The United Nations says the Ethiopian government promises to ease its de facto blockade on the northern territory of Tigray, where hundreds of thousands are facing famine after a year of conflict.
👉 Courtesy: PBS
💥 It′s Too Late, It’s Too Late. The Damage is Done | በጣም ዘግይቷል ፣ ዘግይቷል ። ጉዳቱ ተፈጽሟል!💥
የሕዝበ ክርስቲያኑን/ የጥንታውያኑን ክርስቲያኖች ቁጥር ይቀንስላቸው ዘንድ ሥልጣን ላይ አውጥተው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የሚደግፉትን አረመኔውን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊን ለማዳን ሉሲፈራውያኑ እንቅልፍ አጥተዋል። መንፈሳዊውን ውጊያ አልቻሉትም! ከእግዚአብሔር ጋር፤ ከጽዮንና ቅዱሳኑ ጋር የሚያካሂዱትን ፍልሚያ እንደማያሸንፉት አውቀውታል፤ የጽላተ ሙሴንን ኃይል በመፈታተን ለአንድ ዓመት ያህል፤ “እስኪ እንየው!” በሚል ድፍረት የተሞላበት “የአምላካዊነት” ሤራቸው ሙቀቱን ሲለኩ ቆይተዋል። በትግራይ ከባድ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተሠራ ገና ከጅምሩ አይተውታል። ሆኖም እየተሠራ ያለው ግፍና ወንጀል ብዙም አያሳስባቸውም፤ እንዲያውም በአንደኛው የዓለም ጦርነት ሲካሄድ የነበረውን ዓይነት ውጊያ ዛሬ በኢትዮጵያ በቀጥታ የሳተላይት ቴሌቪዥናቸው/ ‘Reality TV Show’ ማየቱ ሱስ ሆኖባቸዋል፣ ልክ በጌታችን ስቅለት ወቅት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ደሙን ሲያፈሱበት ይደሰቱት እንደነበረው ሉሲፈራውያኑም ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈው ደማቸውን ሲያፈሱ እስኪሰክሩ ድረስ ነው እየተደሰቱ ያሉት፣ አባቶቼና እኅቶቼ፣ ወንድሞቼና እኅቶቼ ከእነ ልጆቻቸው በረሃብ ሲሰቃዩ ማየት ለእነርሱ ከምናስበው በላይ ሰይጣናዊ እርካታን ነው የሚሰጣቸው። እነዚህ አረመኔዎች በወኪላቸው ግራኝ አብዮት አህመድ በኩል በደንብ በተጠና መልክ ያዘጋጁትን ይህን የዘር ማጥፋት ጦርነት ማቆም አይፈልጉም፤ እንዲቆም አይፈልጉም። እግዚአብሔር ግን ይበቀላቸዋል። በእነዚህ ቀናት ሰሜናውያኑ ኤዶማውያን (ምዕራባውያን እና ምስራቃውያን) በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ አማካኝነት ከመካከለኛው ምስራቅ ባመጧቸውና በቤሎሩሲያ እና ፖላንድ ድምብር አካባቢ ባሰፈሯቸው ስደተኞች ጋር በተያያዘ ሠራዊቶቻቸውን በመጥራት ላይ እና የኑክሌር መሣሪያዎቻቸውንም በማንቀሳቀስ ላይ ናቸው።
ይህች ዲያብሎስ የነገሰባት ዓለም፤ ”ኢትዮጵያውያን ነን” የሚሉትን ከሃዲዎች ጨምሮ በትግራይ ስለተሠራው እጅግ በጣም ከባድ ወንጀልና ግፍ መስማት፣ ማየትና ማወቅ አትሻም፤ የትክክለኛዋ ኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ግን እያንዳንዷን ነገር በቪዲዮው ቀርጾታል። አሁን የፍርድ ቀን ተቃርቧልና ጉዳዩ በጨካኞቹ የሉሲፈራውያኑ ጭፍሮች እና በእግዚአብሔር መካከል ብቻ ነው!
✞✞✞[፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፬፡፲፭፥፲፱]✞✞✞
“ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር። ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው? ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።”
_______________