ከንጉሡ አብረው የሚገለጡ የኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው የሚሾሙት አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ናቸው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 19, 2021
❖❖❖ ተስዐቱ ቅዱሳን ❖❖❖
ከሮማ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ፃድቃናት ሶስት የተሰወሩ ናቸው፡፡ ከሶስቱም አንዱ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ናቸው። አባታችን አቡነ አረጋዊ የአቡነ ገሪማ የእህት ልጃቸው ናቸው።
ከተስዐቱ ቅዱሳንም በዕደሜ ያነሱ ነበሩ። ነገር ግን የሚናገሩትና የሚሰሩትም ሁሉ አብሯዋቸው ለነበሩ ሌሎች ቅዱሳን የሚያስገርም ነበር።
አባታችን አቡነ አረጋዊ የመጀመርያ ስማቸው ዘሚካኤል ነበር። የሚሰሩትም ሆነ የሚናገሩት ሁሉ ያስገረማቸው አጎታቸው አቢነ ገሪማ “አረጋዊ” “አረግከነ” ሲሉ ጠሩዋቸው።
አረጋዊ ማለት አረግከነ ከሚል የግእዝ ቋንቋ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም አንተ ከእኛ በእድሜ ያነስክ ነህ ነገር ግን በምታደረገው ሁሉ ከእኛ በላይ ታላቅ ሰው ነህ ማለት ነው።
ከንጉሱ አብረው የሚገለጡ የኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው የሚሾሙም አባታችን አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ናቸው፡፡ በመጨረሻ ዘመንም አባታችን አቡነ አረጋዊ በሀሳዊ መሲሁ ተሰይፈው ሞትን ይቀምሳሉ።
❖❖❖ የአባታችን አቡነ አረጋዊ በረከታቸውና ረዲኤታቸው ከእኛ ይሁን።❖❖❖
_________________________________
Leave a Reply