶ ቢያወጣው ለምጽ ሆነ፡፡ ደግመህ አግብተህ አውጣው አለው ደግሞ አግብቶ ቢያወጣው ደህና ሁኗል፡፡

ሙሴም ይህን ነገር ለፈርዖን አሳይቶ እስራኤልን ስደዳቸው ቢለው እምቢ አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ፈርዖን እስራኤልን አለቅም እግዚአብሔርንም አላውቅም በማለቱ ምክንያትና ልቡን በማደንደኑ ፈጣሪ ብዙ መቅሰፍት አወረደ፡፡ በዚያን ጊዜ መቅሰፍት ሲወርድ የእስራኤል ሕዝብ በሚኖርበት በጌሤም መቅሰፍት አልነበረም፡፡ ሙሴን አሮንን ጸልዩልን እያሉ መቅሰፍቱ ይቆም ነበር፡፡ ሙሴም እጁን ወደ እግዚአብሔር ዘርግቶ በመጸለይ ያማልድ ነበር፡፡ ሎቱ ስብሐት ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ ዘፀ. ፱፡- ፩ ፥ ፰፡-፪

በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ፦ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳላሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ ዘፀ. ፳፫፥፳፡፳፪

እግዚአብሔር አምላክ ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ እያለ በተደጋጋሚ ፈርዖንን በሙሴ አማካኝነት ቢያዘው ፈርዖን እምቢ በማለቱ ምክንያት ከፈጣሪ የታዘዙ መቅሰፍታት እኒህ ናቸው፡፡

1ኛ. ጓጉንቸር 2ኛ. ቅማል 3ኛ. የዝንብ መንጋ 4ኛ. ቸነፈር 5ኛ. ቁስል 6ኛ. ሻኝህ 7ኛ. በረዶ 8ኛ. አንበጣ 9ኛ. ሰው የሚዳስሰው ጽኑ ጨለማ 10ኛ. ሞተ በኲር 11ኛ. ስጥመት ናቸው፡፡

ወፈነወ መልአኮ ወአድኀኖሙ/ መልአኩን ልኮ አዳናቸው

ከዚህ በኋላ ፈርዖን እስራኤልን ወደሀገራቸው ሰደዳቸው፡፡ እሱም ከዋለበት ቢመጣ ከተማይቱ ጭልል ብላ አገኛት፡ ፈርዖንም ለካስ ከተማይቱን ያስከበሯት እስራኤሎች ናቸው ብሎ እነሱን ለመመለስ አንድ የወይራ ፍልጥ የሚበላ ፈረስ ነበረው፡፡ ሠራዊቶቹንና እያኔስን እያንበሬስን ባሬስን አስከትሎ እሱ በፈረስ ሆኖ ገስግሶ ከእስራኤል ደረሰባቸው፡፡ እስራኤልም ከባሕረ ኤርትራ ደርሰው ባሕረ ኤርትራ ሞልታ ነበርና ሙሴ በበትሩ ቢመታት እንደ ግድግዳ ወደታች ወደ ላይ ከሦስት ተከፍላ አሳልፋቸዋለች፡፡ ያን ጊዜ እስራኤልን ቅዱስ ሚካኤል እየመራ አሻገራቸው፡፡ ፈርዖንም እነሱን አይቶ እሻገራለሁ ብሎ ባሕረ ኤርትራ ገብቶ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ ቁጣውን ቢያሳየው ከነፈረሱና ከነሰራዊቱ ሰጥሞ ቀርቷል፡፡ እስራኤልም ሰባት ደመና ታዞላቸው አንዱ በፊት፤ አንዱ በኋላ፤ አንዱ በቀኝ፤ አንዱ በግራ፤ አንዱ ለእግራቸው ምንጣፍ፤ አንዱ ከላይ ለእራሳው ጥላ ከለላ፤ አንዱ መንገድ ጠራጊ ሆኖ እየመራቸው ከስደት ወደ ምድረ ርስት ተመልሰዋል፡፡ የእስራኤልም ልጆች በግብጽ የኖሩበት ዘመን ዐራት መቶ ሰላሣ ዓመት ነው፡፡ ዘፀ. 12፡-40

ይህ ሁሉ የሆነው ከፈጣሪያችን ታዞ በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና ረዳትነት ሕዝበ እስራኤል/እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበትን በማሰብ ስለሆነ እኛን እስራኤል ዘነፍስንም ከሲኦል፤ ከገሃነም እንዲያወጣን፤ በነፍስ በሥጋ እንዲታደገን፤ከፈጣሪያችን እንዲያማልደን በእየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል የምናከብርበት ምክንያት ይህ ነው፡፡

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

❖❖❖ በአክሱም ላይ ጥቃት፤ ኅዳር ፲፥ ፲፩ /፳፻፲፫ ዓ.ም ኖቬምበር 19-20 /2020❖❖❖

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2021

እልቂቱ የከተማዋን ነዋሪዎች ቀሰቀሳቸው። አንድ ሰው ከቤት ወደ ቤት በተረገው ግድያ ልጆቹን ያጣውን ዘመዱን ጎብኝቶት ነበር። – “ልጆቿን ገድለው ከወጡ በኋላ መጀመሪያ ላይ ማንም ሰው እንዳይገባ የግቢውን በር ቀርቅረው ዘጉት። ከሁለት የሞቱት ልጆቿ አካላት ጋር ለአንድ ቀን ተኩል ያህል ለብቻዋ ቀርታ ነበር። እሷን ባየናት ጊዜ ምላሽ የማትሰጥና የደነዘዘች ነበረች።”

ለአንድ ሳምንት ያህል ወታደራዊ ኃይሎቹ ይዘርፉና ይገድሉ ነበር። ለሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዎችተናግረው የነበሩት ሌሎች ነዋሪዎች የኢትዮጵያዊ ሰራዊት ተካፋይ ነበር፤ አብዛኞቹ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲሁ ቆመው ዝርፊያውን እና ግድያውን ይመለከቱ ነበር። አንድ ሰው ይህ ለእኛ ህመም ነበርብሏል። የኢትዮጵያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቧ የቆመ ይመስለን ነበር ነገር ግን የኤርትራዊ ሰራዊት ሲዘርፍና ሲገድል ምንም አላሳሰባቸውም። ዝም አሉ።

❖❖❖Attack on Axum, November 19-20/ 2020❖❖❖

The massacre left the town’s inhabitants reeling. One man visited a relative who lost her children in the house-to-house killings: “They killed her children and locked the compound door behind them, so no one could get in at first. She was left alone with the bodies of her two dead children for a day and a half. She was numb, unresponsive by the time we saw her.”

For about a week, the military forces pillaged. While several residents who spoke to Human Rights Watch saw Ethiopian forces participate, most said the soldiers just stood by and watched. “It was painful,” said one man. “I thought the Ethiopian military stood for Ethiopia and its people… but they did nothing as Eritrean forces looted and killed. They just kept silent.”

Human Rights Watch was unable to determine the number of civilian deaths resulting from the joint Ethiopian-Eritrean offensive on Axum and the ensuing massacre. However, based on interviews with elders, community members collecting identification cards of those killed, and those assisting the retrieval of the dead, Human Rights Watch estimates that over 200 civilians were most likely killed on November 28-29 alone. Human Rights Watch also received a list of 166 names of victims allegedly killed in Axum in November, 21 of which correspond to the names of those killed on November 28 and 29 given by witnesses interviewed.

International humanitarian law, or the laws of war, applicable to the armed conflict in Ethiopia’s Tigrayregion, prohibits deliberate attacks on civilians and attacks that are indiscriminate or cause disproportionate civilian harm. Indiscriminate attacks strike military objectives and civilians or civilian objects without distinction, including those not directed at a specific military target. The laws of war also prohibit all violence against captured combatants and civilians, including murder and torture. Pillage and looting are also prohibited. Individuals who commit serious laws-of-war violations with criminal intent, including as a matter of command responsibility, are liable for war crimes.

Crimes against humanity include murder and other unlawful acts committed as part of a widespread or systematic attack on a civilian population.

The late November attacks were documented by media organizations, as well as by Amnesty International. The Ethiopian Human Rights Commission has also begun investigations. Human Rights Watch provided its findings to Ethiopian and Eritrean government officials on February 18 but received no response. On February 26, the Ethiopian government announced it would thoroughly investigate events in Axum and expressed “readiness to collaborate with international human rights experts.”

While the lack of access to conflict areas has hindered reporting on the conflict, Human Rights Watch and others have reported on other massacres, the indiscriminate shelling of towns, widespread pillaging, including destruction of crops, and the apparent extrajudicial executions by Ethiopian and Eritrean forces, as well as forces from the neighboring Amhara region.

Given the presence of multiple armed forces and groups and the poor track record of the warring parties in investigating grave abuses, the UN Office of the High Commissioner for Human Rights (OHCHR) should conduct an urgent, independent inquiry focused on establishing the facts, collecting forensic and other criminal evidence, and investigating war crimes and possible crimes against humanity in Axum and elsewhere is crucial, Human Rights Watch said.

“Condemnations are not enough to bring justice to the victims of grave abuses committed by both Ethiopian and Eritrean forces in Tigray,” Bader said. “Attention and action by UN member states is needed now to ensure those responsible for these grave abuses are held accountable. So far, reports of these chilling abuses have been met by shameful silence.”

💭 Attack on Axum, November 19-20 / 2020

Axum is in northern Tigray, home to an ancient civilization, and declared a World Heritage Site in 1980 by the United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO). Following the outbreak of armed conflict in Tigray in early November, many residents fled the fighting in western Tigrayby crossing into Sudan or by going east, including to Axum, where they hoped to find a safe haven given the town’s historical and religious significance.

Axum residents were already feeling shortages because of the conflict. Ethiopia’s federal government cut off access to Tigrayat the war’s start and food was in short supply. “Electricity was shut,” one resident said. “We couldn’t grind the grains. People subsisted on crackers. After a week, there was nothing. This affected everyone.”

In mid-November, airstrikes hit an area near Axum’s airport.

On November 19, residents heard the distant sounds of artillery getting closer from the direction of Sheree, a town 40 kilometers west that Ethiopian federal forces had captured two days before. Several residents then saw Tigray special forces and militia withdraw from the town. “People were scared because of the terror in Sheree,” said a man who fled to Axum. “No one opened their shops or the market.”

At about 4 p.m., Ethiopian and Eritrean forces fired artillery into Axum that struck buildings, hit the town’s cobblestoned streets, and killed and injured civilians. Panicked residents sought cover from the shelling, some hiding in their homes, others fleeing to rural areas, following a pattern of attacks already documented by Human Rights Watch during the conflict.

Artillery hit the wall of a house in Kebele 02, killing four civilians inside. One young man said: “We were scared, this was our first experience with war. We didn’t know what they were targeting. A heavy weapon hit a home. The blast scattered the bodies of Kassa Enquay, Almaz Zeraya, Ammanuel Berhe, and a young woman who worked as a housekeeper.”

The shelling continued until evening. Residents then heard gunfire.

Source

____________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: