አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፥ ተማመኑ አንተም አዳንሃቸው ✞
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 31, 2021
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
ጽዮናውያን ሆይ፤ ሁሌ እግዚአብሔርን ብቻ እናምልከው፣ ቅዱሳኑን እና ጽዮን ማርያምን እናስታውሳቸው፤ ለድል ያበቁን፣ እያበቁን ያሉትና ለወደፊትም የሚያበቁን እኮ እነርሱ ብቻ ናቸው። ሕዝባችን ከረሃብ፣ ከበሽታ፣ ከስቃይ እና ከዲያብሎስ ባርነት ሙሉ በሙሉ ነፃ ይወጣል፤ የዚህ ድል ባለቤቶች እግዚአብሔር፣ ቅዱሳኑ፣ እናታችን ጽዮን ማርያም እና ጽላተ ሙሴ እንጂ የሰው ልጅ፣ ዲያብሎሳዊው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እና የብሔር ብሔረሰቦች ተረተረት፣ ስጋዊው/ባሕላዊው “ትግራዋይነት”፣ ኃያላን ሃገራት፣ ክልሎች፣ ሕወሓቶች፣ የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበት ባንዲራና የመሀመዳውያኑ ‘ካባ’ ድንጋይ ጥምጣሞች አይደሉም። ይህ በጽዮናውያን ታሪክ አክሱም ኢትዮጵያውያን ለሺህ ጊዜ ሲጎናጸፉት የነበረውን የድል አክሊል ዛሬም በድጋሚ በዓይናችን አይተነዋልና ለዚህ ድል የሚያበቁንን እግዚአብሔር አምላካችንን፣ እናታችን ጽዮን ማርያምንን፣ ቅዱሳኑን እና ጽላተ ሙሴን ለሰከንድ እንኳን ከማመስገድ ልንቆጠብ አይገባንም።
ከሠላሳ ዓመታት በፊት የወያኔን በደርግ ላይ ድል መንሳት እና አዲስ አበባ መግባት አስመልክቶ በጣም ተደንቆ የዘገበው እንግሊዛዊው ጋዜጠኛና ደራሲ ግርሃም ሃንኮክ/ Graham Hancock „The Sign and The Seal“ በተሰኘው መጽሐፉ፤ “ትግራዋያን በረሃብ እየተሰቃዩ ለዚህ ድል የበቁበት ኃይል የተገኘው ሌላ ከየትም ሊሆን አይችልም ከጽላተ ሙሴ ነው።” ብሎ ነበር። የሚገርም ነው፤ ግራሃም ሃንኮክ ከቴምፕላሮች ጋር በተያያዝ ያለሆነ መላምት ይዞ ቢመጣም፤ ይህን በተመለከተ ግን የመንፈሳዊ ደረጃው ከደራሲው ፍሰሐ ያዜ (በሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ፤ እንደተቀሩት የአማራ ልሂቃን “አማራ፣ አማራ” በማለቱ) በእኔ እይታ ትንሽ ከፍ ብሎ ይታያል ።
ገና ብዙ መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚጠብቃቸውና እስከ ሞቃዲሾ እና ካርቱም የሚዘለቁትን እግዚአብሔር ለጽዮናውያኑ ኢትዮጵያውያን የሰጣቸውን የእነ አብረሃ ወጽበሃ ምድር ሁሉ ነፃ በማውጣቱ ረገድ (መለኮታዊ ግዴታቸው ነው! ይህን ካላደረጉ ዲያብሎስ ያሸንፋቸዋልና) የዛሬይቷ መንደረ ትግራይ ጽዮናውያን ወገኖቼ በእግዚአብሔር፣ በቅዱሳኑ፣ በጽዮን ማርያም እና በጽላተ ሙሴ ኃይል ሁሌ እንደሚያሸንፉና ዛሬም በእርሱ እርዳታ ድል እንደሚቀዳጁ ምንም አልጠራጠረም። መከራው እንዳይከፋ ምናልባት ዛሬም ኢ-አማኒ የህዋሓት አባላት ካሉ (ከዚህ ሁሉ ጉድ በኋላ ሊኖሩ አይገባቸውም) ወደ እግዚአብሔር እጃቸውን ዘርግተውና እንደ አደዋው ድል ቅዱሳት ጽላቶቻቸውን ተሸክመው ወደ እያንዳንዷ የዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ መደበቂያ ዋሻ መዝመት ይኖርባቸዋል። በድብቅም ቢሆን ይህን እያደረጉ እንደሆነ የደሴው ዘመቻቸው የሚጠቁመን ነገር አለ። ኢ-ዓማኒው የሩሲያው/ሶቪየት ሕበረት ኮሙኒስት መሪ ጆሴፍ ስታሊን እንኳን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጀርመኖች ወረራ ወቅት አዘግቷቸው የነበሩትን ገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ እና ሰራዊቱም የእምበቴታችን ስዕሎች ተሸክሞ እንዲወጣ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
ጽዮናውያን ስንት መስዋዕት ከፍለው ልክ ደሴና ኮምቦልቻ ሲደርሱ ፥ አምና ሻሸመኔን እና አጣዬን ያጋያቸው የፋሺስቱ ግራኝ ኦሮሞ አገዛዝ ግራ ክንፍ፡ “OLA“ ዛሬ በኬሚሴ ከሃጅ ጂሃድ ቀሚስ ወጥቶ “አለሁ! ኢኔ! ኬኛ” አለን! ዋው!
ደሴ በነገራችን ላይ ከፍተኛ የመንፈሳዊ እና መለኮታዊ ጸጋ የነበራቸው/ያላቸው ታላቁ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ ነበሩ የቆረቆሯት። በቦታው የሆነ ደስ የሚል ነገር ስለታያቸው ነበር ከተማዋን “ደሴ” ብለው የሰየሟት። አሁን “ወሎ፣ ወረኢሉ፣ ወረባቦ ወዘተ” ተብለው በዋቄዮ-አላህ-አቴቴ እርኩስ መንፈስ የተሰየሙት ቦታዎች ሁሉ ሌላ መጠሪያ መያዝ ይኖርባቸዋል። መጠሪያዎቻቸው እካሁንም ድረስ የቆየው፤ በአማራዎች ደካማነትና ስንፍና እንዲሁም ያላግባብ በጋልኛ ቋንቋ እንዲጠሩ የተደረጉትን የቦታዎችን ስም ይለውጡ ዘንድ አፄ ምኒልክ የአፄ ዮሐንስን ምክር ባለመስማታቸው ነው።
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፩]✞✞✞
፩ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ።
፪ አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ፥ አልመለስህልኝም፤ በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም።
፫ በእስራኤል የተመሰገንህ አንተ ግን በቅድስና ትኖራለህ።
፬ አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፥ ተማመኑ አንተም አዳንሃቸው።
፭ ወደ አንተ ጮኹ አመለጡም፥ አንተንም ተማመኑ አላፈሩም።
፮ እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፤ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ።
፯ የሚያዩኝ ሁሉ ይላገዱብኛል፤ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይላሉ።
፰ በእግዚአብሔር ተማመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ቢወድደውስ ያድነው።
፱ አንተ ግን ከሆድ አውጥተኸኛልና፥ በእናቴ ጡት ሳለሁም በአንተ ታመንሁ።
፲ ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ።
፲፩ ጭንቀት ቀርባለችና የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
፲፪ ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤
፲፫ እንደ ነጣቂና እንደሚጮኽ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።
፲፬ እንደ ውኃ ፈሰስሁ፤ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ።
፲፭ ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ።
፲፮ ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።
፲፯ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።
፲፰ ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
፲፱ አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ፤ አንተ ጕልበቴ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
፳ ነፍሴን ከሰይፍ አድናት፥ ብቻነቴንም ከውሾች እጅ።
፳፩ ከአንበሳ አፍ አድነኝ፥ ብቻነቴንም አንድ ቀንድ ካላቸው።
፳፪ ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፥ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።
፳፫ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፥ አመስግኑት፤ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፥ አክብሩት፥ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፥ ፍሩት።
፳፬ የችግረኛን ችግር አልናቀምና፥ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከእኔ አልሰወረምና፥ ነገር ግን ወደ እርሱ በጮኽሁ ጊዜ ሰማኝ።
፳፭ በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው። እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እሰጣለሁ።
፳፮ ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፤ እግዚአብሔርንም የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸውም ለዘላለም ሕያው ይሆናል።
፳፯ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሱ፤ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።
፳፰ መንግሥት ለእግዚአብሔር ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል።
፳፱ የምድር ደንዳኖች ሁሉ ይበላሉ ይሰግዳሉም፤ ወደ መሬት የሚወርዱት ሁሉ በፊቱ ይንበረከካሉ፤ ነፍሴም ስለ እርሱ በሕይወት ትኖራለች።
፴ ዘሬ ይገዛለታል፤ የምትመጣው ትውልድ ለእግዚአብሔር ትነግረዋለች፤
፴፩ ጽድቁንም ለሚወለደው ሕዝብ፥ እግዚአብሔር ያደረገውን ጽድቁን፥ ይነግራሉ።
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፪]✞✞✞
፩ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
፪ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
፫ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
፬ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
፭ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
፮ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፫]✞✞✞
፩ ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።
፪ እርሱ በባሕሮች መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም አጽንቶአታልና።
፫ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?
፬ እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ።
፭ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል።
፮ ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ።
፯ እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።
፰ ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል።
፱ እናንተ መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።
፲ ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የጭፍሮች አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።
______________________
Leave a Reply