Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for June 6th, 2021

❖ ይእከለናባ! ❖ | ዘማሪት ትርሃስ ገብረ እግዚአብሔር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 6, 2021

✞✞✞[ድጕዓ ኤርምያስ ምዕራፍ ፫፥፵፰]“ብጥፍኣት ሕዝበይ ካብ ዓይነይ ከም ማይ ርባ ንብዓት ይውሕዝ ኣሎ።”

✞✞✞[ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫፥፵፰] “ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች።”

“ደጕዓ” የሚለው የትግርኛ ቃል “ሰቆቃው” ማለት መሆኑን ዛሬ ተማርኩስለ ዘማሪት እኅታችን ትርሃስ ገብረ እግዚአብሔር ከሰማሁ በጣም ቆየሁ፤ እስኪ ዛሬ ባለ እግዚአብሔር ነውና ትርሃስን ልፈልግ ስል ይህን ድንቅ መዝሙር አገኘሁና እምባዬ መጣ። ከሁለት ቀናት በፊት በዕለተ መድኃኔ ዓለም “መልክአ መድኃኔ ዓለም”ን ለማንበብ ወደ በረንዳ ስወጣ ሁለት ነጫጭ እርግቦች መጥተው ደረጃው ላይ አረፉ፤ ያኔም በደስታና በመገረም እምባዬ መጣና መልክ አ መድኃኔ ዓለምን ሳነብ የሚከተለው አንቀጽ ትኩረቴን በይበልጥ ሳበው፤

❖❖❖“ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ አቤቱ ከችግርና ከፈተና አድነኝ፣ አባትህም ‘በምስሕ ደብረ ጽዮን‘ በሚያደርገው ታላቅ የምሳ ግብዣ ላይ ይዘኽኝ ግባ፣ ከአንተ በቀር ሌላ የማውቀው ዘመድ የለኝምና።”

እንግዲህ ወዲያው ብልጭ ብለው የታዩኝ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ነበሩ። “ምን ሊሆን ይችላል?” ብዬ በመጠየቅ እስካሁን በማሰላሰል እና መልሱን ለመገመት በመሞከር ላይ ነኝ። በጣም ይገርማል!

ባለ እግዚአብሔር ሆይ በዕለተ ቀኑ ሐገራችን ኢትዮጵያን ከነገሡባት እርኩስ ጠላቶቿ አድነህ ስላም አድርግልን፣ በትግራይ የሚሰቃዩትን አባቶቻችንን፣ እናቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንን እና እኅቶቻችንን ሁሉ ጠብቅልን፣ ለታመሙት ምሕረት ላጡት ማግኘቱን፣ በስደት ዓለም ያሉትንም በያሉበት ጠብቅልን። መልካም ዕለተ ስንበት፣ መጭዎቹንም የተባረኩና የተቀደሱ ሳምንታት፣ ወራት እና ዓመታት አድርግልን።❖

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 6, 2021

✞ “አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፤ ባሪያዎችህም ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና።”✞

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፩]✞✞✞

፩ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።

፪ በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ።

፫ ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ መቃጠያ ተቃጥለዋልና።

፬ እህል መብላት ተረስቶኛልና ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ።

፭ ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ።

፮ እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ።

፯ ተጋሁ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ።

፰ ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም ተማማሉብኝ።

፱ አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና፥

፲ ከቍጣህና ከመዓትህም የተነሣ፤ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።

፲፩ ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።

፲፪ አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘላለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።

፲፫ አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፤

፲፬ ባሪያዎችህም ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና።

፲፭ አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፤

፲፮ እግዚአብሔር ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።

፲፯ ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።

፲፰ ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለእግዚአብሔር እልል ይላል፤

፲፱ እግዚአብሔር ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና፤

፳ የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ ሊገድሉ የተፈረደባቸውን ያድን ዘንድ፤

፳፩ የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ፤

፳፪ አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለእግዚአብሔር ይገዙ ዘንድ።

፳፫ በኃይሉ ጎዳና መለሰለት። የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ።

፳፬ በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።

፳፭ አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።

፳፮ እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል፤

፳፯ አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።

፳፰ የባሪያዎችህም ልጆች ይኖራሉ፥ ዘራቸውም ለዘላለም ትጸናለች።

_____________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: