Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2021
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 29th, 2021

ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 29, 2021

ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ፤ የሰማዕታት ሁሉ አለቃ እንደመሆንህ ቀድሞ ሰብዓ ነገሥታትን እንደ ደመሰስካቸው ነበልባላዊ በምትሆን ጸሎትህ የጽዮንን ጠላቶች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊና የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮቹን ሁሉ ደምስሳቸው፤ እንደ አመድ በነው እንደ ጢስ ተነው ይጥፉ። አሜን፤ ወአሜን! ይሁን፤ ይሁን!

ይሄን እኮ ነው ዛሬ በሃገራችን እያየንና እየሰማን ያለነው። ከትንሹ እስከ ትልቁ፣ ከወጣቱ እስከ ሽማግሌው፣ ከሴቱ እስከ ወንዱ፣ ከዶ/ሩ እከ ፓስተሩ ሁሉም ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፣ በምላሳቸው ይሸነግላሉ፣ የአባቶቻቸውንና እናቶቻቸውን፣ የወንድሞቻቸውንና እኅቶቻቸውን ደም ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው። ከአህዛብ እና መናፍቃንስ አንጠብቅም፤ ግን “ተዋሕዷውያን ነን! ኢትዮጵያውያን ነን!“ ከሚሉት ወገኖች መካከል፡፤ “ከአህዛብ እና መናፍቃን እንዲሁም ታሪካዊ ባዕዳን ጠላቶቻችን ጋር ሕብረት አይኑረን፤ ጦርነት አያስፈልግም፣ ያውም ክርስቲያን የሆኑትን አክሱም ጽዮናውያንን በረሃብና በጥሜት ለመቅጣት መንገድ መዝጋት፣ እርዳታ መከልከል፣ አጽዋትና ሰብል ማውደም፣ ውሃ መበከል፣ እንስሶችን ሳይቀር መጨፍጨፍ እጅግ በጣም ከባድ ኃጢዓት ነው፣ እግዚአብሔርን በጣም የሚያስቀይም ሥራ ነው፤ በቃ!ደም መፋሰስ ይቁም!” የሚል አንድ ካህን፣ አንድ ቄስ፣ አንድ መምህር ስንኳ እንዴት ይጥፋ?! የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንደ እንጀራ እንደሚበሉ እና ከባድ ኃጢአትም እንደሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን?

ቅዱስ ቃሉ እኮ እንዲ ብሎናል፤

ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም። ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፩]✞✞✞

አቤቱ፥ አድነኝ፤ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።

እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።

የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ፤

ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።

ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር። አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።

በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።

አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።

በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫]✞✞✞

ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።

የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።

ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።

ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤

ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤

ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።

ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።

በዚያ በታላቅ ፍርሃት እጅግ ፈሩ፥ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና።

የድሆችን ምክር አሳፈራችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው።

ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ አድባራት

እስራኤል

ጆርጂያ

ሩሲያ

_________________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: