Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2021
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for September 6th, 2021

Orthodox Father’s Warning Against Freemasons and New World Order

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 6, 2021

✞✞✞ የኦርቶዶክስ አባት በፍሪሜሶን እና በአዲሱ የዓለም ሥርዓት ላይ ማስጠንቀቂያ ✞✞✞

✞✞✞God bless you, Mar Mari Emmanuel!✞✞✞

እግዚአብሔር ይስጥልን አባ አማኑኤል! እግዚአብሔር እንደርስዎ ያሉ በግልጽና በቀጥታ የሚሰብኩና የሚናገሩ አባቶች ይስጠን። ለዚህ ክፉ ጊዜ የተዘጋጀችውማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፤ ግን ምን ይደረግ በከሃዲዎች እጅ ውስጥ ናት፤ አባ አማኑኤል እንዳሉት፤ “በዘመነ ክርስቶስ አንድ ከሃዲ ይሁዳ ነበር፤ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያንን በገንዘብ የሚለውጡ ብዙ ይሁዳዎች አሉ!”። አባ አማኑኤል ቀጥለውም፤ “እኔ ልጆቼ/ በጎቼ ሲያለቅሱ ዝም አልልም፤ በዳዮቹ ከእኔ ጋር ነው የሚጣሉት፤ እሳት ነው የሚጠብቃቸው፤ ልጆቼን አላስነካም፤ ለእነርሱ እና ለአምላኬ ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስል ሁሌ ሕይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።” ብለዋል። ክርስቲያናዊ አባት ማለት እንዲህ ነው! ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መፈንቅለ መንግስት በጊኒ | የግራኝ ወዳጅ አምባገነኑ ፕሬዚደንት ታሠረ፤ ቀጣዩ አ. አህመድ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 6, 2021

ከአረመኔዎቹ አምባገነኖች ኢሳያስ አፈቆርኪ እና ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በፍቅር መተቃቀፍ የሚወደው ፋሺስቱ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ዛሬ ከስልጣን ወርዶ ከታሠርው የጊኒ አምባገነን ከፕሬዚደንት አልፋ ኮንዴ ጋርም ጥሩ ግኑኝነት ነበረው።

🦃 Birds of a Feather Flock Together 🦃

🦃 የላባ ወፎች አብረው ይጎርፋሉ 🦃

TDF = ELA (ኢነሠ) = ‘የኢትዮጵያ ነፃ አውጪ ሠራዊትባፋጣኝ ግራኝን መያዝ አለበት፤ ጦርነት አያስፈልግም፤ እንደ ጊኒዎች ልዩ ኮማንዶ ወደ አዲስ አበባ ላኩ!

TDF ከ እንግዲህ ወዲህ የኢትዮጵያ ነፃ አውጪ ሠራዊትELA (ኢነሠ) ተብሎ ይጠራ፤ ብዙ ሕዝብ አስተባብሮ በይበልጥ መጠናከር ይችላልና። ጽዮናውያን እንደ እባብ ብልሕ ሁኑ፤ ጦርነቱንና ሰቆቃውን ሁሉ ባጭሩ ለመግታት አውሬውን መያዝ ወይም መድፋት ግድ ነውና! እስካሁን አንድም የወንጀለኛው ግራኝ ባልደረባ አለመያዙ እና በእሳት አለመጠረጉ በጣም የሚያስገርም ነው፤ እነ ባጫ፣ ጁላ እና የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ፈላጭ ቆራጮች ይህን ሁሉ ግፍ ሠርተው ለአንድም ቀን እንኳን ቢሆን እንዴት አየር መሳብ ተፈቀደላቸው? ያውም እስከ ሃምሳ ሺህ የታጠቁ ጽዮናውያን በሚገኙባት በአዲስ አበባ። ኧረ ባካችሁ፤ አንድ በአንድ ድፏቸው!

የጊኒ እና ኢትዮጵያ ባንዲራዎች ተመሳሳይ ቀለማት አሏቸው።

ከወራት በፊትም የኢትዮጵያን ቀለማት የተዋሰችው ምዕራብ አፍሪቃዋ ማሊም አምባገነን መሪዋን አስወግዳለች።

በመጥፎው አያድርገው እንጂ፤ ምኒሊካዊቷ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ የዚህ ትንቢት መፈጸሚያ እየሆነች አይደለምን?

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፥፲፮]

እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

👉 የማሊ ጦር ሰራዊት መፈንቅለ መንግሥት አደረገ | የኢትዮጵያ ሰራዊትስ?

💭 በምዕራብ አፍሪቃዋ ማሊ ፀረ-መንግስት ተቃዋሚዎች በሠራዊቱ ድጋ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አካሂደዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩና ፕሬዚደንቱ ታሥረዋል። አሁን ማሊያውያን የኢትዮጵያን ቀለማት እያውለበለቡ ወደ አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን በመግለጥ ላይ ናቸው።

👉 ዛሬ ፲፪/፲፪/፲፪ ነው – ቅዱስ ሚካኤል + ፍልሰታ ለማርያም

🔥 ቀጣዩ በኢትዮጵያ?

በኢትዮጵያም ተመሳሳይ መፈንቅለ መንግስት በሃገርወዳድ የሠራዊቱ አባላት በቅርብ ይካሄዳል የሚል እምነት አለኝ። ሽብርተኛው አብይ በመርበትበት ላይ ነው፤ ሙቀቱ ጨምሯል። ከፖለቲከኞችና ዋጋቢስ ድርጅቶቻቸው ምንም ተስፋ የለም!

_____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: