ህመም የለም ፣ መዳፍ የለም ፥ መስቀል የለም፣ አክሊል የለም
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2021
♰♰♰
ህመም የለም ፣ መዳፍ የለም ፥ እሾህ የለም ፣ ዙፋን የለም። ሐሞት የለም ፣ ክብር የለም ፥ መስቀል የለም፣ አክሊል የለም።
በመስቀል ላይ ሣለ የገሃነመ እሳትን ጠባቂ ጭፍሮች ያስደነገጣቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!
በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን የጸብ ግርግዳ አፍርሶ በመስቀሉ ሠሌዳ ላይ በደሙ ቀለምነት የሕይወታችንን መጽሐፍ የጻፈልን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መስቀሉ፣ ጦሩ፣ ስሙ ጋሻችን ሆኖልና ድነነናል።
💭 በአቅራቢያዬ የምትገኘውን ውብ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ዛሬ ስጎበኛት ይህን በአክሊል ቅርጽ ተሠርቶ የቆመውን መብራት አብሬ ለማየት ቻልኩ። ከእኅታችን የመስቀል ወረብ ጋር በእውነት ድንቅ ድንቅ ነው!
አቤቱ በዘመኑ ሁሉ የጥፋትና የኃጢአት አውሬ (ዲያብሎስ) እንዳይቀርበን በሐጹረ ቅዱስ መስቀልህ አጥርነት ጠብቀን፤ አሜን!
✞✞✞መስቀል ኃይላችን ነው!✞✞✞
______________________________
Leave a Reply