Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for June 10th, 2021

Ethiopia | Hunger As a Weapon Facing Famine in Tigray

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 10, 2021

Seven Months of #TigrayGenocide later, Secretary-general of the United Nations Mr. António Manuel de Oliveira Guterres is awake from winter sleep.

✞ They all knew 100% seven months ago a catastrophe is coming, but they didn’t care enough to avoid it through sincere and humane engagement. They They didn’t want to take serious action because they wanted to protect their evil Nobel Laureate darling PM of Ethiopia. Isn’t this the reason why they put him into power – and awarded the Nobel Peace Prize – license for genocide – to him in the first place?

All the parties, all sides in the conflict involved work towards the same goal: the Extermination of ancient Christians of Tigray – It’s a Battle for ‘THE TREE OF LIFE’. The Almighty is watching!✞

👉 USAID will provide enough food to feed three million people, as well as seeds, tools and fertilizers to help farmers replant crops.!

Problem Reaction Solution” for ‘THE TREE OF LIFE‘.

One of the reasons they waited for so long is, because they want to show images of emaciated Ethiopian men, women and children to the world – so that they could blame Russia & China and kick them out of The SC.

Look around, the world immediately stands up with the Muslim Uyghurs of China, Muslim Rohingya of Myanmar and Muslim Palestinians — not with Christians of Syria, Armenia and Tigray. It’s all clear now!

Imagine The worldwide outrage if the 150,000 already dead Tigrayans in this genocide had actually been Palestinian, and the aggressors Israeli Troops.

👉 Now, I’m almost convinced that evil Abiy Ahmed + Isaias Afewerki + Debretsion all work for the UN-Agenda 21- its main aim is to control the world & “reduce” human population. The Almighty God is watching!✞

The UN allowed Afewerki & Ahmed to destroy plantations &Trees The intent of the armies rampaging through Tigray. Their goal is to reduce the Tigrayan people to penury, to grind them down so that “THE TREE of LIFE” can never grow again.

❖“When you besiege a city for a long time, making war against it in order to take it, you shall not destroy its trees by wielding an axe against them. You may eat from them, but you shall not cut them down. Are the trees in the field human, that they should be besieged by you?” [Deuteronomy Chapter 20:19]

________________________________

Posted in Ethiopia, Infos, Life, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከዋልድባ እንዲሰደዱ የተደረጉት መነኮሳት በምሕላ አክሱም | ይብላኝ ለጎንደር ክርስቲያኖች፤ እዬዬ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 10, 2021

እንደው ለመሆኑ እነዚህን አባቶች ከዋልድባ ለማባረር የደፈረው የትንቢት መፈጸሚያ ማን ይሆን? ለመላዋ ኢትዮጵያ ለመላዋ ዓለም ስራስር እየተመገቡ ጸሎት የሚያደርሱት እነዚህ መነኮሳት ተንገላተው፣ ተደብደበውና ተሳድደው ለረሃብ ሲጋለጡ በእነ ገመድኩን ሰቀለ የጎፈንድሚ የሚሰበሰብላቸው የአማራ “መነኮሳት” እንጀራ እየበሉ በሰላም ሊኖሩ? ምን ዓይነት ጉድ ነው?! ዋይ! ዋይ! ዋይ! በይበልጥ የማዝነው ዛሬ አክሱም እንዲገቡ ለተገደዱት አባቶቻችን ሳይሆን ከዋልድባ ላስወጧቸው ፍጥረታት ነው። እግዚአብሔር በጣም የሚጠላው ተግባር ነውና።

ሌላው በጣም የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ይህን ትልቅ ክስተት ቸል በማለት “መነኮሳት ለምን ከዋልድባ ወጡ?” “እንዲሰደዱ የተደረጉት መነኮሳት ሁኔታስ ምን ላይ ይገኛል?” በማለት ለማሰላሰል፣ ለመጠየቅ እና ክርስቲያናዊ ግዴታውን ለመወጣት ያልቻለው/ያልፈለገው “ኢትዮጵያዊ እና ክርቲያን ነኝ” ባይ ወገን ነው።  በዚህ ወቅት ከዚህ የበለጠና 24/7  ሊነገርለት፣ ሊታሰብለትና መፍትሔ ሊገኝለት የሚገባ ሌላ ጉዳይ ይኖራልን? በፍጹም! ማድረግ ያለበትን ነገር ማድረግ አለመቻሉንና አለመፈለጉን ሳይ “ምን ያህል ልቡ ቢጨልም ነው? እጆቿን ወደ እግዚአብሔር እንደምትዘረጋ ቅዱስ ዳዊት የተነበየላትን ኢትዮጵያ አገራችንን ምን ያህል ቢጠሏት ነው? ” ብዬ እራሴን ደግሜ ደጋግሜ እንድጠይቅ እገደዳለሁ። በመንፈሳዊ ሕይወት የሚገጥመንን ይህን  መሰሉን ተግዳሮት ለመፋለም አለመሞከርና አለመሻት ወደ ጥልቁ የሚያስወርድ ውድቀት  ነውና።

በአማራ፣ በኦሮሞ፣ በቤኒሻንጉል እና በደቡብ ክልሎች ላሉ ክርስቲያን ወንድሞች እና እኅቶች እንባዬን አነባለሁ። ካልረፈደና መማር የምትሹ ከሆነ ትማሩበት ዘንድ ኃይል ከማን ጋር እንደሆነ ታዩት ዘንድ ግድ ይሆናል። እንግዲህ ያው ዛሬ በጌታችን የዕርገት ዕለት የአዲስ አበባውን መስቀል አደባባይን በአህዛብ አስነጠቃችሁት፤ ለምን? ለራሳችሁም፣ ለልጆቻችሁም፣ ለወንድሞቻችሁና እኅቶቻችሁም ለአምላካችሁም መቆም/መኖር ስላቃታችሁ እኮ ነው። አዎ! ለጌታችን ካላችሁ ፍቅር ይልቅ ለትግራዋይ የጽዮን ልጆች ያላችሁ ጥላቻ ጠንክሮባችኋል እኮ፤ እዬዬ! እዬዬ! እዬዬ!

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

“ናይ ጎይታና ዕርገት”| ኣብ ኣክሱም ጽዮን ናይ ሊቃውንቲ ማህሌት | የጌታችን ዕርገት ፪ሺ፲፪ ዓ.ም በአክሱም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 10, 2021

ዕርገት፤ በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡

በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪-፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡

በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡- ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡- ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡

በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል (ትርጓሜ ወንጌል)፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩-፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፤›› በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በኾነ ቋንቋ የጌታችንን ወደ ሰማይ ማረግና ለሐዋርያት የሰጠውን አምላካዊ ትእዛዝ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡

ኖርንም ሞትንም የክርስቶስ ነንና ዘላለማዊ ሕይወትን እንወርስ ዘንድ አምላካችን ይርዳን። ልዑል እግዚአብሔር በኑሮአችን ሁሉ ባርኮን፤ ቀድሶን፤ በእርሱ ፈቃድ እንድንኖር ይርዳን። የምንሻትን መንግስተ ሰማያትን ያወርሰን ዘንድ የእናቱ የድንግል ማርያም አማላጅነት፤ ስለ እርሱ ክብር ሲሉ ሕይወታቸውን ሰውተው ያለፉት ቅዱሳን ሰማዕታት ምልጃ እና ጸሎት አይለየን አሜን።

_________________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, War & Crisis | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: