ቡሄ | ቅ/ሚካኤል እና ጽዮናውያን ለደብረ ታቦር ደረሱላት ፥ ይብላን ለናዝሬትና ለደብረ ዘይት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 17, 2021
አዎ! እራሳቸውን ወደ ክርስቶስ ተቃዋሚው ጎራ ለመመደብ በመወሰናቸው፤ “ናዝሬትን”፣ ‘አዳማ’ ፥ “ደብረ ዘይትን” ቢሸፍቱ በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መጠሪያዎቻቸውን በክህደት ለመቀየር ደፍረዋል/ፈልገዋል።
✞✞✞በዚህ ወቅት እድለኛዋና ጥንታዊቷ ደብረ ታቦር ከዋቄዮ–አላህ ባርነት ነፃ ወጣች። ✞✞✞
😊 በአጋጣሚ? 😊
❖ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል❖
💭 ገና ከስምንት ዓመታት በፊት የሚከተለውን በጦማሬ ጽፌ ነበር፤
መጠሪያ ስሞቻችን፣ የክርስትና ስሞቻችን ወይም ክርስቲያናዊ የሆኑ የቦታ ስሞችን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ገናናነት ለማሳወቅ፡ ለእርሱ ክብር ለመስጠት የምንሰይማቸው ቦታዎች ወይም ከተሞች በርሱ ዘንድ ከፍተኛ ትርጕም አላቸው፤ ለኛም ሰላምን፣ ጽድቅንና በረከትን ያመጡልናል። ሶማሊያዎች እስከ ናዝሬት ከተማ ድረስ ያለው ግዛት የኛ ነው በማለት በህልማቸው የነደፉትን ካርታ ጥገኝነቱን ለሰጣቸው እንግዳ ተቀባይ የአዲስ አበባ ነዋሪ በድፍረት/በንቀት ያሳያሉ። ይህን በቅርብ ሆኜ ለመታዘብ በቅቻለሁ። ለመሆኑ በፊት ጂጂጋ ደርሰው “ናዝሬት” ዘው ለማለት ያቃታቸው ለምን ይመስለናል? “ናዝሬት” “እየሩሳሌም“፡ የእነዚህ ቦታዎች መጠሪያ ሁልጊዜ የጦርነት ወኔያቸውን ይቀሰቅሰዋል፡ ለምን? መልሱን ሁላችንም እናውቀዋለን።
ታዲያ ሁለት ሺህ ዓመታት በሞሉት የክርስትና ታሪካችን፡ ብዛት ያላቸው ምሳሌዎችን ለማየት እየበቃን፡ እንደ “ደብረ ዘይት” የመሳሰሉትን የቦታ መጠሪያዎች በዘፈቃድ ለመለወጥ የሚሹ ግለሰቦች በምን ተዓምር አሁን ሊመጡብን ቻሉ? ከተራራው በረሃውን፥ ከቅቤው ቤንዚኑን፥ ከደብረ ዘይት የመኪና ዘይትን የሚመርጥ ትውልድ፡ የመቅሰፍት ምንጭ አይሆንብንምን? መቼም ለክርስቶስ ጥላቻ ያላቸው፣ ጸረ–ክርስቶስ የሉሲፈር ፈቃደኛ ወኪሎች ካልሆኑ በቀር እዚህ ድረስ ሊያደርሳቸው የሚችል ሌላ ነገር ሊኖር ይችላልን? አይመስለኝም! ይህ እንደ ቀላል ነገር ተደርጎ መታየት ያለበት ጉዳይ አይደለም፡ ምክኒያቱም በግለሰቦቹ ላይ ሊመጣባቸው የሚችለው ፍርድ ልክ መንፈስ ቅዱስን የሚያስቀይሙት ግለሰቦች ከሚመጣባቸው ኃይለኛ ፍርድ የሚለይ አይሆንምና፤ የመንፈስ ቅዱስን ክብር ደፍረዋልና!
________________________________________
Leave a Reply