Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የሮማው ጳጳስ ከእኛዎቹ በልጠው ለትግራይ ጸሎት ያደርሳሉ | “ረሃብን መታገስ የለብንም!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 13, 2021

💭 የቫቲካን መልዕክት፦

የሁሉንም ህሊና የሚፈታተን አደጋ፤ በትግራይ ያለው የረሃብ ደወል። ፍራንችስኮስ ከአንጀሉስ በኋላ ባደረጉት ሰላምታ በጭፍጨፋው ለተጎዱት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሕዝቦች “ሰላም ለኪ” አቅርበዋል። “ረሃብን መታገስ የለብንም” ብለዋል

Una tragedia che interpella la coscienza di tutti: l’allarme alimentare nel Tigray. Nel saluto post Angelus, Francesco recita un’Ave Maria per la popolazione della regione dell’Etiopia colpita da violenze. L’appello a non tollerare che si muoia di fame.

👉 እንግዲህ ይህ ከG7 ጉባኤ ጋር በተናበበ መልክ የቀረበ መልዕክት መሆኑ ነው። ግን ይሁን እስኪ!

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምነው ጠፉ?

ከዚህ በፊት ኤርትራ ውስጥ ያሉት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካርዲናሎች ኤርትራውያን ከትግራይ ተሰርቀው ወደ ኤርትራ የሚገቡትን ቁሳቁሶች እንዳይገዙ ት ዕዛዝ በማስተላለፍ ከትግራይ ሕዝብ ጋር እንደሚሰለፉ ገልጠው ነበር፤ ያውም በኢሳያስ አፈቆርኪ ግዛት። የኛዎቹስ ሰባት ወራት እንደ ሞእተ ሰው “ጭጭ” ብለዋል።

የአገር ውስጥ ሜዲያዎች ለሆዳቸው ያደሩ ፈሪ ጥንቸሎች ስለሆኑ ይህን ማድረግ እንደማይፈልጉና እንደማይችሉ ግልጽ ነው፤ ግን የውጭ ሜዲያዎች ለምንድን ነው አቡነ ማትያስን ለቃለ መጠይቅ የማይጋብዟቸው? የትግራይ ጉዳይ እኮ አንዴ ብቻ ተነግሮበት በዝምታ የሚታለፍና ቸል የሚባልበት ጉዳይ አይደለም። የቤተ ክህነት ግድየለሽነትና ከግራኝ ጋር ተደማሪነት፣ የኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ብሔሮች ዝምታና ከግራኝ ጋር ተደማሪነት፣ የሜዲያዎች ሽርሙጥና እና ከግራኝ ጋር ተደማሪነት ናቸው ጭፍጨፋው፣ አስገድዶ መድፈሩ፣ ረሃቡና ስደቱ እንዲቀጥል እርዳታ እያደረጉለት ያሉት። እኔ ሁሉንም መጠራጠር ጀምሬአለሁ/ ግዴታየም ነው፤ ከእግዚአብሔር አምላኬ እና ቅዱሳኑ በቀር ከላይ እስከ ታች ማንንም አላምንም! ሁሉም ተናብበው የእግዚአብሔርን ልጆች ለማጥፋት በጋራ እየሠሩ ነው። የትም ዓለም እኮ ታይቶ የማይታወቅ ክስተት ነው ዓለም እየተገነዘበው ያለው። ብጹእነታቸው ከሳምንታት በፊት ከዘመድኩን በቀለ ጋር በስልክ እንዲነጋገሩ በመገደዳቸው/በመደረጋቸው በጣም ነበር ያዘንኩት!

_________________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: