👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ ♰ መድኃኔ ዓለም
✞✞✞💭👉🔥 በቤተክርስቲያኗ የመድኃኔ ዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዕለት፤ ማክሰኞ ታህሣሥ ፳፯/ ፪ሺ፲፫ ዓ.ም የሰማዕትነት አክሊልን የተቀዳጁት ፴/30 የጉዕተሎ መድኃኔ ዓለም ልጆችን ነፍስ በቅዱሳኑ እቅፍ ያኑርልን ከማህበረ ፃድቃን ይደምርልን። ✞✞✞
ከአንድ ሰዓት በፊት መልክአ መድኃኔ ዓለምን ለማንበበ በረንዳ ላይ ልክ ወጣ ስል አንዲት እርግብ ፀሐይዋን ሸፍና ከበላዬ ላይ ቀርባ በረረች። ከአምስት ሰከንድ በኋላ ያልነበረ ነፋስ “ዥውው!” ብሎ ሲያልፍና ፀጉሬንም ሲያራግበው በጣም የተለየ ስሜት ተሰማኝ። እኔን ለማሳመን መሰለኝ፤ እርግቧ ተመልሳ እንደዚሁ ባቅራቢየ በረረች አሁንም ነፋሱ ወዲያና ወዲህ ሲል ተገነዘብኩት። “የመድኃኔ ዓለም ሥራ ድንቅ ነው” ብዬ የሚከተሉትን የመልክአ መድኃኔ አለም ኃይለኛ ቃላትን አንበበኩ፤
“ለ ዕርገትክ መድኃኔ ዓለም ሆይ፤ በዓውሎ ነፋስና በእሳት ነበልባል አምሳል መንፈስ ቅዱስን ትልክልን ዘንድ በነጐድጓድና በመባርቅት የሠረገላ ዘባን ለተከናወነ ዕርገትህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤ ቅድመ ዓለም የነበርክ ዛሬም ያለህ ለዘለዓለሙም ጸንትህ የምትኖር አምላክ ስትሆን የታሠሩ አገልጋዮችሁን አንተ ታሥረህ ፈታሃቸው በሞትህም የሞቱትን ወገኖችህን አስነሣሃቸው።
ለኅጡእ ምግባ መድኃኔ ዓለም ሆይ፤ ሃይማኖት ስንኳ ቢኖረኝ በጎ ምግባር የሌለኝ አነስተኛው አገልጋይ ማደሪያ ቤቴ መኖሪያ ቦታዬ ከቅዱሳኖችህ ጋር ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን አቤቱ!
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤ ከከንቱ ሞት አድነኝ። ሁሉ ከንቱ ነው። የዚህ ዓለም ንብረት የከንቱ ከንቱ ነው። ሁሉም ኃላፊ ጠፊ ነውና።
ስብሐት ለከ፤ አቤቱ በፍጥረቱ ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል። አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ የምትሆናቸው ላእንተ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።”
♰♰♰ በእውነት ድንቅ ድንቅ ድንቅ ነው!♰♰♰
እውነት ነው፤ አቤቱ ፈጣሪያችን ጸጋህን በምታድልበት መንፈስ ወገኖችሁን ጽዮናውያንን ደስ አሰኛቸው፤ የከበደውን የጨነቀውን ነገር የምታቃልል አንተ ነህ የተቸገረውን፣ የተጎሳቀለውንና የተበደለውን ሁሉ የምትረዳ አንተ ነህ፤ የሕዋርያት ጌጣቸው የነዳያን ገንዘባቸው ተስፋ ላጡ ሰዎች ተስፋቸው፣ አለኝታቸው አንተ ነህ፤ ሙታንንም የምታስነሣቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ ለአብ ኃይሉ ጥበቡ የምትሆን አንተን እናመሰግናለን። ዛሬም መቼም መች ለዘላለሙ አሜን።
👉 የ ፴/30ውን ሰማዕታት ስም እየጠራን ለመድኃኔ ዓለም “እልልል!” 😊😊😊 እንበል!!! ይብላን ለገዳዮቻቸው!👹 ወዮላቸው!
❤️ የሰማዕታቱ የስም ዝርዝር፦
ስም | ጾታ | ማዕረግ | |
1 | ቄስ ገብረ ዮሐንስ ደስታ | ወንድ | የቤተክርስቲያን ሊቅ |
2 | ቄስ ነጋ ተስፋይ | ወንድ | |
3 | መሪጌታ ኪዳነ ማርያም ተፈሪ | ወንድ | የቤተክርስቲያን ዋና ሊቅ |
4 | ቄስ ሐዱሽ ኃይለ ማርያም | ወንድ | ቄስ ገበዝ የቤተክርስቲያን ሊቅ |
5 | ቄስ ገብሬ አጽበሐ | ወንድ | የቤተክርስቲያን ሊቅ |
6. | ሀጎስ ሃይሉ | ወንድ | |
7 | ኪዳኔ ተክለ ሐይማኖት | ወንድ | |
8 | ብርሃኔ ገብረ አረጋዊ (አንገታቸው ተቀልቷል) | ወንድ | |
9 | ግርማይ ንጉሤ (ከልጃቸው ሚኪያስ ጋር) | ወንድ | |
10 | ሚኪያስ ግርማይ ንጉሤ (ከአባታቸው ግርማይ ጋር) | ወንድ | |
11 | ዲያቆን በርሔ ደስታ ወልደ ገብርኤል | ወንድ | |
12 | ዲያቆን ብርሃኔ ገብረ ሥላሴ | ወንድ | |
13 | ዲያቆን ጽጋብ አለም ፊትዊ | ወንድ | |
14 | ደሳለኝ ተስፉ ሀጎስ | ወንድ | |
15 | አታክልቲ መሰለ ገብረ ዮሐንስ | ወንድ | |
16 | ሴት መነኩሴ እታይ ዘ–ሀፍታ | ሴት | |
17 | ምሕረት ገብረ እግዚ | ሴት | |
18 | ሀደጋ ለማ | ሴት | |
19 | ካሕሳ ገብሬ | ሴት | |
20 | ኪዳን ወልዱ | ሴት | |
21 | ኪዳን ረዳ | ሴት | |
22 | ለታይ ገብረ ማርያም (ከሴት ልጃቸው ብርሃን ጋር) | ሴት | |
23 | ብርሃን ገብረ ጻድቅ (ከእናታቸው ለታይ ጋር) | ሴት | |
24 | በኩረ ጽዮን ደስታ | ወንድ | |
25 | ደስታሰላም ግርማይ | ወንድ | |
26 | ብርሃኔ ገብረ ኢየሱስ | ወንድ | |
27 | መሪ ጌታ ደሳለኝ ካህሳይ | ወንድ | የቤተክርስቲያን ሊቅ |
28 | አብረኸት እቁባዝጊ | Female | |
29 | ተስፋይ ገብረ ሥላሴ | ወንድ | |
30 | አንገሶም ገብረ ሥላሴ ታደሰ | ወንድ |
____________________