Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2021
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ቆሻሻው ግራኝ አብዮት አህመድ የጨለቖት ሥላሴ ቅርስን መንካት አልነበረበትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 17, 2021

እንግዲህ ይህን ‘ምናልባት ለንግስናው ሊጭነው‘ አቅዶት የነበረውን ዘውድ እንዲመለስ የፈቀደውም ለተንኮል፣ ለዲያብሎሳዊ ዓላማው፣ ምኞቱ እና ስልቱ መሆኑ ግልጽ ነው። አዎ! አታክልቶችን፣ ሰብሉን፣ እህሉን፣ ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን በማውደም ከቦምብና ጥይት ጭፍጨፋ የተረፉትን ጽዮናውያን በስጋ ማዳከም ብቻ ሳይሆን ዓላማው ፥ ዓብያተ ክርስቲያናቱን፣ ገዳማቱንና ቅርሶቿን በትግራይ የቀሩትን ዛፎችን (ልብ እንበል፤ በተለይ ለኮሮና ወረረሽኝ ብቸኛ የመድኃኒት ምንጭ የሆኑትን የእጣን ዛፎችን ሁሉ በማውደም ትግራይን ልክ እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ልክ ‘እንደ በሻሻ‘ የመንፈሳዊ ምድረበዳ የማድረግም ፍላጎትና ሕልምም ስላለው ነው።

በውጭ ሃገር ያሉትን የተዋሕዶ ክርስትና ቅርሶች ሁሉ በማስገባት ማውደም፤ ልክ በሱዳን ስደት ላይ የሚገኙትን ጽዮናውያንን ወደ ትግራይ መልሶ እና ወደ ሱዳን ተሰደድው ለመውጣት የሚሹትን ሁሉ ድንበሩን ዘግቶና አፍኖ ለመጨፍጨፍ እንዳቀደው። ልክ አቡነ መርቆርዮስን ከአሜሪካ አስመጥቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የዋቄዮ–አላህ ባሪያው ኢሬቻ በላይ መፈንጫ እንድትሆን እንዳደረገው።

😈 አረመኔው ግራኝ ከ ጨለቖት ሥላሴ የተዘረፈውን ዘውድ ለምን ለማምጣት ፈለገ? አምባሳደሩስ ለምን ከዱት?

ለማንኛውም ይህ በዛሬው በሥሉስ ቅዱስ ዓርብ ዕለት የምናነበው ተዓምር የግራኝ አብዮት አህመድን እና ጭፍሮቹን ማንነት እና እጣ ፈንታቸውን በከፊል ይገልጥልናል።

ቀደም ሲል ጄነራል ጻድቃን አዲስ አበባ እያሉ ለፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ መሪ ለግራኝ አብዮት አህመድ ትግራይን እንዳይተናኮል እና በሕዝቡም ላይ ጦርነት እንዳይከፍት፣ ሕዝቡን ፈጽሞ ማንበርከክ እንደማይቻል መክረውት እንደነበር ሰምተናል። ግራኝ ግን የመለሰላቸው፤ “በገንዘብ እና በጦር ኃይል የማንበረከክ ሕዝብ የለም!” በማለት ነበር መልስ የሰጣቸው።

ጄነራል ጻድቃን እና ባልደረቦቻቸው አሁን ወደ ማንነታቸው ተመልሰዋል ለሥላሴ ይሰግዳሉ፣ ጽዮን ማርያምን ይማጸናሉ የሚል ተስፋ አለኝ። ከዚህ ሁሉ ዕልቂትና ጥፋት በኋላ ዛሬም ይህን ካላደረጉ ግን የትግራይን ሕዝብ ሊመሩት አይችሉምና እነርሱ ለንስሐ የሚያበቃቸውን ገድል ፈጽመው ከአመራርነት በክብር እንዲሰናበቱ ይደረጋሉ፤ ከዚያም የከንቱ ምድራዊ ርዕዮተ ዓለም ባሪያ ያልሆነና ለሕዝቡ የቆመ ጽዮናዊ የሆነ መሪ ይነሳ ዘንድ ግድ ይሆናል።

አንጐት = ጨለቖት

የተረፈው አስተዋዩ፣ ታማኙ ነጋዴ = በቅድስት ሥላሴ ፍቅር የተጠመደ ጽዮናዊ መሪ

😈 በገንዘብ ፍቅር ተታለው ነፋሱ ጠራርጎ ያጠፋቸው ከሃዲዎቹ ነጋዴዎች = ግራኝ አሊ ባባ እና የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮቹ

❖❖❖የሥላሴ ተአምር❖❖❖

. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው…….ላይ ይደርና

የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተአምራታቸው ይህ ነው።

. አንጐት በሚባል አገር ብዙ ነጋዴዎች ነበሩ።

. እኒህ ነጋዴዎች ኢየሩሳሌም ወርደው በሥላሴ ሥዕል እነሆ እንዲህ ሲሉ ተማፀኑ።

. ከሄድንበት ሀገር ከጥልቅ ባሕር መሰጠምና መርዘኛ ከሆነው ከአዞ መበላት ወይም መነከስ ድነን

በሰላም ወደ ቤታችን ብንመለስ።

. እነሆ ከአተረፍነው ትርፍ ወርቅና ብሩን ግማሽ በግማሽ ለሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንሰጣለን ተባባሉ።

. ይህንም ካሉ በኋላ ለንግድ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ወረዱ።

. ወደ መርከብ በገቡ ጊዜ የባሕሩ ማዕበል ፀጥ አለላቸውና የሰላም ጉዞ ሆኖላቸው ተጓዙ።

. በዚህ ጊዜ ከሀገሩ ሰዎች አንዱ እንዲህ አላቸው።

. ይህ ጥልቅ ባሕር ሳያሰጥማችሁ እንደምን ተሻገራችሁ ሰውን የሚውጠው አዞስ እንዴት ሳያገኛችሁ ቀረ አላቸው።እኒህ ነጋዴዎችም በእምነታችን መሠረት በብዙ ወርቅ የሥላሴን መርከብ ተከራየን (ለሥላሴ ብፅዓት አደረግን)

፲፩. ወደ ሀገራችንም በሰላምና በደህንነት ብንመለስ ከገንዘባችን ሁሉ እኩሌታውን ለሥላሴ ቤተ ክርስቲያን

ብፅዓት አድርገን እንሰጣለን ብለናል አሉት።

፲፪. ከጥቂት ቀን በኋላም እኒህ ነጋዴዎች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተነሡ ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ ነጋዴ

ወንድሞቼ ሆይ ባሕሩን ተሻግረን እዚህ ለመድረስ አስቀድመን የተናገርነውን አንርሳ በማናውቀውም ሀገር

ብዙ ወርቅና ብር አትርፈናልና ብፅዓታችንን ወይም ስእለታችንን እንዳንተው ሲል አሳሰባቸው።

፲፫. አሁንም ወንድምቼ ሆይ በእውነት የምነግራችሁን ስሙኝ እንደ ሥእለታችን ከገንዘባችን ካልሰጠን

ዳግመኛ ለንግድ በምንሄድበት ጊዜ እሊህ ሦስቱ ሥላሴ ገንዘባችንን ሁሉ ያጠፉብናል አላቸው።

፲፬. እነሱ ግን እኛ አንድ ብር እንኳ አንሰጥም አንተ ግን ከፈለግህ ስጥ ለራስህም አንተ ራስህ እወቅ።

፲፭. እኛስ ነገርህን አንሰማም እንደ አንተ ያለም መካሪ አንሻም በሥላሴ ስም ከቶ አልተማፀንምና አሉት።

፲፮. ይህም ነጋዴ ወንድሞቼ ሆይ የተናገራችሁትን ቃል እንዴት ታጥፋላችሁ ወይም እኮ ሰይጣን

ኃላፊና ጠፊ በሚሆን በገንዘብ ፍቅር አታለላችሁ ይሆን አላቸው።

፲፯. ይህ በቅድስት ሥላሴ ፍቅር የተጠመደ ነጋዴም ይህን ተናግሮ ዝም አለ።

፲፰. ከዚህ በኋላ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በመርከብ ተሳፈሩ።

፲፱. በዚህ ጊዜ ከነፋሱ ኃይል የተነሣ መርከቡ ተነዋወጠ ሊያሰጥማቸውም ተቃረበ።

. በዚህ ጊዜ መርከቡ ተሠበረና ሰዎቹ በባሕር ውስጥ ሰጠሙ።

፳፩. ይህን ታማኝ ነጋዴ ግን ሥላሴ ከባሕር አውጥተው በባሕር ዳርቻ አስቀመጡት።

፳፪. ከጣፈጠ አነጋገርህ የተነሣ ታማኝ አገልጋይ አደረግንህ አሉት።

፳፫. እንግዲህ የአንተን ገንዘብ አንፈልግም እምነትህ ይበቃናል።

፳፬. እነዚህ ከሐዲዎች ጓደኞችህ ግን በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንደሰጠሙ ተመልከት አስተውል አሉት።

፳፭. እንግዲህ አንተ ወደ ምድረ አንጐት ውረድና የሆነውን ነገር ሁሉ ለዘመዶቻቸውና ለቤተ ሰባቸው ሁሉ

ንገር አሉት።

፳፮. ነጋዴውም እናንት የሀገር ታላላቅ አባቶች ሆይ እናንተ እነማን ናችሁ ስማችሁስ ማን ይባላል አላቸው።

፳፯. እነሱም እኛ ዓለሙን ሁሉ የፈጠርን ሥላሴ እንባላለን አሉት።

፳፰. ይህንንም ቃል ከአብና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ አንደበት በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው።

፳፱. የደረሰበትን ነገር ሁሉ ነጋዴዎቹም በከንቱ እንደጠፉና እሱ ግን ሥላሴን በማመን እንደዳነ ለአንጐት ሰዎች

ነገራቸው።

. ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ ስለ ነጋዴዎቹ የተደረገው ነገር ሁሉ እጅግ አስደናቂ ነው በማለት አደነቁ።

፴፩. በዚህ ጊዜ ይህ ነጋዴ ብሩንና ወርቁን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በሥላሴ ስም መፀወተ።

፴፪. ኃላፊና ጠፊ ከሚሆን ከዚህ ዓለም ድካም እስከ ዐረፈ ድረስ በየወሩ በ፯ ቀን ይልቁንም በጥርና በሐምሌ ወር

የበዓላቸውን መታሰቢያ አብዝቶ ያደርግ ጀመር።

፴፫. ይቅርታቸውና ሀብተገ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው ከ…….ጋር ለዘለዓለሙ ይኑር አሜን።

💭 ቅዳሜ / ጥቅምት ፰/8 ፪ሺ፲፪ / 2012 ዓ.ም ላይ እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በትግራይ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ሊጀምር ፩ ዓመት ሲቀረው የጨለቖት ቅድስት ሥላሴ ዘውድ ወደ ትግራይ እንዲመለስ ፈቀደ። እዚያ ክቡር ዘውድ ላይ እጁ ሲያርፍ ሳየው እጅግ በጣም ነበር ያንቀጠቀጠኝና ያስቆጣኝ!

👉 ያኔ የወጣው መረጃ የሚከተለው ነበር፤

/20 ዓመታት በላይ በኔዘርላንድ የቆየው የዘውድ ቅርስ ትግራይ ክልል ለሚገኘው የጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተመለሰ

ከመቐለ ፲፮/16 ኪሎ ሜትር በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኘውና ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረው የሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በርካታ ንዋየ ቅድሳት እንዳሉ ይነገራል። በተለይም ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስትያኑ እልፍ ንዋየ ቅዱሳን ማበርከታቸውን ቤተ ክርስትያኑ ግቢ ውስጥ ለዓመታት የኖሩ አባቶች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ፹፪/82 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ፤ ሦስት ዘውዶችን ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስቲያኗ መስጠታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ፲፯፻፵፭–፲፰፻፷፭/1745-1865 በወቅቱ የእንደርታ ዙሪያ የሚባለውን ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩት ራስ ወልደሥላሴ በአራት ቦታዎች ማለትም በጨለቆት፣ በሕንጣሎ፣ በፈለግዳዕሮና በመቐለ ቤተ መንግሥቶችን ገንብተው ነበር። በአንድ ወቅትም ጨለቆትን ዋና ከተማቸው አድርገዋታል።

ራስ ወልደሥላሴ ካበረከቷቸው ዘውዶች መካከል አሁን በኔዘርላንድ የተገኘው ዘውድ አንዱ ሲሆን፤ ከ፳/24 ዓመታት በፊት መሰረቁንና ከዚያም መሰወሩን ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የተወሰደው ዘውድ ኔዘርላንድ ውስጥ መገኘቱንና በዛሬው ዕለት ወደ አገሩ መመለሱን ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሳውቀዋል።

ይህ ዘውድ ንብረትነቱ የጨለቆት ሥላሴ መሆኑ የማያጠራጥር በመሆኑ ወደቦታው ተወስዶ በክብር ሊቀመጥ ይገባዋል።”

💭 በቪዲዮው፤

👉 ማክሰኞ/ የካቲት ፳፬/24 ፪ሺ፲፪ / 2012 .

የዘውዱ ሥርዓት አቀባበል በትግራይ

👉 ነሐሴ ፪ሺ፲፫ / 2013 .

በኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሚሊዮን ሳሙኤል አረመኔውን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ።

👉 በዚሁ ወር ላይ ከሃዲዋ ኦሮሞ ሲልፋን ሃሳን ለኔዘርላንዶች ሦስት ሜዳሊያ ሠረቀችላቸው።

💭 ቀደም ሲል የቀረበ፤

❖❖❖ ጨለቖት ሥላሴ ❖❖❖

😈 በአውሬው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የሚመራው የኦሮማራ አህዛብ ሠአራዊት ለዝርፊያ ከተሰማራባቸው ታሪካዊ ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት አንዱ የደብረ ምሕረት ጨለቖት (ሀገረ ማርያም)ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ነው። ወረድ ብለን እንደምናነበው በረከታቸው ይደርብንና የሃገር ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ከማረፋቸው በፊት በቦታው ላይ ያሉትን በርካታ የታሪክ ቅርሶች የዝመነ መሳፍንት ታሪክና ቅርስ ዝክር እና በዚያ ዘመን ቤተ ክርስቲያን የነበራትን ሕይወት ማስታዋሻ የሆኑ ሐብቶች መጠበቂያ የሚሆን ቤተ መዘክር የማሠራት እቅድ እንደነበራቸውና ይኽውም ከፍተኛ ድጋፍና ማበረታቻ እነሚያስፈልግ ገልጸው በአካል ተለይተውናል። ዛሬ ይዞታው ምን ላይ ይሆን? ታሪካዊ ቅርሶቹስ? የኦሮሞራ ቃኤላውያኑ እነዚህን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ቅርሶች ለመዝረፍ የብዙ ዓመታትና ዘመናት ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ዛሬ በፍሬዎቻቸው አውቀናቸዋል፤ ለዚህ የዘረፋ ተግባር ከኤዶማውያኑ የተማሩትን ስልት እና ጥበብ ተጠቅመዋል፤ የትግርኛን ቋንቋ ማጥናት ችለዋል። ከግራኝ እስከ ጉማሬው ብርሃኑ ነጋ ለፖለቲካው ድራማም ለሌብነቱና ለጭፍጨፋው ያመቻቸው ዘንድ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ስነ ልቦና፣ ባሕል፣ ህልም ብሎም የትግርኛን ቋንቋ ሳይቀር በሚገባ አጥንተዋል።

_______________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: