አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል | ደብረ ታቦር
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 18, 2021
💭 አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ደብረ ታቦር ሰንበት ትምህርት ቤት እንዳሳወቀው፤
ከሁለት ሣምንታት በፊት በዚህ በአንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ደብረ ታቦር ላለፉት ረጅም አመታት ለጸበል አገልግሎት እየተጠቀመበት የሚገኘውን የቅዱስ ሚካኤል እና የቅዱስ ቂርቆስ የጸበል ቦታን ቤተ ክርስቲያን እንተክላለን የሚሉ ግለሰቦች ለ ፳፯/፲፩/፲፫ ዓ.ም ያለ ሰበካ ጉባኤ እና ያለ ምዕመናን እውቅና ታቦት ይዘን እንገባለን ሲሉ ነበር።
የአካባቢው ህብረተሰብ ይህን ጉዳይ በቦታው ተገኝቶ መቃወሙ ተገልጿል።
❖❖❖ለአዕይንቲከ ሚካኤል ሆይ ለሰው ልጅ ይቅርታን ለማስገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልዱ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል። ሚካኤል ሆይ በጠላት ተማርከው ለሚጨነቁትና ለሚሰቃዩት ዋስ ጠበቃቸው አንተ ነህና። በኔ ላይ የሚተበትቡትን የጠላቶቼን የምክር መረብ በጣጥሰህ ጣልልኝ ነፍሴንም ሥጋዬንም ለአንተ አደራ ሰጥቻለሁና።❖❖❖
________________________________________
Leave a Reply