Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2021
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for September 2nd, 2021

ዲያቆኑ ከጦር ግንባር | ጦርነቱ ክርስቲያኖችን አጥፍቶ የ666ቱን እስላማዊ ኤሚራትን በኢትዮጵያ የማንገሻ መንገድ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 2, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

፻/ 100% ትክክል! አዎ! ዓለም ሰምቶት ለማያወቀው ግፍ፣ ለጭፍጨፋ፣ ለረሃብ፣ ለበሽታ፣ ለአድሎና ለስደት እየተጋረጡ ያሉት ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው፣ እየወደሙና እየታቃጠሉ ያሉት የተዋሕዶ ክርስትና ገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም ለአዳም ዘር ሁሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ በጽዮናውያን እምነተ ጽኑነት እንዲቆዩ የተደረጉ ታሪካዊ ቅርሶች ናቸው። አዎ! የፕሮቴስታንት ቸርች ወይም የሙስሊም መስጊዶች ሲፈርሱ አናይም፤ “አል-ነጃሽ”ም ሆን ተብሎ ነው በግራኝና ቱርክ ሞግዚቱ እንዲፈርስ የተደረገው። በአክሱም ጽዮን ጂሃዳዊ ጭፍጨፋ መላው የኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ይነሳብናል ብለው ስለተደናገጡ። አዎ! እነዚህ የዲያብሎስ ጭፍሮች አንድ ሺህ ክርስቲያን ገድለው፤ አንድ ሙስሊም ይገድላሉ፣ መቶ ዓብያተ ክርስቲያናት አቃጥለው፤ አንድ መስጊድ ያቃጥላሉ፣ ዘጠኝ “መድኃኒት” ሰጥተው አንድ መርዝ ጠብ ያደርጋሉ። ይህ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከተሰቀለበት ዕለት አንስቶ ሲከተሉት የነበረ እባባዊ አካሄድ ነው።

የኤዶማውያኑ፣ የእስማኤላውያኑ እና የኦሮሞዎቹ ዋና ተልዕኮ ኢትዮጵያውያኑኢትዮጵያዊነታቸውን፣ ተዋሕዶ ክርስትናቸውን እንዲሁም ግዕዝ ቋንቋን እርግፍ አድርገው በመተው እንደ ሱዳን የወደቁ ሕዝቦች እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ያው! በዘመናችን ደግሞ በዲቃላው ምኒልክ በኩል የተጀመረውን ጂሃድ አንድ በአንድ እየተገበሩት ነው።

ታዲያ ይህ በእንዲህ እያለ፤ አሁን መጠየቅ ያለብን፤ የ፫ሺህ ዓመት ሥልጣኔ ያላቸው ጽላተ ሙሴን በእጃቸው ያደረጉ፣ ጽዮን ማርያምን እና ቅዱሳኑን ከጎናቸው ያሰለፉት አክሱማውያን፣ ከምኒልክ እስከ ግራኝ አብዮት ባሉት ዘመን እንዴት የኦሮሞዎች፣ የኤዶማውያንና እስማኤላውያን ሤራ ሰለባዎች በቀላሉ ለመሆን በቁ? ዛሬም የኤርትራም የትግራይም ተጋሩዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን በደማቸው እየገበሩ ሳለ፤ ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው የሚባል አስተዋጽኦ ያላበረከቱት ኦሮሞዎች የራሳቸውን ልጆች ሳይገብሩ በእጅ አዙር በኩል የኢትዮጵያውያንን ደም እያፈሰሱና የ አዲስ አበባን፣ ቤኒሻንጉልን እና ወሎን በሮች ቁልፎች ከጽዮናውያን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ይህን መሰሉ ሞኝነትና የዋሕነት የተሞላበት ክስተት በጽዮናውያን ዘንድ እንዴት በተደጋጋሚ ሊከሰት ቻለ? መቼ ነው ጽዮናውያን ማንነታቸውንና ምንነታቸውን ብሎም ታሪካቸውን በአግባቡ ተረድተው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ነገር ሁሉ “የኛ ነው” በማለት ከምስጋና ጋር ለመያዝ ዝግጁዎች የሚሆኑት? ምናልባት እንደ አፄ ካሌብ ያለ መሪ ሲመጣ?

የጽዮንን ልጆች መፈታተን፣ መተናኮል እና ለማጥፋት መሻት ከጥንት ጀምሮ የኤዶማውያኑ እና የእስማኤላውያኑ እስራኤል ዘስጋ ሕልምና ተግባር ነው። እኛ ከምናውቀው ታሪክ እንኳን እንነሳ ብንል፤ በኢትዮጵያ አክሱም/ትግራይ የሚገኙትን ጽዮናውያኑን የጽላተ ሙሴ ጠባቂ አባቶቻችንና እናቶቻችንን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በ፮/6ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን (ከወረርሽኞች ሁሉ የከፋው666 እስልምና የተገለጠበት ዘመን) ዘመቻው ተጧጡፎ ነበር።

በቁስጥንጥንያ እና አክሱም መኻል ምን ተፈጠረ? ግብጻውያን ክርስቲያኖችን ይተናኮሉ የነበሩት ቁስጥንጥናውያን በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችም ላይ ተንኮል ሠርተው ይሆን? ከዚህ ዘመን አንስቶ ዓለምን የለወጡ ወረርሽኞች የያኔዎቹን ኃያላን መንግስታትን ክፉኛ አጠቋቸው።

Anti Ethiopia Conspiracy Can Cause Universal Cataclysm as Ethiopia is a Biblical Nation Under the Almighty Egziabher God

በቢዛንታይን / በቁስጥንጥንያ፤ በንጉሠ ነገሥት ዮስጢያኖስ (እ.አ.አ ፭፻፳፯፥፭፻፷፭/ 527-565 ከክርስቶስ ልደት በኋላ) ዘመነ መንግሥት ውስጥ ከተከሰቱት ወረርሽኞች መካከል አንዱ(የዩስጢያኖስ ወረርሽኝ ፭፻፵፩፥፭፻፵፪/ 541-542) በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ለ፪፻፳፭/225 ዓመታት ያህልበባሕረ ሜዲትራኒያኑ ዓለም የሚኖሩ ብዙ ሚሊየን ሰዎችን ጠርጓል።ወረርሽኙ የጠፋው በ፯፻፶/ 750 ዓ.ም. ላይ ነበር። ወረርሽኙ ከኢትዮጵያ በግብጽ በኩል ተሰራጭቷል ተብሎ ይታመናል። ጽላተ ሙሴን፣ በጽዮን ተራራ የሚገኙትን ቅዱሳን እና የአባይ/ተከዜ ወንዞችን እናስታውስ!

የመላው ዓለም ታሪክን ከተመለከቱ፤ ሙሉውን የ ፭፻/ 500 ዎቹ መካከለኛ በእያንዳንዱ ታላላቅ ስልጣኔ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ታይቶ ነበር። ያልተለመዱ የአየር ሁኔታዎች፣ መጥፎ ሰብሎች፣ እንደዚሁም ከዚህ አይነት አደጋ ጋር ሊዛመዱ የሚችሉ ሌሎች ክስተቶች የታዩባቸው ዘመናት ነበሩ።

👉 ሮማዊው ግዛት ወደቀ

👉 የቻይና ኩን ሥርወመንግሥት አከተመ

👉 በጃፓን የሞኖኖቤ / ሶጋ ጦርነት በመቀስቀሱ የሺንቶ እምነት ተወግዶ የቡድሃ እምነት የበላይነቱን ያዘ

👉 በኮሪያ የሶስት ነገስታት ሶስትዮሽ ጦርነት

👉 የእስልምና ወረርሽ የመካከለኛው ምስራቅን አጥለቀለቀው

👉 በሕንድ ውስጥ ከፍተኛ ዕልቂት

👉 ‘በዛሬውዎቹ የአሜሪካ ግዛቶች’ ይገኝ የነበረው ጥንታዊው የማያ (ሜክሲኮ) ሥርወ-መንግሥት ውድቀት። 2012/2021 ዓ.ም’ ን የፍጻሜ ዘመን መጀመሪያ አድሮ የቆጠረው የማያ ካሌንደር ከኢትዮጵያ የሔኖክ ካሌንደር ጋር ዝምድና እንዳለው ይነገራል።

✞✞✞ የቅዱሳን ሕይወት (ክብረ ቅዱሳን)✞✞✞

የ፮/6ኛው መቶ ክፍለ ዘመንበአውሮፓውያኑ ዘንድ ይፈሩ የነበሩትና በአውሮፓ ላይ ከፍ ያለ ተጽእኖ የነበራቸው አንጋፋው ንጉሠ ነገሥት ቅዱስ ካሌብ

በ፮/6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ (የአክሱም) መንግሥት ቀይ ባሕርን ተሻግሮ እስከ ደቡብ ዓረብ (የመን)ድረስ ግዛቱን አስፍቶ እንደነበር ይታመናል። ከ፬፻፺፭፭፻፳፭ /495-525 .. የነገሡት አጼ ካሌብ በየመን (ናግራን/Najran) አካባቢ የሚገኙ ክርስቲያኖች ድሁ ንዋስ (ፊንሐስ) በተባለ አይሁዳዊ ከደረሰባቸው ጥቃት ለመከላከል መቶ ሃያ ሺህ/120.000 ሠራዊት በ፷/60 መርከቦች አዝምተው ከጥቃት ታድጓቸዋል። አጼ ካሌብ ከየመን በድል ከተመለሱ በኋላ ድል ያቀዳጀውን ክርስቶስን አመስግነው፣ አክሊለ ንግሡን (ዘውዱን) ወደ ኢየሩሳሌም ለመታሰቢያ ልከው፣ ልቻቸው ገብረ መስቀልን በምትኩ አንግሠው ቀሪ ሕይወታቸውን ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ አባ ጰንጠልዮን አክሱም አካባቢ በመሠረቱት ገዳም በምናኔ አሳልፈዋል።

ከአብርሃና አጽብሓ ቀጥሎ ከተነሡት ቅዱሳን ነገሥታት ክርስትናን በማስፋፋትና በመንከባከብ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያደረጉት ከ፬፻፹፭፥፭፻፲፭/485-515 .. የነበሩት አፄ ካሌብ ናቸው፡፡

አፄ ካሌብ ስለ ክርስትና መስፋፋት፤ ስለ ክርስቲያኖች አንድነት ብዙ ተጋድሎን ከተጋደሉና ከአሳለፉ በኋላ መንግሥታአውን ለልጃቸው ለአፄ ገብረ መስቀል አስረክበው፤ መንነው፤ ልብሰ ምንኩስናን ለብሰው ከአክሱም ወደ ሰሜን ምሠራቅ በሚገኘው በአባ ጰንጠሌዎን ገዳም በሚገኘው ዋሻ የምናኔ ሥራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ከዚህም ጋር ቤተ መንግሥታቸውን ለቀው በመነኑበት ሰዓት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነውን ማለትም የነገሡበትን ዘውድ ወደ ጌታ መቃብር ጎልጎታ ልከው በምናኔ 12 ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ በ536 .. ግንቦት 20 ቀን አርፈዋል፡፡ አፄ ካሌብ በምንኩስናና በምናኔ ሕይወት የቅዱሳንን አሠረ ጽድቅ ፈጽመው ያለፉ ደገኛ ንጉሥ ስለነበሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቁጥራቸው ከቅዱሳን ነው፡፡ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ 1974 ..)

አፄ ካሌብ የታዜና ልጅ ሲሆኑ የኖሩበትም ዘመን ከ417 እስከ 527 ዓም ነው። በኢትዮጵያ ክርስትና ከተሰበከ ወዲህ ከነገሱ የአክሱም ነገሥታት ከኢዛና ቀጥሎ ከፍ ያለ ስም ያላቸውና ከፍተኛ ተግባርም ያከናወኑ ናቸው። በአፄ ካሌብ ዘመነመንግስት ኢትዮጵያ ከከፍተኛ ብልፅግና እና የስልጣኔ ደረጃ ላይ የደረሰች ቢሆንም የሰላም ጊዜ ግን አልነበረም። አገሪቱ በውስጥም ሆነ በውጭ የተለያዩ ጦርነቶች ነበሩባት። ስለአፄ ካሌብ ዘመነ ስልጣኔ ጦርነት ብዙ ማስረጃዎች በድንጋይ ላይ ከተቀረፁ ፅሁፎች ተገኝተዋል።

የአፄ ካሌብን ታሪክ አስመልክቶ በተወሳ ቁጥር በብዙ ፀሐፊዎች የሚጠቀሰው በደቡብ አረብ የደረጉት ዘመቻ ነው። አፄ ካሌብ ወደደቡብ አረብ (ወደ አሁኑ የመን) ያደረጉት ዘመቻ አላማ ሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ፍላጎት እንደነበረው ታዉቁዋል። ከአፄ ካሌብ በፊት የነበሩት የአክሱም ነገስታት የጦር አበጋዞቻቸውንና እንዲያም ሲል አልጋዎራሾቻቸውን እየላኩ በደቡብ አረብ ዉጊያ አድርገዋል። ይሁንና ግን ንጉሡ ራሱ የጦርነቱ መሪ በመሆን ከኢትዮጵያ ውጭ ውጊያ ያካሄደ ንጉስ አፄ ካሌብ የመጀመሪያው እንደነበሩ የታሪክ ማስረጃወች ይጠቁማሉ። አፄ ካሌብ ጦርነቱን አውጀው እና ሰራዊታቸውንም ይዘው ባህር ተሻግረው ለዘመቻ ከመሄዳቸው በፊት የህዝብን ድጋፍ ጠይቀዋል ። በዚያን ዘመን ህዝቡ የሃይማኖት መሪዎችን አጥብቆ ያዳምጥ ስለነበር የአክሱም ህዝበ ክርስትያን ርቀው እንዳይሄዱየሚለዉን ትእዛዝ በማንሳት ወደ ደቡብ አረብ ሄደው ለሚያደርጉት ጦርነት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የነበሩትን ጰንጠልዮንን ጠየቁ። አቡነ ጴንጠልዮንም ሙሉ ድጋፋቸውን ከመስጠታቸውም በላይ ጦርነቱን በአሸናፊነት አጠናቀው በክብር ወደመናገሻ ከተማቸው አክሱም እንደሚመለሱ ያላቸውን መልካም ምኞት ገለፁላቸው። አፄ ካሌብ ይህን መሰል ማበረታቻ ከጳጳሱና በእሳቸው በኩል ከሕዝበክርስትያኑ ካገኙ በሁዋላ ሰራዊታቸውን የምያጉጉዙበት ብዙ መርከቦችን አዱሊስ አጠገብ በነበረው የመርከብ መስሪያ ማሰራት ቀጠሉ።

በአፄ ካሌብ ዘመን የኢትዮጵያ መርከቦችን አሠራር አስመል ክተው የባዛንታይነ የታሪክ ፀሐፊዎች መጠነኛ ሃሣብ አስፍረው አልፈዋል፡፡ አንደነሱ አባባል ከሆነ በዚያን ዘመን የኢትዮጵያ መርከ ቦች የሚገጣጠሙት በምስማር ሳይሆን በገመድ ነበር፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ በቂ ብረት ባለ መመረቱ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን የመርከቦቹ መጠን በሮማውያን መንግሥት እና በአካባቢው ከሚሰሩት ያነሰ አልነበረም፡፡ አፄ ካሌብ ወደ ደቡብ አረብ የሚዘምተውን ሠራዊት በባህር ላይ የሚያጓጉዙ በት በኪራይ የተገኙ 110 መርከቦች እና አዱሊስ አጠገብ ገበዛን በሚባል የመርከብ መንቢያ ቦታ ያሠሯቸው 120 መርከቦች በአን ድነት 230 መርከቦችን አሠማርተው እንደነበር የፅሁፍ ማስረጃ ዎች ያሪጋግጣሉ፡፡ በነዚህ መርከቦች የተጓጓዘውን የአፄ ካሌብ የሠ ራዊት ብዛት በተመለከተ አንዳንዶቹ የፅሁፍ ማስረጃዎች 32,000 ነው ሲሉ ሌሎቹ ቁጥሩን ወደ 70,000 ያደርሡታል፡፡ አፄ ካሌብ ሠራዊታቸውን እጓጉዘው ደቡብ እረብ በደረሱ ጊዜ የዚያ አገር መሪ የነበረው ዱነዋስ የአክሱም ንጉሥ ጦር በመገስገሥ ላይ መሆ ኑን ተገንዝቦ ነበርና በወደቡ ላይ መርከቦቹ ጭነታቸውን እንዳያራግፉ ረጅምና የማይበጠስ ሰንሰለት አጋደመበት። ይህንንም የሚ ጠባበቁ ወታደሮች ዘብ እቆመበት፡፡ በዚህም ምክንያት የአፄ ካሌብ መርከቦች ደቡብ አረብ ሢደርሱ መልህቅ ጥለው ጦሩን ወደየብሶ ለማራገፍ ሳያስችሰው ቀረ፡፡ ከላይ የፀሐይ ሙቀት ከታች ቅዝቃዜ ሢ ያጠቃው የሠራዊቱ መንፈስ እንዳይዳከም ያሰቡት ንጉሡ ወ ደቡ ራቅ ብለው በመጓዝ አመቺ በሆነ ቦታ እየቆሙ የተወሰነውን ወታደር አራገፉ እና ወደቡን ይጠብቁ የነበሩትን የዱነዋሰ ወታ ደሮች ከበስተጀርባቸው ሄደው አጠቋቸው፡፡ ሠንሠለቱም ተበጠሠና ለብዙ ቀናት ባህር ላይ ይጉላላ የነበረው ጦር ወርዶ የዱነዋስን ጦር በብርቱ ተዋግቶ ድል አደረገ፡፡ አፄ ካሌብ በመጨረሻ በአሁኑ የየመን ዋና ከተማ ሰንዓ ደርሰው ሰላምን ካፀኑ በኋላ በቂ የጦር ኃይል ትተው በድል አድራጊነት ወደእከሉም ተመለሡ።

የአፄ ካሌብን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የደቡብ አረብ መሪ ዱነዋስ በሰማ ጊዜ በዚያ የሚገኘውን የንጉሡን ወኪል ወታደሮች በየ ጊዜው ጦርነት እያደረገ ማጥቃት ጀመረ፡፡ ይህንም የጦርነት ዜና አክሱም በደረሰ ጊዜ እፄ ካሌብ በቂ ቁጥር ካለው ወታደር ጋር አብርሃ የሚባለውን የጦር አበጋዝ ወደደቡብ እረብ ላኩት፡፡ አብርሃ እጅግ ስሙ የተጠራ የጦር አበጋዝ ነበረና የዱነዋስን ሠራዊት ደምስሶ የአካባቢውን ሰላም እንደገና አስጠብቆ ተመለሰ፡፡ አፄ ካሌብ ከደቡብ አረብ ዘመቻ መልስ ጥቂት ዓመታት እንደቆዩ ልብሰ- ግሥታቸውን አውልቀው አልባሌ ልብስ ለብሰው አባ ጰንጠሊዮን ገዳም ገብተው ዘጉ፡፡ አፄ ካሌብ የገዳም ኑሮ ለመኖር በወሰኑ ጊዜ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ከነበራቸው አራት ወንዶች ልጆች ለአንደኛው ማስረከባቸው በህይወት ታሪካቸው ተፅፏል፡፡ አፄ ካሌብ የገዳም ኑሮ በጀመሩበት ወቅት ዘውዳቸውን ኢየሩሳሌም በሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ በተሰራው ቤተክርስቲያን መንበ ር ላይ እንዲያስቀምጡት ወደዚያ መላካቸው ተፅፏል፡፡ ኢየሩሳሌ ሴም ብዙ ጊዜ ስስተወሪረች ግን የአፄ ካሌብ ዘውድ :እስከዛሬ:ድረስ: ተጠብቆ ለመቆየት አልቻለም። አፄ ካሌብ ፃድቅ የተባሉ ሢሆን መታሰቢያ ቀናቸውም ግንቦት ፳/20 ቀን ነው፡፡

✞✞✞ብርሃ ወ አጽብሃ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት። የሁለቱ ወንድማቾች የመቃብር ስፍራቸው ውቅሮ አካባቢ ነው።✞✞✞

በፊት እንደተገለጸው አብርሃ አሪየልን ገሎ በመንገሱ የኢትዮጵያው ንጉስ አፄ ካሌብ ተናደዱ፡፡ በመናደዳቸውም አብርሃን ለመውጋት ምለው ነበር፡፡ አብርሃ በብልጠቱ ማህላቸውን ካስነሳቸው በኋላ አምኖ ሊቀመጥ ባለመቻሉ የሚያስደስታች ነገር ለመስራት ብዙ ይጥር ነበር፡፡ ሰዎች ከየመንም ተነስተው ሆነ ከሌላ ቦታ የመንን አቋርጠው ወደ ካባ (መካ) ሲሄዱ ያያል፣ ይሰማል፡፡ አሁን ባብ አልየመን የሚባለው አካባቢ በጣም ግዙፍ ቤተክርስቲያን ለመስራት አሰበ፡፡ ያሰበውን ቂም ይዞብኛል ብሎ ለፈራው አፄ ካሌብ ‹‹…እነሆ በረከት ንጉስ ሆይ የሚያስደስትህ ከሆነ ይህን ልስራ..›› አለ፡፡ ፍቃድም አገኘ፡፡ ረጅም ጊዜ የወሰደ አል ቊለይስየተባለ ቤተክርስቲያን አሰራ። በአይነቱም ሆነ በግዝፈቱ በዛን ወቅት በጣም የተለየ እጹብ ድንቅ ነበር፡፡ እንዲያውም ከቁስጥንጥንያው ሃጊያ ሶፊያ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ እስከታነጸበት ዘመን ድረስ በዓለም ድንቁ የቤተክርስቲያን እርሱ ሊሆን እንደሚችል በብዙዎች ዘንድ ይነገራል። በየመኑ ጦርነት ምን እንደረሰበት አናውቅም እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይህ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ለጉብኝት ክፍት ሆኖ ነበር፡፡

አብርሃ እንዲህ ሲል አዋጅ አስነገረ፡፡ “..እዚሁ በቅርቡ ትልቅ ቤተክርስቲያን እንደ መካ ያለ ስለሰራን መካ በመሄድ ፋንታ እዚህ ተጠቀሙ፡፡ ይህ ማለት እምነታሁን ለውጡ ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም በእየእምነቱአለ፡፡ ከመካ የመጣ ሰው ወደዚህ ቤተክርስቲያን በመግባት ቤተክርስቲያኑን በሰገራ እና በሽንት አቆሸሸው!“ ይላል ታሪክ፡፡ ሲቀጥልም አብርሃ ይህንን በተመለከተ ጊዜ ንዴቱን መቆጣጠር አልቻለም ነበር። ስለዚህ ሰራዊት አዘጋጅቶ መካን ለመውረርና ለማጥፋት ወሰነ። ምነው ያኔ አጥፍቶት ቢሆን! ግድየለም አሁንም እንደ ሙስሊሞቹ ትንቢት፤ ቀጭን እግር ያለው ኢትዮጵያዊ ይህን የ666 መሳለሚያ ጥቁር ድንጋይ እንደሚያፈርሰው ይጠቁመናል። የተበላሸም ሰዓት በቀን ሁለቴ ትክክል ነውና ይህን ትንቢት መድኃኔ ዓለም ያስፈጽመው!

ካዘጋጀው ፲፫/13 ዝሆኖች መካከል ሙሃሙድ የሚባል ግዙፍ ዝሆን ይገኝበታል። (The year of elephant) ተብሎ ያወቅት የሚጠራው በዚህ ምክንያት ነው) ለጦርነቱ ጉዞ ሰራዊቱን ለማሰባሰብ ‹‹እንቁም›› ያለበት ቦታ ዛሬ ድረስ ‹‹ንቁም›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ታክሲ ገብተህ ንቁም ብትል እዛው ወስደው ያወርዱሀል፡፡ ጉዞው ተከውኖ አብርሃ እያሸነፈ መካ ደረሰ። የሀሰተኛው ነብይ አያት አብዱል ሙጠሊብ ያቀረቡትን እርቀ ሰላም አልቀበል ብሎ ካባን ለማፍረስ ጉዞውን ቀጠለ። የመሀመድ አያትም ከተማዋ ከሚደርስባት ሰማያዊ መቅሰፍት ይጠበቊ ዘንድ ከከተማ ወጥተው ወደ ከፍታ ቦታ ከነቤተሰቦቻቸው እንዲሸሹ ለሰዎች ነገሩ፡፡ ሽሽቱ ቀጠለ..…

የአብርሃ ጦር መካ መግቢያ ላይ አልሙሃሲር የተባለ ሸለቆ እንደደረሰ በወፍ መንጋ ተከበበ ተደበደበም። አብርሀም ከዚህ ጥቃት ለመሸሽ ወደ የመን ተመለሰ። ዳሩ ግን በመንገድ ሳለ በጥቃቱ ስጋው ተበጣጥሷል። (ይህ ነው ቢባልም ጂዛን ላይ እንደሞተ ነው የሚነገረው፡፡ ያውም ወፏ የያዘችውን አጥንት ስትለቀው ወርዶ በረቀሰው የሚልም አለ፡፡)

አብርሃ በስልጣን ላይ ባለበት ወቅት ያው ለንጉስነቱ እንዲሰግዱለት እንዳስገደዳቸው እነሱም አንሰግድም እንዳሉት ይነገራል፡፡ ታዲያ ብልሁ አብርሃ የቤቶቻቸውን በሮች ከአንድ ሜትር ትንሽ ብቻ ከፍ አድርጎ በማሰራቱ ሲወጡ እና ሲገቡ የግዳችን ሰገዱለት ይባላል፡ ለዚህ ይባላል ግን ማረጋጫ አለው፡፡ አሁን አሮጌው ሰነዓ የሚባለው ባብ አልየመን ያሉ በእሱ ጊዜ የተሰሩ 14000 ቤቶች ምስክርነት ለመስጠት ቆመዋል፡፡

ከእስልምና እምነት መምጣት በፊት አረቦች የሚኖሩት መካ፣ ያትሪብ/መዲና (የአይሁዶች ከተማ ነበረች) ወዘተ ተብለው ይጠሩ በነበሩ ሠፈሮች አካባቢ ነበር። አረቦች የአስተዳደር ሥርዓት ፣ የህግ ሥርዓት ወይም የእደ ጥበብ ስምሪት አልነበራቸውም። መንግሥትና መንግሥታዊ አስተዳደር የሚባል ነገርም አያውቁም ነበር። ቁሬሺ፣ ባኑ ሃሺም፣ ባኑ ኡማያ ወዘተ በሚባሉ ጎሳዎች ተለያይተው ግን ይጣሉ ነበር። ጣዖት አምላኪዎችም ነበሩ። ካባ የተባለ ድንጋይም ያመልኩ ነበር። እስከ አራት መቶ ዓ.. አካባቢ አረቦች ለሚናገሩት ቋንቋ መፃፊያ ፊደል አልነበራቸውም። ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ በንግግር ግጥም መፎካከር የአረቦች ባህል ነበር። እጅግ በጣም ግጥም የሚገጥመውን ሰው መጅኑን እያሉ ይጠሩት ነበር። አረቦች ከእስልምና በፊት የነበረውን ዘመን ጃሂሊያ ወይም የድንቁርና ዘመን ብለው ይጠሩታል።

በዚህ ጊዜ ነበረ አንድ መሀመድ የሚባል አረብ መካ አጠገብ በሚገኜው የሂራ ኮረብታ ላይ ሳለሁ ጅብሪል ነገረኝ ብሎ አዲስ እምነት በአቅራቢያው ላሉ ሰዎችና ለዘመዶቹ የሰበከው። በልዩ ልዩ የምዕራባዊ ትረካዎች እንደሚነገረው መሀመድ በሂራ ኮረብታ ላይ ጅብሪል ነገረኝ ካለበት ጊዜ በፊት እሱ በሚኖርበት አካባቢ ክርስትናን ለማስፋፋት ክርስቲያኖች ብቅ ይሉ እንደነበረ ይነገራል። ከነዚህም ውስጥ ዋናዎቹ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ከኢትዮጵያውያንም መካከል የሂመራ (የየመን) ንጉሥ አብርሃ አረቦች ወደ ሰንዓ መጥተው በሰንዓ የተገነባውን ትልቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተደብቀው በመጸዳዳት ባረከሱ ጊዜ አረቦቹን ለመቅጣትና የመካን የካባ ጣዖት ለማፍረስ ሥንቅ በዝሆኖች ጭኖ ያደረገው ዘመቻ ይታወሳል። መሀመድ ይዞት ለተነሳው እምነት መሠረተ ሃሳቡን ያገኘው ክርስትናን ለማስፋፋት እሱ ወደሚኖርበት አካባቢ ከሄዱ ኢትዮጵያውያን የወንጌል አስተማሪዎች መሆኑን በእስልምና እምነት በተለይም በቁርአን ውስጥ ያሉ ጭብጦች ያመለክታሉ።

የእስልምና እምነት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ “ኢሳ” የሚባል ስም ነው የተሰጠው። በሌሎች አገሮች የነበሩ ወንጌላውያን ኢየሱስ ክርስቶስን፥ “የሽዋ” ወይም “ሄሱስ” ወይም “ጀሽዋ” ወይም “ጂሰስ” ወይም “አየሱስ” እያሉ ነበር የሚጠሩት። በእስልምና ውስጥ ላለው “ኢሳ” ለሚለው ቃል በጣም የሚቀርበው የግዕዙ “ኢየሱስ” ሲሆን ቀጥሎም የግሪኩ “አየሱስ” ነው። መሀመድ ቃሉን ከግዕዙ ወይም ከግሪኩ መውሰዱን ለመለየት ቀላሉ ማነጻጸሪያ መሀመድ “ማርያም” የሚለውን ቃል ከየት እንዳገኘው መለየት ነው። በእስልምና “ማርያም” የሚለው ቃል ድንግል ማርያምን ለመጥራት የሚጠቀሙበት ሲሆን ቃሉ በግሪክ “ማሪያ” የሚል ሲሆን በግዕዝ ደግሞ “ማርያም” ነው። ለድምዳሜ በቂ ባይሆኑም ከነዚህ አጠራር በቀላሉ መሀመድ ቃሉን ከግዕዝ ሰዎች እንዳገኘው መንገዱን ያሳያል። እብራይስጥና ግዕዝ ተቀራራቢ በመሆናቸው ምክንያት አጋጣሚውን በመጥለፍ አንዳንድ ታሪክን ለመሠሪ ዓላማ ለመጠቀም የተነሱ ምዕራባውያን እና አይሁድ ነን ባዮች መሀመድ የእስልምና እምነትን መሠረተ ሃሳብ ያገኘው ከአይሁዶች ነው ለማለት ይቃጣቸዋል። ነገር መሀመድ ሃሳቡን ከአይሁዶች እንዳላገኘው ብዙ ማስረጃወችና አመልካቾች አሉ። በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሱስ ክርስቶስ አያምኑም። ስሙንም አይጠሩም። እንኳን አምላክ ነቢይ ነውም አይሉም። ቅድስት ድንግል ማርያምንም በእምነታቸው አያውቋትም። በተጨማሪ “ኤልያስ” የሚለውን መጠሪያ እስላሞች የሚጠሩት እንደ ግዕዙ “ኤልያስ” ብለው እንጂ እንደ እብራይስጡ “ኤልያሁ” ብለው አይደለም። በተለይም ደግሞ የእስላሞች ቁርአን መጠሪያው “መጽሐፍ” ተብሎ ነው። “መጽሐፍ” የአረብኛ ቃል አይደለም ከግዕዝ ውጭ በሌላ ቋንቋ ውስጥም አይገኝም። እስልምና ቃሉን የወሰደው ከግዕዝ ነው። ሙስሊሞች ግን ቁርአን ከአላህ በወረደ በጥንታዊው ንጹሕ አረብኛ ቋንቋ ነው ሙሉ በሙሉ የተጻፈውይላሉ። ይህ ክስተት ብቻ የእስልምናን እምነት በዜሮ ያባዘዋል!

ከሁሉም በላይ ደግሞ አዲሱን እምነቱን እንዳያስፋፋ በመካና በመዲና ተቃውሞ ሲያጋጥመውና በዳሩል ናድዋ የተሰበሰቡት የቁሬሺ ጎሳ ባላንጣዎቹ ተከታዮቹን ሊገድሉ ሲያሳድዷቸው ፥ መሀመድ ለተከታዮቹ፣ “ፍትህን ሳያጓድል የሚያስተዳድር ደግ ንጉሥ በእውነት ምድር በሐበሻ አገር ይገኛልና ወደ እርሱ ሂዱ። ያስጠጋችኋል።”[5] አላቸው። ተከታዮቹም ወደ አክሱም ተሰደዱ። ንጉሠ ነገሥቱም ተቀብለው አስትናገዷቸው። እዚህ ላይ ትኩረት የሚያስፈልገው “የሐበሻው” ንጉሥ ደግ መሆናቸውን ማን ነገረው? ፍትሕን ሳያጓድሉ የሚፈርዱ መሆናቸውንስ እንዴት አወቀ? የሚለው ጥያቄ ነው። ከአይሁድ ወይም ከግሪክ ወይም ከፋርስ ወደ አረብ አገር የሚመጡ ሰዎች ስለ “የሐበሻ” ንጉሥ ደግነት ሊነግሩት አይችሉም። ስለ ኢትዮጵያ ንጉሥ ደግነት ለመሀመድ ሊነግሩ የሚችሉት ከኢትዮጵያ ወደ አረቦች ሠፈር የሄዱ ኢትዮጵያዊ የክርስትና ተከታዮች ወይም የወንጌል መምህራን ናቸው። እንግዲህ እነዚህ መረጃዎች የሚያሳዩት መሀመድ እስልምናን ለወገኖቹ ለመስበክ መነሻ የሚሆነውን ትምህርት ያገኘው ከኢትዮጵያውያን መሆኑን ነው።

የመሀመድ ተከታዮች አክሱም እንደደረሱ መልካም መስተንግዶ እንደተደረገላቸው የአረብ ተራኪዎች እራሳቸው ዘወትር ይመሰክራሉ። በተለይም ደግሞ ቁሬሺ የሚባሉት የመሀመድ ተቃዋሚዎች አክሱም ድረስ ለንጉሠ ነገሥቱ እጅ መንሻ ይዘው በመምጣት በሽሽት የመጡት የመሀመድ ተከታዮች ወንጀለኞች ናቸውና ስጡን፣ ወደ አረብ አገር መልሰን እንውሰዳቸው ብለው ሲጠይቋቸው ንጉሠ ነገሥቱ የሁለቱንም ወገን ቃል ካዳመጡ በኋላ ስደተኞቹን አሳልፌ አልሰጥም ማለታቸው እስካሁን ይነገራል። እነዚህ የመሀመድ ተከታዮች የሆኑ ስደተኞች ወደ አረቦች አገር ቢመለሱ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ያዩት ነጉሠ ነገሥቱ ስደተኞቹ በሂመራ (የመን) እንዲሠፍሩና እንዲኖሩ ፈቀዱላቸው። አሁንም እዚህ ላይ ከላይ የተጠቀሱት ነዳጅ ፈላጊ ሃሰተኛ ምዕራባዊ ተራኪዎችና አይሁድ ነን ባዮች ከእስልምና በፊት የመንን ፋርሶች አጥቅተው ይዘዋት ነበር የሚል ሃሰት ይተርካሉ። ከነሱ የሃሰት ትረካ ሌላ እነሱ ለሚሉት ነገር ጭብጥ ማስረጃ የለም። የመን የኢትዮጵያውያን ምድር እንደነበርችና በውስጧም ከኢትዮጵያውያን በቀር አረብ የሚባል ጎሳ እንዳልነበረባት፣ አረብኛ ቋንቋም እንዳልተነገረባት ይልቁንስ የሂመራ ሰዎች የሚናገሩት ቋንቋ፣ የሚጽፉትም ጽሁፍ ግዕዝ እንደነበረ፣ ባህላቸውም “የሐበሻ” እንደነበረ የሚያረጋግጡ በጣም በርካታ ማስረጃዎች አሉ። የመሀመድ ተከታዮች በኢትዮጵያ ከተሰደዱ በኋላ ጊዜው ሲረጋጋ አንዳንዶቹ እየተመለሱ እስልምናን አስፋፉ። ከሞት አፋፍ ላይ ደርሶ የነበረው እስልምና በኢትዮጵያው ንጉሥ ደግነት ምክንያት እንደገና አንሰራራ።

እንግዲህ ይህን የመሰለ መስተንግዶ የተደረገላቸው አረቦች ግን እስልምናቸውን ሲያስፋፉም ሆነ ሲገድሉ፣ በመሬት ንጥቂያም ላይ ሲሰማሩ ርኅራኄ ያደረገችላቸውን ኢትዮጵያ በርኅራኄ አይን አይተዋት አያውቁም። ብዙ አረቦች “ኢትዮጵያ ስላስጠጋቻችሁ እሷን አትንኩ” ብሎ መሀመድ ተናግሯል ሲሉ ይደመጣሉ። ይሁንና ከእስልምና በኋላ አረቦች ኢትዮጵያን ሳይነኩ የሰነበቱበት ዘመን የለም። ከእስልምና ማንሰራራት በኋላ ኢትዮጵያ በእስልምና የደረሰባትን ውድቀት ሲመለከቱ ንጉሠ ነገሥቱ ለነዛ ለተሰደዱ አረቦች ያደረጉላቸው መስተንግዶ ከደግነትም አልፎ የየዋህነት/የሞኝነት/አጠንቅቆ ያለማወቅ እንደነበር አዙሮ ለሚያይ ሁሉ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ንጉሠ ነገሥቱ እጃቸውን ዘርግተው አረቦቹን መቀበላቸው ለኢትዮጵያ ተናዳፊ እባብን እጅ ዘርግቶ እንደመቀበል ነው የሆነባት።

የመንን ወሰዱ። ኢትዮጵያውያንን አረዱ። የቀሩትንም መንገድ ላይ ጣሏቸው።

የየመን አክሃዳሞች ከተደረገላቸው ከዚህ ሁሉ ቸርነት በኋላ አረቦች እስልምናን ለማስፋፋትና የሌሎችን መሬቶች ለመንጠቅ ሲሰማሩ የመጀመሪያ ሰለባ ያደረጉት የኢትዮጵያን አውራጃ ሂመራን (የመንን) መውረርና የራሳቸው ማድረግ ነበር። አረቦች በሂመራ በኢትዮጵያውያን ላይ የሠሩት ግፍ ምዕራባውያን አፍሪካውያንን በባርነት ቀንበር ከገዙበት ግፍ ቢበልጥ እንጂ አያንስም። አረቦች ሂመራን (የመንን) ሲወሩ መጀመሪያ በሰንዓ የሚገኘውን እጅግ የተዋበውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ነበር ያፈረሱት። ክርስቲያኖችንም አረዱ። የቀሩትን ኢትዮጵያውያን አስገድደው አሰለሟቸው። በባርነትም ገዟቸው። የመንንም አጥለቀለቋት። እጅግ የሚዘገንኑ ግፎችንም በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጸሙባቸው። ልጆቻቸው ታሪካቸውን እንዳያውቁ አደነቆሯቸው። የሚበሉት፣ የሚጠጡትና የሚለብሱትም አሳጧቸው። አክሃዳም (ጠራጊወች) የሚል ስምም አወጡላቸው። አክሃዳሞች ከሽንት መጥረግና ከጫማ ማጽዳት ውጭ ሌላ ሥራ አይፈቀድላቸውም፡፤ ልጆቻቸውም አይማሩም። አረቦች “እቃህን ውሻ ቢነካው እጠበው፤ አክሃዳም ከነካው ግን ጣለው” የሚል ፈሊጥ አውጡ። አረቦች አክሃዳም እያሉ የሚጠሯቸውን ሥራና ትምህርት ብቻ ሳይሆን የከለከሏቸው ሰው መሆንን ጭምር ነው።

ከየመን ወረራ በኋላ አረቦች እስልምናን በማንገብ የሌሎች ሰዎችን መሬቶች ለመንጠቅ ወደ ሰሜን አፍሪካ፣ ወደ መካከለኛው ምስራቅና ወደ ፋርስ ዘመቱ። የተከላከሏቸውን በጎራዴ እያረዱ ገደሉ፣ የቀሩትን እስላም አደረጓቸው፣ መሬታቸውንም ሁሉ ወሰዱ። በተለይ ጥቁሮችን በማጥፋት ከሲሶ በላይ የሚሆነውን የአፍሪካ መልክአ ምድር በንጥቂያ ወሰዱ። ኢትዮጵያን በዙሪያዋ ከበቧት። በግድም በውድም ብዙ ኢትዮጵያውያንን አሰለሙ። በዳር ድንበርም በማህል አገርም ያሉ ኢትዮጵያውያንን ካሰለሙም በኋላ የክርስቲያን መንግሥት ስለሆነ ለመካከለኛው መንግሥት አትገዙ፣ ጎጦቻችሁንም ከመካከለኛው መንግሥት ገንጥሉ የሚሉ ፋትዋዎችን በመደንገግ ሙስሊም የሆኑትን ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ላይ ለጦርነት በማነሳሳት ኢትዮጵያን በአመጽ ለብዙ መቶ ዓመታት አስጨነቁ። የባህር በሮቿንም ያዙ።

አረቦች ቢዛንቲያ/ ቆስጠንጥኒያ ተብሎ የሚጠራውን አገር በንጥቂያ ከወሰዱ በኋላ ኦስማንየ የሚባል የቱርክ የእስልምና መንግሥት ተቋቁሞ እሱም በመስፋፋትና እስልምናን በማስፋፋት ብዙ የዓለም ክፍሎችን ይቆጣጠር ጀመር። ኦስማንየ የተባለው የእስልምና ቀንበር ጫኝ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን መሣሪያ በማስታጠቅ ኢትዮጵያን ለብዙ አመታት በአመጽና በጦርነት አደቀቁ። በተለይም አህመድ ግራኝ በመባል የሚታወቀውን ሙስሊም በማስታጠቅ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ በጦርነት አመሷት። አብያተ ከርስቲያናትን አወደሙ። ቅዱሳን መጻሕፍትን አቃጠሉ። ካህናትን እና ምእመናንን አረዱ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የአረብ ስደተኞችን ካስተናገዱ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በችግር፣ በጦርነትና በሰላም ማሳጣት አረቦች እንዳመጡት እስልምና ኢትዮጵያን ያዎካት የለም። የአረቦች እስልምና አዋኪነቱ በማበጣበጥ ብቻ የተገታ አይደለም። ታሪክንም በመበረዝ ጭምር ነው።

በተለይ ባለፉት ሃምሳ አመታት በአረባዊው በግብጽ መንግሥትና ካይሮ በሚገኘው የዓለም ሙስሊሞች እንዲከተሉት የእስልምና መመሪያ ወይም ፋትዋ ማፍለቂያ ማእከል በሆነው በአልአዛር ተቋም አበረታችነት በኢትዮጵያ የተኪያሄዱት ሁከቶች ኢትዮጵያን ትልቅ አደጋ ላይ የጣሉ ነበሩ። ይህ የአረቦች የአመጽ ጥንስስ በኢትዮጵያ ብዙ ደም ካፈሰሰ በኋላ “ኤርትራ” ተብላ የምትጠራውን የኢትዮጵያ አካል ከነነዋሪዎቿ ከኢትዮጵያ ገንጥሏል። በእስልምና ስም የሚመጣው የአረቦች የብጥብጥ እርሾ በሰሜን፣ በማሀል አገር፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ ወዘተ እስካሁን ድረስ ጥፋቱን እንደቀጠለ ነው።

አረቦች እስልምናን ተጠቅመው በሚፈጥሩት ሁከት ምክንያት ኢትዮጵያ በመታመሷና ድህነትም ላይ በመውደቋ በተለይ ባለፉት አርባ አመታት ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ኢትዮጵያን ትተው በመሰደድ በተለያዩ የዓለም አገሮች ተበታትነዋል። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ወደ አረቦች አገር ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተሰድደው በዛ እስከ አሁን ይኖራሉ። ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም በታህሳስ ወር ፪፲፻፬ ዓ.. ሰላሳ አምስት የሚሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን የክርስቶስን ልደት በቤታቸው ተሰብስበው ስላከበሩ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት እነዚህን ክርስቲያኖች በእሥራትና በድብደባ ካንገላታቸው በኋላ ክሳዑዲ አረቢያ አባሯቸዋል። አረቦች የመጀመሪያው ሂጅራ እያሉ በሚያስታውሱት ስደታቸው ከአረብ አገር ተሰድደው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢትዮጵያውያን ላደረጉላቸው አቀባበል፣ የተሰደዱትንም ችግር እንዳያገኛቸው በኢትዮጵያ እንዲኖሩ መልካም መኖሪያ ለሰጧቸው ኢትዮጵያውያን የከፈሉት ውለታ እነሆ ኢትዮጵያውያን በአረቢያ በተሰደዱ ጊዜ ዱላ፣ እሥራትና ካገር ማባረር ሆነ። ዛሬም እንደትናንትናው አረቦች ኢትዮጵያውያንን የማጥቃትና የማዋረድ ሥራቸውን ቀጥለውበታል። በተለይ ሰሞኑን በሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን እያሳደዱ በመያዝ እየደበደቡ አጉረዋቸዋል። አንዳንዶችንም ገድለዋቸዋል። ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከቤታቸው እያወጡ አስራ አምስት እና ሃያ እየሆኑ ሰብአዊነት በሌለው ሰይጣናዊ ሁኔታ ደፍረዋቸዋል። ከቤታቸውም ከተሰደዱበትም ቦታ እያወጡ ጥለዋቸዋል። የርኅራኄ መስተንግዶ የተደረገላት ቄዳር ግፍን መለሰች። በቄዳር ድንኳኖች ውስጥ ያላችሁት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችሁ ተመልከቱ። ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍስ ብዙ ጌዜ ኖረች። ኢትዮጵያ ማረፊያ ሰጥታ ሰላምን ለቄዳር ልጆች ሰጠች፣ የቄዳር ልጆች ግን ስላምን ነሷት። መኖርያቸው ለራቀ፣ በቄዳር ድንኳኖች ላደሩ ወዮ፥ እግዚአብሔር ተናግሯልና እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋልና።

✞✞✞መድኃኔ ዓለም የተመሰገነ ይሁን።✞✞✞

💭 ፀረ-ክርስቶስ ቱርክ ጥንታዊውን የቅድስት ሶፊያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን መስጊድ ልታደርገው ነው

ዛሬ የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመን ደግሞ ከመጭው 15 ሐምሌ ጀምሮ ይህን ታሪካዊ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ መስጊድ በማድረግ እስላሞች ገብተው እንዲሰግዱ እንደሚደረግ ነው።

የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ ኮሮና አልበቃ ብሏት በቅድስት ሶፊያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰሞኑን በድፍረት የአዛን ጋኔን እየለቀቀች ነው። በሃገራችንም እየተሠራ ያለው ይህ ነው። ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ መስጊድ የሚገነቡት ያለ ምክኒያት አይደለም፤ ክርስትናን መዋጋትና ለማጥፋት መታገል የመሀመዳውያኑ አምልኮታዊና ታሪካዊ ግዴታ ነውና። ነቀርሳ ጤናማውን ህዋሳታችንን ካላጠቃ እራሱን በልቶ ይሞታል።

ዓለም በኮሮና ቫይረስ ተናውጣልች፤ በቱርክም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ይታወቀል (ኤርዶጋን ደብቆታል)፤ በክርስቶስና ልጆቹ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው ሸሆችና ኢማሞች ግን በክርስቲያኖች ቁስል ላይ ጨው ለመጨመር እዚህ ታሪካዊ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ውስጥ ገብተው አስቀያሚውን የአዛን ጩኸት ያሰማሉ። አቤት ድፍረት! አቤት ቅሌት! ቱርክ መጥፊያዋ ተቃርቧል! እርኩሶች! ልሳናቸው ይዘጋባቸው!

ሌላ የሚገርመው፤ ልከ የኮሮና ቫይረስ በቻይና መቀስቀሱ እንደተሰማ ቱርክ በሃገሯ የሚገኙትን በሚሊየን የሚቆጠሩና “ስደተኞች” የተባሉትን መሀመዳውያን ወራሪዎችን ወደ ኦርቶዶክስ ግሪክ በጉልበት ለማስገባት መወሰኗ ነው።

የክርስቲያኖች ዋና ከተማ የክርስቲያኑ ንጉሥ የቆስጠንጢኖስን ሀገር የነበረችውን የዛሬዋን ቱርክ በአጭር ጊዜ ተቆጣጠረ። የቅድስት ሀጊያ ሶፊያንም ቤተመቅደስ ተቆጣጥሮ መስጊድ አደረገው።

ቱርክ የአውሮጳ ኅብረት አባል ለመሆን ጥያቄ ባቀረበች ጊዜ ከመስፈርቶቹ አንዱ የክርስቲያኖች ንብረት የነበረውን አስደናቂውን የሀጊያ ሶፍያ ቤተመቅደስ ከመስጊድነት ወደ ቤተመቅደስነት ለክርስቲያኖች እንድታስተላልፍ ነበር የተጠየቀችው ይባላል። ነገር ግን የቱርክ መንግሥት ቤተመቅደሱን ለክርስቲያኖች አልመልስም። መሥጊድ መሆኑንም አስቀርቼ የሚጎበኝ ሙዚየም አደረገዋለሁ ባለው መሠረት አሁን የቅድስት ሀጊያ ሶፊያ ካቴድራል መስጊድ መሆኑ ቀርቶ ሙዚየም ሆኖ ይጎበኛል። በነገራችን ላይ ክቡ አጼ ኃይለሥላሴ ያሠሩት የአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ህንጻ ዲዛይን በቀጥታ በቱርክ ኢስጣንቡል ከሚገኘው ከቅድስት ሀጊያ ሶፊያ ቤተክርስቲያን የተቀዳ ነው።

እናስታውስ፤ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ቀዳማዊ ግራኝ አህመድን አሰማርታ አባቶቻችን ካህናትን፣ ምዕመናንን ስታሳርድ፣ ዓብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥልና ስትዘርፍ የነበረችው ቱርክ ናት ፣ ዛሬም ከቱርክ ድጋፍ በማግኘት ላይ ያለው የዳግማዊ ግራኝ አህመድ አሊ ኦሮሞ ሠራዊት ተመሳሳይ ተግባር በመፈጸም ላይ ነው። የሚገርም አይደልም? እነዚህ ከሃዲዎችም ልክ እንደ ቱርክ የኮሮና ቫይረሰን መስፋፋት ተገን አድርገው በድፍረትና በንቀት ክርስቲያኖችን በመተናኮል ላይ ናቸው።

እ.አ.አ (532-537)በንጉሠ ነገሥት ዮስጢያኖስ የተመሠረተውና “ሀጊያ ሶፊያ” ወይም “ቅድስት ጥበብ” በሚለው የመድኃኔዓለም ስሙ የተሰየመው ይህ የእግዚአብሔር ወልድ ቤተ ክርስቲያን በቁስጥንጥንያ መንበር ታላቁ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን እጅግ አስደናቂ የሕንጻ ጥበብ የታየበትና የብዙ ቅዱሳን አጽም ያረፈት ታላቅ ካቴድራል ነበረ። በኦርቶዶክሳዊያንና በዓለም የክርስትና ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሥፍራ ያለውና በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የዓለም ቅርሶች አንዱ የሆነው ይህ ቤተ ክርስቲያን በ1453 ዓ ም ቁስጥንጥንያ፡ ያሁና ኢስታምቡል፡ በኦቶማን ቱርክ እጅ ስትወድቅ በሱልጣን መሀመድ ዳግማዊ ትእዛዝ ወደ መስጊድነት ተቀይሯል። ከ1935 ዓ ም እስከ ዛሬም ድረስ ደግሞ ወደ ቤተ–መዘክርነት ተቀይሮ የቀደመ ታሪኩ ብቻ እየተነገረ ለጎብኚ ክፍት ሆኖ ይገኛል። አሁን እብዱ የቱርክ ፕሬዚደንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በሙስሊም ወንድሞቹ ግፊት ይህን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን መስጊድ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው አውስቷል።

የክርስቲያን ሃገራትን በመውረር እስካሁን ድርስ ይዛ የቆየችው የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ መጥፊያዋ ተቃርቧል፤ ቁስጥንጥንያንም ለግሪኮችና አርመኖች በቅርቡ ትመልስ ዘንድ ትገደዳልች፤ ስልዚህ በጣም ያቁነጠንጣታል ያለው። እንደ እኛዎቹ ሁሉንም ነገር “ኬኛ” ትላለች። አውሮፓ የእኔ ነው፣ ሰሜን አፍሪቃ የእኔ ነው ትላለች። እንዲያውም “አሜሪካን እኛ ቱርኮች ነን ያገኘነው” በማለት እብዱ ኤርዶጋን በቅርቡ ቀለባብዶ ነበር። “ኬኛ” የመሀመዳውያን መንፍስ እንደሆነ እያየን ነው?

የሀጊያ ሶፊያ ቤተክርስቲያን ወደ ቀደመ ክብሩ መመለስ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኦርቶዶክስ ምእመናን ታላቅ ደስታ የሚሆን ነው። በዓለም ዙሪያ ብዙ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በሀጊያ ሶፊያ ቤተክርስቲያን ሕንጻ አምሳል መሠራታቸውም ለቤተክርስቲያኑ የሠጡትን ትልቅ ሥፍራ የሚያስረዳ ነው። ሀጊያ ሶፊያን መስለው ከተሠሩ ቤተክርስቲያኖች መካከል በግብጽ ካይሮ የሚገኘው የዘይቱን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንና በኢትዮጵያ የሚገኘው የርእሰ አድባራት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ይጠቀሳሉ። በቱርክ እና ግብጽ የሚገኙት ሙስሊሞችም አብዛኛዎቹን መስጊዶቻቸውን ከዚህ ድንቅ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ኮርጀው ነው የሠሯቸው።

ቀድሞ ቁስጥንጥንያ ዛሬ ደግሞ ኢስታንቡል በመባል የምትታወቀው የግሪኮችና አርመኖች ከተማ ስሟን ያገኘችው „εἰς τὴν πόλιν“ „is tim boli (n)„ ከሚለው የግሪክኛ ቃል ነው። “ከተማው” ወይም “በከተማው” ማለት ነው፤ ለቁስጥንጥንያ። የኦርቶዶክስ ጠላት የሆኑት ቱርኮች ግሪክ ኦርቶዶክሶችን የጎዱ ስለመሰላቸው ነበር ቁስጥንጥንያን ኢስታንቡል ብለው የሰየሙት። ልከ በአገራችንም ከሃዲዎቹ የዋቄዮ አላህ ልጆች ኦርቶድክስ ኢትዮጵያን ያሸነፉ መስሎ ስለታያቸው አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” ብለው ለመጥራት ይታገላሉ፤ ግን ፊንፊኔ የአማርኛ ቃል መሆኑን አላወቁም ነበር።

💭 ኦርቶዶክስ አገራት ብሔራዊ የሀዘን ቀን አወጁ

ሰዶማውያኑ ቱርኮች የቅድስት ሶፊያን ቤተ ክርስቲያን መስጊድ በማድረጋቸው።

ከስድስት መቶ ዓመታት በፊት ሰዶማውያኑ ቱርኮች የኮኒስታንቲኖፕልን ከተማ ወርረው ሲይዙ በዚህ ታሪካዊ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ውስጥ በጣም ብዙ ዲያቆናት፣ ካህናት ፣ ቀሳውስትና ጳጳሳት ምዕመናቱ ፊት በግፍ ታርደው ለሰማዕትነት በቅተዋል። ዛሬም ቱርኮች እጅግ በጣም ይቅበዘበዛሉ፤ ቤተክርስቲያኑን መስጊድ ያደርጋሉ፤ ወታደሮቻቸውን ወደ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ሰሜን ቆጵሮስ፣ ካታር፣ አዘርቤጃን ወዘተ ይልካሉ፤ ለዳግማዊ ግራኝ አህመድና ኦሮሚያ ለተባለው ህገ-ወጥ ክልል መሣሪያዎችን በድብቅ ያቀብላሉ። በሃገራችን እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ የቱርኮችና አረቦች ድጋፍ አለው!

የተዋሕዶ ልጆች፤ “ቤተሰብ ሜዲያ፣ አደባባይ ሜዲያ፣ ዘመድኩን በቀለ” እነዚህ ከሃዲዎች ለኦሮሙማ ፕሮጀክት የሚሰሩ ከሃዲዎች ናቸው፤ ገንዘባችሁን፣ ጊዜያችሁን እና አትኩሮታችሁን አትስጧቸው! እንዳትቆጩ፤ በቅርብ የምታዩት ነው!

አማራ” ነን የሚሉ ሜዲያዎች እየተገደለ ላለው ወገኑ መቆም ሲገባቸው ለሚገላቸው ግራኝ አብዮት አህመድ ወግነው ሌላውን ወገናቸውን በጅምላ ያስጨፈጭፋሉ። ስለጽዮን ዝም ያሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው።

መልዕክቱን የሚያጅቡት ምስሎች ላይ የተቀመጡት ሜዲያዎች/ዩቲውብ ቻነሎች በአሁኑ ሰዓት ጭንብላቸውን በመግለጥ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን አሳውቅውናል። ያሳዝናል፤ ስላወቅን ግን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! እያንዳንዷ ቀን የፈተና ቀን ናት፤ በተለይ ለአማራ ኢትዮጵያውያን፤ ምክኒያቱም፤ ሌላ ጊዜ የምመለስበት በጣም ቁልፍ የሆነ ርዕስ ነው፤ ዲቃላዎቹ ጋላማራዎች ብዙ ድራማ እየሠሩና ዥዋዥዌ እየተጫወቱ አማራ ኢትዮጵያውያንን ከጽዮን ለመነጠል በሁሉም አቅጣጫ ብዙ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸውና ነው።

የየዋሁን መንጋቸውን ማንነትና ምንነት ለመቀየር የተጠቀሱት ሜዲያዎች በጣም የተራቀቀ ዲያብሎሳዊ ሥራ እየሠሩ ነው፤ አንዴ ቀዝቃዛ ውሃ፣ ሌላ ጊዜ ሙቅ ውሃ፣ አንዴ ሃዘን ሌላ ጊዜ ደስታበመስጠት ብሎም አንዴ ተቃዋሚ፣ ሌላ ጊዜ ደጋፊ ሆነው በመምጣት የነፍስ እደና ዘመቻ ነው የተያያዙት ብል አላጋነንኩም። ብዙ ጊዜ የምንሰማው ነው፤ “አብዮት አህመድ ጥሩ ሲሰራ እናመሰግነዋለን፣ መጥፎ ሲሰራ እንወቅሰዋለን!” የሚል ተልካሻ አቋም በመያዝ መሰራት ከሚገባው ሥራ ብዙውን በማዘናጋት ላይ ናቸው። ዲያብሎስም እኮ ብዙ በጎ ነገሮችን ይሠራል፤ አይደል እንዴ? ለክርስቶስ እኮ ዓለምን ሁሉ ላውርስህ”ብሎት ነበር።

✞✞✞ [የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፬፥፰፡፲] ✞✞✞

ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ። ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።”

***በፍሬዎቻቸው ይታወቃሉ***

በዘመነ ወረርሽኝ፣ ወገን በተቀሩት የሃገራችን ክፍሎች እንደ ዝንብ በሚረግፉበት፣ ዓለም ከፍተኛ የኢኮኖሚና ማሕበረሰባዊ ቀውስ ውስጥ በገባችበት በዚህ አስከፊ ወቅት፤ ወደ እግዚአብሔር እጆቻችንን ዘርግተን እንደመጮኽ፤ እየገደላቸው ያለውን ገዳያቸውን “እሰየው፣ በለው! ከሰይጣንም ጋር ተሰለፌ ትግሬዎችን እዋጋለሁ፣ አስደሳች ድል! ቅብርጥሴ” የጦርነት ከበሮ እየመቱ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ያሉት ግብዞች ሊውጣቸውን ሊሰለቅጣቸው የጓጓውን ዘንዶ እየቀለቡት እንደሆነ እንዴት መረዳት ተሳናቸው? አባቶቻችን የወንድማቸው ደም ሲበቀሉ ነበር የሚፎክሩት ይህ ግራ የተጋባ ትውልድ ግን ወንድሙን ገድሎ ይፎክራል፤ ይህን ያህል ጥላቻ ለትግሬ ወገናቸው! አባታቻን አባ ዘወንጌል ካስጠነቀቁን ነገሮች መካከል “ባስከፊው በዚህ ጊዜ ፀረትግሬ የሆነ አቋም እንዳይኖረን” ነው። ለእኔ ወገኑን ለመውጋት ጦርነት ካወጀው ቆሻሻው ግራኝ አብዮት ይልቅ እነዚህ ውዳቂዎች ናቸው በይበልጥ የከፉት የኢትዮጵያ ጡት ነካሾች!

ስለዚህ የጽዮንን ተራሮች በጭራሽ አምባና መሸሸጊያ አይሆኗቸውም፤ ከዝርዝሩ ተወግደዋል/ተሠርዘዋልና!

✞✞✞ [መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፰፥፴፡፴፩] ✞✞✞

በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፤ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው። መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”

_____________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: