Earthquake in Ethiopia 6-7? | የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 17, 2021
✞✞✞[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፮፥፲፰፡፳]✞✞✞
“መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፥ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ። ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች። ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም።”
🔥 4.5 / 4.3 አማካይ መጠን የመሬት መንቀጥቀጥ
ዓርብ፣ ጥቅምት ፭/፳፻፲፬ ዓ.ም(አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ)
እሑድ፣ ጥቅምት ፯/ ፳፻፲፬ ዓ.ም (ሥላሴ)
‘አድዋ’ በተባለው እሳተ ገሞራ አካባቢ
(ሶማሌ + ኦሮሚያ በተሰኙት ፀረ-ኢትዮጵያ ክልሎች)
🔥 6 እስከ 7 ከፍተኛ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ
በመጭው ማክሰኞ ጥቅምት ፱/ ፳፻፲፬ ዓ.ም (ጨርቆስ)
‘አድዋ’ በተባለው እሳተ ገሞራ አካባቢ
(ሶማሌ + ኦሮሚያ በተሰኙት ፀረ-ኢትዮጵያ ክልሎች)
✞ይህ ከአክሱም/አድዋ ጋር የተያያዘ ነው፤✞
በትግራይ በጽዮናውያን ላይ ከተከፈተው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ጋር የተያያዘ ነውን? አዎ! የሚገርም ነው በሶማሊያ እና ኦሮሚያ ህገ–ወጥ ክልሎች መከሰቱ ለዚያውም “አድዋ” የተሰኘው የተኛ እሳተ ገሞራ ነቃ ነቃ በሚልበት አቅራቢያ። ዋው!
በተጨማሪ ከዚሁ ጋር በተያያዘ፤ እርቀት የማይወስነው መለኮታዊ ኃይል በአትላንቲክ ውቂያኖስ አፍሪቃ ጠረፍ በምትገኘውና የስፔይን ግዛት በሆነችው የላስ ፓልማስ ደሴት ኃይለኛ የእሳተ ገሞራን ቀስቅሷል። ይህ በጣም የሚፈራው እሳተ ገሞራ የሚፈጥረው የመሬት መንሸራተትና፣ የሱናሚ ጎርፍ አውሮፓን እና ምስራቅ አሜሪካን አውድሞ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊገድል ይችላል። ይህ ለብዙ ዓመታት ሲጠብቅ የነበረ አስፈሪ ትንቢት ነው። የቱሪስቶች መናኸሪያ ከሆኑት ከካናሪ ደሴቶች መካከል በሆነችው ላስ ፓልማስ ልክ ከወር በፊት እሳተ ገሞራው ፈንድቶ የላቫ ፍሰቱ እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ቀጥሏል። ከደሴቲቷ ሰማኒያ አምስት ሺህ ነዋሪዎች መካከል አሥር ሺህ የሚሆኑት ተፈናቅለዋል። ።
አንዳንድ ታዋቂ ሳይንቲስቶች እርግጠኞች ሆነው እንደሚናገሩት ከዚህች ደሴት የሚቀሰቀሰው ከፍተኛ የእሳተ ገሞራ በሰሜን አሜሪካ ምስራቃዊ ዳርቻ (ኒው ዮርክ) እና የሜዲትራንያን ባሕር አዋሳኝ በሆኑ የአውሮፓ ሃግራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊገድል ይችላል፤ ይህ እስኪሆን ድረስ የጊዜ ጉዳይ ብቻ እንደሆነም ያስጠነቅቃሉ።
____________________________
Leave a Reply