Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ከዋልድባ እንዲሰደዱ የተደረጉት መነኮሳት በምሕላ አክሱም | ይብላኝ ለጎንደር ክርስቲያኖች፤ እዬዬ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 10, 2021

እንደው ለመሆኑ እነዚህን አባቶች ከዋልድባ ለማባረር የደፈረው የትንቢት መፈጸሚያ ማን ይሆን? ለመላዋ ኢትዮጵያ ለመላዋ ዓለም ስራስር እየተመገቡ ጸሎት የሚያደርሱት እነዚህ መነኮሳት ተንገላተው፣ ተደብደበውና ተሳድደው ለረሃብ ሲጋለጡ በእነ ገመድኩን ሰቀለ የጎፈንድሚ የሚሰበሰብላቸው የአማራ “መነኮሳት” እንጀራ እየበሉ በሰላም ሊኖሩ? ምን ዓይነት ጉድ ነው?! ዋይ! ዋይ! ዋይ! በይበልጥ የማዝነው ዛሬ አክሱም እንዲገቡ ለተገደዱት አባቶቻችን ሳይሆን ከዋልድባ ላስወጧቸው ፍጥረታት ነው። እግዚአብሔር በጣም የሚጠላው ተግባር ነውና።

ሌላው በጣም የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ይህን ትልቅ ክስተት ቸል በማለት “መነኮሳት ለምን ከዋልድባ ወጡ?” “እንዲሰደዱ የተደረጉት መነኮሳት ሁኔታስ ምን ላይ ይገኛል?” በማለት ለማሰላሰል፣ ለመጠየቅ እና ክርስቲያናዊ ግዴታውን ለመወጣት ያልቻለው/ያልፈለገው “ኢትዮጵያዊ እና ክርቲያን ነኝ” ባይ ወገን ነው።  በዚህ ወቅት ከዚህ የበለጠና 24/7  ሊነገርለት፣ ሊታሰብለትና መፍትሔ ሊገኝለት የሚገባ ሌላ ጉዳይ ይኖራልን? በፍጹም! ማድረግ ያለበትን ነገር ማድረግ አለመቻሉንና አለመፈለጉን ሳይ “ምን ያህል ልቡ ቢጨልም ነው? እጆቿን ወደ እግዚአብሔር እንደምትዘረጋ ቅዱስ ዳዊት የተነበየላትን ኢትዮጵያ አገራችንን ምን ያህል ቢጠሏት ነው? ” ብዬ እራሴን ደግሜ ደጋግሜ እንድጠይቅ እገደዳለሁ። በመንፈሳዊ ሕይወት የሚገጥመንን ይህን  መሰሉን ተግዳሮት ለመፋለም አለመሞከርና አለመሻት ወደ ጥልቁ የሚያስወርድ ውድቀት  ነውና።

በአማራ፣ በኦሮሞ፣ በቤኒሻንጉል እና በደቡብ ክልሎች ላሉ ክርስቲያን ወንድሞች እና እኅቶች እንባዬን አነባለሁ። ካልረፈደና መማር የምትሹ ከሆነ ትማሩበት ዘንድ ኃይል ከማን ጋር እንደሆነ ታዩት ዘንድ ግድ ይሆናል። እንግዲህ ያው ዛሬ በጌታችን የዕርገት ዕለት የአዲስ አበባውን መስቀል አደባባይን በአህዛብ አስነጠቃችሁት፤ ለምን? ለራሳችሁም፣ ለልጆቻችሁም፣ ለወንድሞቻችሁና እኅቶቻችሁም ለአምላካችሁም መቆም/መኖር ስላቃታችሁ እኮ ነው። አዎ! ለጌታችን ካላችሁ ፍቅር ይልቅ ለትግራዋይ የጽዮን ልጆች ያላችሁ ጥላቻ ጠንክሮባችኋል እኮ፤ እዬዬ! እዬዬ! እዬዬ!

____________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: