Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2021
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

በ፪ሺ፲፪ቱ ደመራ በጉን ይተናኮል ዘንድ በሬውን ያስገባው እርኩሱ ግራኝ አብዮት አህመድ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 26, 2021

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ከወራት በፊት ለአሜሪካዊው ጎብኚ የተናገሯቸውን ኃይለኛና ተገቢ የሆኑ ቃላት ዛሬም በአዲስ አበባው የደመራ ክብረ በዓል ላይ የሚገኙ ከሆነ በድጋሚ ጮክ ብለው መድገም ይገባቸዋል። እንዲያውም አክለው ልክ እንደ ሰርቢያ ኦርቶዶክስክ ቤተ ክርስቲያን ካህን የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ መስጠት ይኖርባቸዋል። አሊያ በክብረ በዓሉ ላይ ባይገኙና ከሃዲው ጋንኤል ክብረት የጻፈላቸውን ንግግር ባያነቡ ይመረጣል።

! እግዚኦ! አንተ እርኩስ የሰይጣን ጭፍራ አብዮት አህመድ አሊ ሆይ፤ ሕዝቤን በረሃብ እና በጥይት እየጨረስከው ነው! ምን ዓይነት አረመኔ ፍጡር ብትሆን ነው?! አንድን የእግዚአብሔር ፍጡር አስረበህ ለመጨረስ መወሰንህ የዲያብሎስን ሥራ እየሰራህ ነውና፤ ጨካኙ ፈርዖን አብዮት አህመድ አሊ፤ ሆይ! ሕዝቤን ልቀቅ! በጎቼን አትጨፍጭፋቸው! የጀመርከውን የጥፋት ዘመቻ ዛሬውኑ አቁም! አቁም! አቁም! በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም!”

ይህን በክርስቲያናዊ ቀጥተኛነትና ድፍረት ቢሉ በሚሊየን የሚቆጠሩትን በጎቻቸውን ሕይወት ለማዳን በበቁ ነበር። በዚህ ፻/100% እርግጠኛ ነኝ!

ከ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መንፈስ ቅዱስ የለም፤ ጨለማ ነግሧል፤ ብርሃኑን ለመመለስ፤ አባቶች በዛሬው ዕለት ይህን ማለት ይኖርባቸዋል!

ለአስናንኪ ለትክክለኛ አበቃቀላቸውና ተሽልተው እንደ ነፁ በጐች መንጋ ንጹሓን ጥርሶችሽ ሰላምታ ይገባል።

የቃል ኪዳኗ እምበኢት ሆይ፤ እኛን ጽዮናውያን አገልጋዮችሽን የቃል ኪዳን ካሣ ዓሥራት አድርጊልን፤ በደልን የሚወዱትን ጠላቶቻችንን ግብፃዊዋኑን የዋቄዮአላህ ጭፍሮችን የጸሎትሽ ክንድ ሙሴ በአሸዋ ውስጥ ይቅበራቸው። አሜን! አሜን! አሜን!

ለዝክረ ስምኪ፤ እምቤቲ ኪዳነ ምሕረት ሆይ፤ በብርሃናዊው ኮከብ ለመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና።

💭 ከ፪ ዓመታት በፊት የቀረበ ጽሑፍ፤

ምስኪኑን በሬ የኢሬቻ ጋኔን ሞልተው ላኩት | የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እሮሮ

👉 ያን ምስኪን በሬ እናስታውሳለን? በዚያን ወቅት እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቄ ነበር፦

ለመሆኑ

  • በሬው የማን ነው?
  • በሬውን ማን አመጣው?
  • በሬው እንዴት ጥብቅ ፍተሻ ሲደረግበት ወደ ነበረው ወደ መስቀል አደባባይ ሊገባ ቻለ?
  • በሬው ወደ ቅ/እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ለምን ተወሰደ?
  • በሬው ፌደራል ፖሊሶችን ለምን አሳሰባቸው? በጠዋትስ ለምን በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተገኙ?

ከደመራ አንድ ሳምንት በፊት በመስቀል አደባባይ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን እና ግዮን(አባይ) ሆቴል አቅራቢያ የሚፈሰውን ወንዝ የዋቄዮአላህ ልጆች ከለሉት፣ ከዚያም የሩጫ ውድድር አካሄዱ፣ የደመራ ችቦ በበራ በሳምንቱ ሰይጣናዊውን የኢሬቻን በዓል በመስቀል አደባባይ በማክበር አጋንንታቸውን በአካባቢው አራገፉ።

አዎ! ይህ በመስቀል አደባባይ እና ቅዱስ እስጢፋኖስ አካባቢ ያለው ቦታ ከፍተኛ የመንፈሳዊ ውጊያ የሚካሄድበት ቦታ ነው። ነገሮችን ለማባባስ በቤተክርስቲያን እና ቤተክህነቷ ውስጥ ሰርገው የገቡ እንደ ኢሬቻ በላይ የመሳሰሉ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ናቸው።

“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸውየሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸውከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይብለህ ተርትባቸውብሎናል አይደል ግራኝ ዐቢይ አህመድ።

አዎ! እኔ ሰይጣን ብሆን ኖሮ የማደርገው ልክ አሁን በቤተክርስቲያን ላይ እይተሠራ ያለውን ነገር ነው። ቤተክርስቲያንን በሞቃታማ ጦርነት ብቻ ተዋግቶ ማሸነፍ እንደማይቻል አውቀውታል፣ ስለዚህ በአንድ በኩል ያዘጋጇቸውን አሕዛብንና መንፋፍቃን ለጥፋት ማሰማራት፣ በሌላ በኩል የኤሬቻ ባሪያዎችን ሰርገው እንዲገቡ ማድረግ፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የቤተክርስቲያንን አመራር በጥቅም መያዝ አስፈላጊ ነው። እንግዳችንን በቁንጣን ለማሰቃየት ብዙ ጉርሻ ማጉረስ እንዳለብን ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማፈንና ከተቀዳሚ የመንፈሳዊ መንገዷ ለማሰናከል ለዓብያተ ክርስቲያናቱ ሰፋፊ መሬት መስጠት፣ ከዚያም “ልማት” በተባለ ዘመቻ አብያተክርስቲያናቱ በንግድ ቤቶች፣ በምግብና መጠጥ ቤቶች፣ በጋራጆች ወዘተ እንዲከበቡ ማድረግ፣ “ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ…” ተብሎ ይተረትባታል።

ባለፈው መስከረም ላይ አርብ ዕለት ወደምወዳት የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አመራሁ፤ ፀሎት ካደረስኩ በኋላ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ምሳ ለመብላት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ወደ ሚገኙት ምግብ ቤቶች አመራሁ። አሳላፊዋ እንደመጣች፣ “የጾም ምግብ መብላት እፈልግ ነበር፤ ግን ምግቦቻችሁን በጭቃው ዘይት (የዘምባባ ዘይት) የምትሠሩ ከሆነ ይቅርብኝ” አልኳት፡ እርሷም “አይ ሁሉም በጭቃው ዘይት ነው የሚሠራው፣ ሁሉም ሰው ተስማምቶ ይበላዋል” አለችኝ። ብዙ ሰው ነበር፤ ወጣቶች። በጣም በማዘን፤ “ምነው! ምነው! እሺ አምቦ ውሃ አምጭልኝ” አልኳት፣ “እሱም የለም ሚሪንዳና ስፕራይት ወይም ሃይላን ውሃ ብቻ ነው ያለን” አለችኝ። ለስላሳ መጠጥ ስለማልጠጣ ውሃ አዝዤ ቁጭ አልኩ። በዚህ ወቅት ባለቤቱ መሰለኝ በእጁ የያዘውን ገንዘብ እየቆጠረ ወደ እኔ መጣና “ውሃው ተስማማህ?… ኑሮ ውድ ስለሆነብን እኮ ነው የጭቃውን ዘይት የምንጠቀመው ፥ ሁሉ ነገር ተወደደ” አለኝ። እኔም፡ “ቤተክርስቲያን ግቢ ይህን መርዛማ ዘይት ለምዕመናኑ በመቀለባችሁ መቅሰፍት እንደሚመጣባችሁ እውቀቱ፣ ጤናማ የሆነውን ዘይት ተጠቅማችሁ ምግቡን ትንሽ ማስወደደ አይሻለም?” አልኩትና ሂሳቡን ሰጠሁት፡ ከዚያም አንገቱን ደፍቶ ሄደ።

ብዙም አልቆየም አንድ አረጋዊ ካህን አባት ምግብ ቤቱ በር ላይ ቆመው ምግብ ሲያዙ አየኋቸው።

የታሸገ ነገር ተሸክመው መራመድ እንደጀመሩ ተከትያቸው ሄድኩና “እንድምን ዋሉ አባ? አንዴ ላናግርዎት?” አልኳቸው። “ከዚህ ምግብ ቤት ምን ዓይነት ምግብ ገዝተው ይሆን? በመርዛማው ጭቃ ዘይት የተሠራውን ምግብ ገዝተው ይሆን?” ስል ፥ እሳቸውም፡ “አይ ልጄ እንጀራ ነው የገዛሁት፣ ምን ዛሬ እንጀራው ውስጥስ ምን እንደሚያስገቡበት ይታወቃል፣ ሰጋቱራ ምናምን ይባላል” አሉኝ፤ በዚህ ጊዜ ሰዎች ከበቡን፡ እኔም፤ “እንዴ አባ ይህ ቦታ የቤተክርስቲያን ንብረት አይደለምን? ማን ምን እንደሚሸጥ ቁጥጥር መካሄድ የለበትምን?” እንዳልኩ በዚህ ጊዜ የከበበን ሰው ቁጥር ጨመረ። ዘበኛ ነገሩም እንደተለመደው “ምንድን ነው? ምንድን ነው?….. ይህን ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄደህ አሳውቅ…ቅብርጥሴ” እያለ መጣ። እኔም “አያገባህም…መንፈስ ቅዱስ ነው የላከኝ፣ በርገር ሁሉ ትሸጣላችሁ…” በማለት ድምጼን “እንደ እብድ” በይበልጥ ከፍ ማድረግ ጀመርኩ። ካህኑም “ተወው ይናገር” በማለት ዘበኛውን ከእኔ አራቁት። አንድ ሌላ ቄስ ወደ እኔ መጥቶ “ኑሮ ውድ ነው፣ በተገኘው ነገር ምግብ ቢሠራ ምን ክፋት አለው? በርገርስ ምግብ አይደለምን?” እንዳሉኝ በይበልጥ ቱግ ብዬ በመጮኽ “ምን ዓይነት መርገም ነው? ቤተክርስቲያን ግቢ እንዴት መርዝ ይሸጣል? በርገር የአሳማ፣ የአህያ ወይም የውሻ ስጋ ሊደባለቅበት እንደሚችል አታውቁምን? ለመሆኑ በጣም ብዙ ምዕመናን ያለው ይህ ድንቅ ቤተክርስቲያን ለምንስ የንግድ ቦታዎች አስፈለጉት? ቤተክርስቲያናችን ሁለት ሺህ ዓመታቱን ሁሉ የዘለቀችው በገንዘብ ነውን? ምግብ ቤቶች መከፈት ካለባቸው እንኳን ባለቤቶቹ ጥንቃቄ የሚያደርጉ የተዋሕዶ ክርስቲያኖች ብቻ መሆን አለባቸው፣ አሊያ ሁሉም መዘጋት ይኖርበታል። ከአህዛብ ሃገር ከማሌዢያ በመጣ በመርዘኛ ዘይት ምግብ ተሠርቶ እየተሸጠ በምን ዓይነት ተዓምር ነው ምዕመናን ከቤተክርስቲያን ተባርከው ሊወጡ የሚችሉት? ቅዳሴው፣ ፀሎቱና ጸበሉ ሁሉ እኮ ኃይላቸውን እየተነጠቁ ነው፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለሁለተኛ ጊዜ በድንጋይ እይወገራችሁት ነው!” በማለት ስናገር ሁሉም በሃፍረት አንገታቸውን ደፍተው ይታዩ ነበር። (የጉልበቶቻቸውንና ክንዶቻቸውን መገጣጠሚያዎች ስለታመሙ አባቶች መስቀል እንዲያሳርፉባቸው የሚጠይቁ ብዙ ወጣቶች አይቻለሁ፤ ጭቃው ዘይት)

በአንድ በኩል ጉዳዩ በጣም የሚያሳዝንና መፍትሄም ቶሎ የሚሻ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ግን በተለይ የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እሮሮ አሁን በዚህ መልክ መሰማት መጀመሩ ለበጎ ነገር ስለሆነ በከፊል አስደስቶኛል። አካባቢው ከፍተኛ መንፈሳዊ ውጊያ የሚካሄድበት ነውና፣ ዲያብሎስ ከሁሉም አቅጣጫ ነው እየተዋጋን ያለው።

_________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: