Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

አህዛብ በትግራይ ላይ የሚያካሂዱትን ጭፍጨፋ በአማራ ላይ አድርገውት ቢሆን ኖሮ ትግራዋያን ለአማራ ሲሉ ደማቸውን ባፈስሱ ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 1, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

አዎ! ምንም ጥርጥር የለኝም! የትክክለኛው ኢትዮጵያዊነትና የክርስቲያን ማንነት መገለጫ ይህ ነውና።  እነርሱም ይውቁታል፤ ግን እንደ ሞኝነት ወይም ጨቅላነት አድርገው ቆጥረውታል።

👉 የኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ስንቃኝ እንኳን፦

🔥 ታላቁ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ ዮሐንስ ለአማራ እና ለተዋሕዶ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ሲሉ መተማ ላይ አንገታቸውን ሰጥተዋል። ኦሮማራው ንጉሥ አፄ ምኒሊክ ግን አፄ ዮሐንስን በመካድ ካስገደሏቸው በኋላ፤ ለአህዛብ ዕውቀትና ጥበብ ሲሉ የአምላኳ እግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓት የተወችውን/የካደችውን ዛሬ የምናያትን ኢትዮጵያ ዘስጋን መሠረቷት። ስጋዊ የዲቃላ ማንነትና ምንነት ያመጣብን መዘዝ!

🔥 ታላቁ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ራስ አሉላ አባ ነጋ በብዙ ጦርነቶች፤ በተለይ በአድዋው ጦርነት ከአገር ወዳዱ የትግራይ ሕዝብና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጎን ሆነው ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት አድነዋታል።

🔥 በዘመነ አፄ ኃይለ ሥላሴ ደግሞ የትግራይ ሕዝብ በኦሮማራው ንጉሥ ጋባዥነት ከየመን በመጡ የብሪታኒያ አውሮፕላኖች ተጨፍጭፎ፣ ሰው ሰራሽ በሆነ ረሃብና በ በሽታዎች እንዲረግፍ ተደርጎ ለኢትዮጵያ ብዙ መስዋዕት በመክፈል ወራሪ ኢጣልያ ለሁለተኛ ጊዜ እንድትባረር ተደርጋለች።

🔥 በዘመነ ደርግ አሁንም የትግራይ ሕዝብ በሶቪየት እና ኩባ አውሮፕላኖች ተጨፍጭፎ፣ በረሃብ በሰው ሰራሽ ረሃብና በሽታዎች እንዲረግፍ ተደርጎና ብዙ ልጆቹን ከሰዋ በኋላ፤ የአማራ ወጣቶችን እና ተዋሕዷውያንን በየመንገዱ ሲረሽን የነበረውን የመንግስቱ ኃይለ ማርያም የኦሮሞ አገዛዝ ገርስሰውታል።

🔥 በዘመነ ኢህአዴግም የእግዚአብሔርን ሥርዓት በሚጻረረውና ሉሲፈራዊ በሆነው በብሔር ብሔረሰብ እኩልነት እና ዲሞክራሲ ቅብርጥሲ ርዕዮተ ዓለምስም ፋሺስታዊውን የአህዛብ ኦሮሞዎችን የበላይነት ባነገሠው በአራተኛው እና በመጨረሻው የኢትዮጵያ ዘስጋ ሥርዓት እንኳን ከማንኛውም የኢትዮጵያ ጎሳ እና ነገድ በበለጠ መስዋዕት እየከፈለ ያለው ትክክለኛዎቹ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት የትግራይ ሕዝብ እንደሆነ ግልጥ ብሎ እያየነው ነው።

💭 የኢትዮጵያ የጥፋትና የውድቀት ምስጢር የተገለጠበት የእግዚአብሔር ቃል በሁላችንም ፊት ምስከር በሆነበት በዚህ በእኛ ዘመን የእግዚአብሔር የመጨረሻው ፍርድ በዚህ የጥፋት ዙፋን ላይ ይሆናል ማለት ነው። በሌላም አገላለጽ የሞትና ባርነት አምልኮ የአራት ትውልድ ዕድሜ ያህል በተቀደሰችው ምድር ላይ ቆይቷል ማለትም ይሆናል። ይህም ማለት አሁን ያለውን የእኛን ትውልድ ፩/1 ብለን ወደኋላ ፪/2፣ ፫/3 እና ፬/4 ትውልድ ስንቆጥር ባለው ጊዜ ውስጥ ይህ የጥፋት አምልኮ ወደ ምድሪቱ ገብቷል ማለት ነው። ከሶስትና አራት ትውልዶች በፊት ነው የሉሲፈር ዙፋን በኢትዮጵያ የቆመው። አሁን ያለንበትን ትውልድ አንድ ብለን ተነስተን ወደኋላ ሶስትና አራት ትውልዶች ስንቆጥር ይህ የዲያብሎስ አምልኮ በኢትዮጵያ ምድር የተተከለበትንና ይህ ርኩሰት ወደ ምድሪቱ የገባበትን ጊዜ/ዘመን እንደርስበታለን። እዚህ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ የአንድን ትውልድ ዘመን/እድሜ የሚገልጸው በጊዜው ያን ትውልድ ይመራ በነበረው መንግስት የጊዜ ቆይታ (ዘመነ መንግስት) ነው። የትውልዱ ዕድሜ የሚወሰነው በዘመነ መንግስቱ ነው ማለት ነው።

👉 ከዚህም በመነሳት ከባዕድ አምልኮ ጋር በቀጥታ የተያያዙትና ለዚህም ተጠያቂ የሆኑት አራቱ ትውልዶች እነዚህ ናቸው፦

፩ኛ. የህወሓት/የኢሕአዴግ/ኦነግ/ብልጽግና/አብን ትውልድ

፪ኛ. የደርግ ትውልድ

፫ኛ. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትውልድ

፬ኛ. የአፄ ምኒልክ ትውልድ

ናቸው።

😈 እንግዲህ ይህ የጥፋትና የሞት ሥርዓተ አምልኮ ወደ ኢትዮጵያ የገባውና የዲያብሎስ ዙፋን በምድሪቱ ላይ የተተከለው በአፄ ምኒልክ ትውልድ ነው ማለት ነው።

✞✞✞[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፳፱]✞✞✞

፲ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።

፲፩ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።

፲፪ እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።

፲፫ እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።

፲፬ ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።

🌞🌞🌞“ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ፤ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ”🌞🌞🌞

✤✤✤ ፃድቁ አባታችን ብፁዕ አቡነ ተክለ ሐይማኖት በመልአኩ ትዕዛዝ ከደብረ ዳሞ ገዳም ወደሌላ ገዳም ለመሄድ ሲነሡ አበምኔቱ አባ ዮሐኒና መነኰሳቱ ሲሸኟቸው አቡነ ተክለ ሐይማኖት አርባ ክንድ ርዝመት ባለው ገመድ ገደሉን ለመውረድ እንደጀመሩ ገመዱን ሰይጣን ከካስማው ሥር ቆረጠባቸው፡፡ ቅዱስ አባታችን ግን በዚህ ጊዜ ስድስት የብርሃን ክንፎች ተሰጣቸውና እየበረሩ ክንፎቻቸውን እያማቱ ሦስት ምዕራፍ ሄደው ሲያርፉ አበምኔቱና መነኰሳቱ አይተዋቸው እጅግ ተደስተዋል፡፡ አባታችን ወደ ትግራይ ሄደው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ገብተው በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ከተቀበሉ በኋላ ተመልሰው ወደ ሐይቅ በመሄድ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ቆብና አስኬማን ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከዚያም ወደ ዋሊ ገዳም ገብተው ከቅዱሳን ጋር ተገናኝተው በትሩፋት ላይ ትሩፋትን በገድል ላይ ገድልን ጨምረዋል፡፡

ከ ፩ሺ፪፻፷፮ እስለ ፩ሺ፪፻፷፯ /1266-1267 .ም ለአንድ ዓመት ያህል የትግራይን ገዳማት በሙሉ በመጐብኘት ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ግብፅም በመሄድ በዚያ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ጎብኝተው መጥተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ “ዳዳ” በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን ፸፭/75 ክንድ የሚረዝመውን ዘንዶ በጸሎት ኃይል በመስቀል ምልክት አማትበውበት በተአምራት ገድለውታል፡፡ በቦታው ላይ በአርባዕቱ እንስሳ ስም ቤተ ክርስቲያን አንጸው ታቦተ ሕግ አስገብተውላቸዋል፡፡ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን አስተምረው መልሰው አጥምቀው አቊርበዋቸዋል፡፡ ✤✤✤

✤✤✤ የፃድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ጸሎታቸውና በረከታቸው ረድኤታቸውና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ፤ አሜን!✤✤✤

💭 ቪዲዮው ውስጥ የተካተቱ መልዕክቶች፦

👉 የወንድማችን የኤድመንድ ብርሃኔ ግሩም እና ፻/100 ትክክለኛ የሆነ መልዕክት (ከወንድማችን ኤድመንድ ብርሃኔ ጋር በአንዳንድ ነገሮች፤ በተለይ ክርስትናን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ኦሮሞዎችን አስመልክቶ በሌሎች ቪዲዮዎች የተላለፉ የማልስማማባቸው ነጥቦች አሉ። ይህን አስመልክቶ እንደ ሁኔታው በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ)

👉 ይህ ቪዲዮ የአማራን/ኦሮማራን “ዲቃላዊ” ማንነትና ምንነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።

ባለፉት ሰባት ወራት የአማራ ልሂቃኑ እንዲህ ሲሉን ነበር፤ ይህ እንግዲህ 0.001%ቱ ብቻ ነው፤ ሌላ የማይቀርብ በጣም ብዙ ጉድ አለ። አብዛኝዎቹ ልሂቃን ሰብዓዊነት + ኢትዮጵያዊነት + መርሕ + ፍቅር + እውነት ምን ያህል እንደራቋቸው ይህን እንደ አንድ ተወካይ ማስረጃ በመቁጠር ቪዲዮውን ከሃዘን ጋር እንመልከት/እናዳምጥ።

👉 በትግራይ ላይ ጦርነት በተከፈተበት ሳምንት

November 8, 2020

👉 አማራው/ኦሮማራው አቶ አያሌው መንገሻ፤

ጦርነቱ ከጀመረ ከሁለት ሳምንት በኋላ November 15, 2020፤

ትግሬዎች/አጋሜዎች፤ እንደ ኦሮሞ አይሸሹም፤ ባሕላቸው እኮ ጦርነት እንጂ ትምህርት፣ ስልጣኔ አስተዋይነት አይደለም፣

👉 እነ ጄነራል አሳምነውን በግማሽ ቀን አሳልፎ የሰጠው “የአማራ ጀግና”አቶ አያሌው መንገሻ፤

ጦርነቱ ከጀመረ ከስድስት ሳምንታት በኋላ፤ December 13, 2020

የትግራይ ሕዝብ የጦርነት ባሕል የለውም፤ ባሕሉ ክህደትና ልመና እንጂ ውጊያ አይደለም!

👉 May23, 2021

ሜሪካ በግራኝ ላይ ማዕቀብ በመጣሏ “ራያ እርስቴ” አማራዎች/ኦሮማራዎች አዘኑ፣ ለምን አሜሪካ ለትግራዋይን ተቆረቆረች በሚል የእቃ እቃ ኩርፊያ ሃዘን ውስጥ ገቡ የትግራይን ንጹሐን ሕዝብ ሰቆቃ ላለማንሳትና ከ “ወገናቸው” ጎን ላለመቆም ምን ያህል እራሳቸውን እንደሚያስጨንቁ።

________________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: