Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2021
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    2930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የራያ ጨፋሪዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ | ቤተክርስቲያንን የባህል ጎዳና የማድረግ ሤራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 2, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

❖❖❖[ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፪]❖❖❖

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”

ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ማርያም በደሴ፣ ቅዱስ ኡራኤል በኮምቦልቻ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አቡነ ተክለ ኃይማኖት በሸዋ አዲስ አበባ እንዲሁም በደቡባዊቷ ኢትዮጵያ መድኃኔ ዓለምን ለማንገስ ጽዮናውያኑን አጅበዋቸው ከሉሲፈራውያኑ የጨለማው ዓለም ገዢዎች ከዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ ጋር በመጋደል ላይ ናቸው። ዓመና ላይ በትግራይ ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱ የተቀሰቀሰባቸውን እነዚህን ቀናት በደንብ እናስታውሳቸው!✞

👉 ለመሆኑ በጽዮናውያን ላይ የተነሳችሁ የተዋሕዶ ልጆች ነንየምትሉ ሁሉ የጽዮን እናታችንን እና የጽላተ ሙሴን ኃያልነት አታምኑበትምን?

ቪዲዮው ላይ የሚታየው ክስተት፤ ባራክ ሁሴን ኦባማ፣ ሸህ መሀመድ አላሙዲን (በግራኝ አብዮት አህመድ በኩል) ፣ የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ተናብበው፤ ነፍሳቸውን ይምራላቸውና፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ከገደሏቸውና በኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኩል ደቡባውያኑን ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ካነገሷቸው በኋላ በአዲስ አበባ በግልጽ መታየት ጀምሮ ነበር። የኃይለ ማርያም ደሳለኝ አገዛዝ ወላይታዎችን ከገጠር በብዛት ወደ አዲስ አበባ በማስገባት የጫማ ጠራጊነት በመሳሰሉት ቀደም ሲል ጉራጌዎች ተቆጣጥረዋቸው በነበኡት ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ሲያደርግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በተጋሩ ላይ “የማዋረድ አጀንዳ” የተከተሉ ስለመሰላቸው ትግርኛ ተናጋሪ የኔ ቢጤዎችን እንዲሁም የራያ ባሕላዊ ጨፋሪዎችን (ቪዲዮው ላይ በአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደሚታየው) እንደዚሁ በብዛት ወደ አዲስ አበባ አስገብቷቸዋል። ይህ ክስተት/ሤራ ከ፳፻፲፪ ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሰፊው ይከሰት ነበር፤ በተለይ ከውጭ አገር ወደ አዲስ አበባ የገባ ታዛቢ በደንብ የሚመለከተው ነበር።

በጽዮናውያን የተዋሕዶ ልጆች እና ቤተ ክርስቲያናቸው ላይ ያነጣጠረው ጦርነት ከሁሉም አቅጣጫ እየተጧጧፈ መምጣቱን በዚህ ዓንድ ዓመት ውስጥ በግልጽ ለማየት በቅተናል። አባቶቻችንን በየገዳማቱ ማጥቃትና መግደል የመጨረሻው ዒላማቸው መሆኑን አስቀድመን ጠቁመን ነበር። መጀመሪያ ግን ክርስቲያናዊ ሕይወትን በየመንገዱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በጉርብትና በመቅረብ ብሎም ወደ ቤተክርስቲያን በመጠጋት ነበር ሲዋጉ የነበሩት።

ለምሳሌ ከ ራያ ያመጧቸውን የባህል ጨፋሪዎች (ድሮም ወደ አክሱምና ላሊበላ አካባቢ አምጥተው እዚያ እንዲሰፍሩ መደረጋቸው የጣዖቱን ዋቄዮ አምልኮት ያስፋፉ ዘንድ እባባዊ በሆነ መልክ በማቀድ ነበር፤ ሰይጣን ከቤተ ክርስቲያን አይርቅም) በየአብያተክርስቲያናቱ እንዲገቡ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለማበላሸትና እምነታችንንም ወደ ባሕላዊ ሥርዓት ለመለወጥ እየሞከሩ ነው። ቪዲዮው ላይ ምዕመናኑ እንዴት እንደሚመለከቷቸው ልብ እንበል።

በነገራችን ላይ፡ እንደ “መስቀል” እና “ጥምቀት” የመሳሰሉትን ክብረ በዓላት የየተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፤ በምህጻሩ UNESCO በሚባለው ድርጅት እውቅናን እንዲያገኝ መደረጉ መንፈሳዊ የሆነችውን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ወደ ዓለማዊው የባህል፣ ወግና ልምድ ሥርዓት ይለወጥ ዘንድ የተጠነሰሰ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው።

ቤተክህነትም ሆነች ምዕመናን ክርስቲያናዊ በዓላታቸውን በአውሬው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ዕውቅና እንዲያገኙ ከመታገል መቆጠብ ይኖርባቸዋል፤ አሊያ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።

_________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: