Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2021
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ቅዱስ እስጢፋኖስ | በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የመስቀሉ ልጆች የዋቄዮ-አላህ አጋንንትን በቅርቡ ያቃጥሏቸዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2021

✞✞✞መስቀል ኃይላችን ነው!✞✞✞

♰♰♰

No Pain, No Gain; No CROSS No CROWN

ያለህመም ማግኘት የለም ፥ ያለ መስቀል ፣ አክሊል የለም

ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፱ ዓ/ም ተመሠረተ። በዚያን ጊዜም ዘመኑ በፈቀድው መልክ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ተጠናቆ ሲወደስበት ሳለ፤ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ ደርሶበት ሕንጻው ተቃጠለ።

ኢትዮጵያ ከ ፋሺስት የወረራ ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ፤ የግንባታው ሥራ በሥራ ሚኒስቴር ኃላፊነት በዘመናዊ መልክ እንዲሠራ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሚኒስትሩ ባላምባራስ (በኋላ ብላቴን ጌታ) ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በአንድ በኩል የአካባቢውም ኗሪ እና የቤተ ክርስቲያኑ ምእመን በመሆናቸው እና በሚኒስቴራዊ ኃላፊነታችው፤ ሥራውን በቅርብ እየተከታተሉና እየተቆጣጠሩ አሠርተውት የአሁኑ ሕንጻ ግንባታ ፍጻሜ አግኝቶ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ የግብጽ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በተገኙበት ተባረከ።

የቀዳሚ ሰማእት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት ነበር | የጽዮናውያንም እንዲሁ

እስጢፋኖስ — በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው። በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው።

ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀዳጃቸው ሦስቱ አክሊላት፡

. ስለንፅህናው ስለድንግልናው

. ስለሰማዕትነቱ /ስለምስክሩ/ ስለተጋድሎው

. ስለስብከቱ /ስለትምህርቱ/ ስለተአምራቱ

ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ታንፆበታል። /ሰባት ቤተክርስቲያናትን አንጿል።/

የቤተክርስቲያን አባቶች የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራውን እንድናይበት አድርጎናል ሲሉ ይገልፁታል እውነት ነውና።

_________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: