ጥንታዊው ገዳም ሚካኤል እምባ ደብረሲና/ አፅቢ ወምበርታ | ድንቅ ነው፤ አገራችንን አናውቃትም እኮ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 18, 2021
❖❖❖ገዳም ሚካኤል እምባ ደብረሲና/ አፅቢ ወምበርታ ትግራይ❖❖❖
በአራተኛው መቶ ክፍለዘመን በ፫፻፴፰/ 338 ዓ.ም ላይ ቅዳሴ የተጀመረበት ታሪካዊ ገዳም ነው።
💭 ገዳም ሚካኤል እምባ በምስራቅ ትግራይ ወረዳ አፅቢ ወምበርታ ሚካኤል እምባ ቀበሌ የሚገኝ ታሪካዊ ግዙፍ ውቅር ቤተክርስቲያን ገዳም ነው።
ከኣፅቢ ከተማ በ ፲፮/16 ኪሎሜትር አቅራቢያ የሚገኘው ይህ ታሪካዊ ገዳም የተሠራበት ዕለት በትክክል ባይታወቅም፤ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በ፫፻፴፰/338 ዓ.ም ላይ ቅዳሴ የተጀመረበት ገዳም ነው።
❖ በ፫፻፴፰/338 ዓ.ም ላይ ቅዳሴ ተጀመረበት
❖ በዘመነ ነገሥታት አብርሃ ወአፅብሃ እንደተሠራ ይነገራል
❖ ፲፪/12 ጥልቅ ከአለት ተፈልፍለው የተሰሩ የውሃ ጎዳጉዶች አሉ ፣ ሰባቱ ሰውን እንዳይጎዳ ተብሎ ተደፍነዋል ፡ ፭/5የውሃ ጠበሎች አሉ
❖ ፵፬/ 44 ምሶሶዎች ኣሉት
❖ የቅዱስ ሚካኤል በረከት በያልንበት ይድረሰን! እንደ እነ አብርሃ ወአፅብሃ ለእግዚአብሔር አምላክ የሚገዙና የሚታዘዙ ፍትሃዊ መሪዎችን ይስጠን! አሜን! አሜን! አሜን!
✞✞✞[መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮፥፲፪]✞✞✞
“ግፍን መሥራት በንጉሥ ዘንድ ጸያፍ ነገር ነው፥ ዙፋን በጽድቅ ይጸናልና።”
✞✞✞[መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፥፰]✞✞✞
“በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዓይኖቹ ይበትናል።”
✞✞✞[መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ምዕራፍ ፰፥፲፭]✞✞✞
“ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው።”
__________________________________
Leave a Reply