ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል እንዴት በእነዚህ እናቶች ላይ ሊዘምት ይችላል? | አዲስ የአክሱም ምሕላ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 9, 2021
ሕጻናቱ እንዴት ያስደስታሉ!😊😊😊
ዛሬ ጽኑና ጠንካራ ክርስቲያኖች የሆኑ እናቶችና አባቶች፤ እንኳን በሌላው ዓለም በኢትዮጵያ እንኳን ተፈልገው አይገኙም። ከእነዚህ እናቶችና ሕፃናት ውጭ ማነው ለኢትዮጵያ እና ለመላው ዓለም ያለመታከት ለዘመናት እንዲህ ጸሎት የሚያደርስ? የትኛዋ እናት?
☆ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ?
☆ መዓዛ አሸናፊ?
☆ ስንቅነሽ እጅጉ?
☆ ሙፈሪያት ካሚል?
☆ አስቴር ማሞ?
☆ አይሻ መሀመድ?
☆ ብርቱካን ሚደክሳ?
☆ ሊያ ታደሰ?
☆ ዳግማዊት ሞገስ?
☆ ፊልሳን አብዱላሂ?
☆ ሂሩት ካሳው?
☆ አዳነች አቤቤ?
☆ ሂሩት ወልደ ማርያም?
☆ ዝናሽ ታያቸው?
መቼስ የአክሱም ጽዮንን እናቶች እንደ ዓይን ብሌኑ እየተንከባከበ ከመጠበቅና በዚህም ቅዱስ ተግባራቸው ከማመስገን፣ ከመደስትና ከመበረታታት በቀር ሊቀና እና ሊናደድ ብሎም ጦር ይዞ ሊዘምትባቸው የሚሻ ፍጡር በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈ የዲያብሎስ ጭፍራ ብቻ ነው።
✞✞✞[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፥፭]✞✞✞
“በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።”
በሌላው ዓለም እኮ ይህ አይታይም/አይታወቅም። ምን ያህል መታደል እንደሆነ እኮ ብዙዎቻችን አላውቅነውም። እስኪ በየትኛው መላው ሕዝብ ለሰባት ወራት ያህል እየተሳደደ፣ እየተደፈረ፣ እየተገለለ እና እየተጨፈጨፈ ይህን ዓይነት የእምነት ጥንካሬና የምግባር ጽናት የሚያሳየው? የአቶ ደመላሽ እርስት አመላሽን እና የሁሉም “ኬኛ”ን ስጋዊ ምኞት ምን ያህል እርቀት እንደወሰዳቸው አየነው እኮ ነው። በኤዶማውያኑም ሆነ በእስማኤላውያኑ ዓለም እኮ ማህበረሰባቱ እንኳን ይህ ሁሉ ግፍ ደርሶባቸው፤ የዕለት ቡናቸውን ካጡ እንኳን ልጆቻቸውን የፈንጅ ቀበቶ አስታጥቀ ወደ ፓርላማ ይልኳቸዋል ፤ በሶማሊያ፣ በሚነሶታ እና በፍልስጤም የምናየው እኮ ይህን ነው።
__________________________________
Leave a Reply