ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 11, 2021
“...በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥ ለሚያጭደው እጁን፥ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።”
💭 አዎ! ኢትዮጵያ ማለት የአዲስ ኪዳኗ እስራኤል ዘ-ነፍስ ማለት ናት። የአክሱም ጽዮንን ልጆች የሚጠሉ ጽዮን ማርያም እናታችንንና ኢትዮጵያንም ይጠላሉ ማለት ነው። ይህም ዛሬ ፺/90% የሚሆኑትን “ኢትዮጵያውያን ነን፣ ክርስቲያን ነን” የሚሉትን ግን ኢትዮጵያውያንም ክርስቲያንም ያልሆኑትን የወደቁትን ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ይመለከታል።
✞ አባታቻን አባ ዘ-ወንጌል ካስጠነቀቁን ነገሮች መካከል፤
❖ ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ መሆናቸውን፤ ስለዚህ እነ አረመኔው ግራኝ የነገሱባት ‘ኢትዮጵያ’ ‘ጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ’ ሳትሆን የዋቄዮ-አላህ ‘ኦሮሚያ’ መሆኗን
❖ በዚህ የፈተና ወቅት ፀረ–ትግራዋይ/ፀረ–ጽዮናውያን የሆነ አቋም እንዳይኖረን
❖ ፲/10% የሚሆኑት ተዋሕዷውያን ብቻ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማየት እንደሚተርፉ
የሚሉት ይገኙበታል። ለሁላችንም በጣም ቁልፍ የሆነ ነጥብ ስለሆነ በደንብ እናስተውል!
💭 ቅዱሱ ነብይ አባታችን ንጉሥ ዳዊትም ይህን ኃይለኛ መልዕክት ነበር ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ያስተላለፈልን፤ ድንቅ ነው!
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፳፰]✞✞✞
፩ እስራኤል። ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ይበል፤
፪ ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።
፫ ኃጢአተኞች በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኃጢአታቸውንም አስረዘሙአት።
፬ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጢአተኞችን አንገታቸውን ቈረጠ።
፭ ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
፮ በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥
፯ ለሚያጭደው እጁን፥ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
፰ በመንገዱም የሚያልፉ። የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም።
💭 ጉብኝት ወደ ፤ ❖❖❖ታላቁ ገዳም ጉንዳ ጉንዶ ማርያም❖❖❖ ፲፬ኛው ምዕተ ዓመት ተመሠረተ
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፳፮]✞✞✞
፩ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
፪ በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ከተቀመጣችሁበት ተነሡ።
፫ እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።
፬ በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፥ የጐልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው።
፭ ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ብፁዕ ሰው ነው፤ ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ እርሱ አያፍርም።
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፳፯]✞✞✞
፩ እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።
፪ የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።
፫ ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።
፬ እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።
፭ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።
፮ የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።
_________________________________
Leave a Reply