Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

በስቅለት ዕለት የብጹዕነታቸውን ድምጽ ለማፈን ተሞክሮ ነበርን? | ኢሬቻ በላይ ምን ይሠራ ነበር?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2021

ባለፈው የጌታችን የስቅለት ዕለት ከቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ ስርጭት ወቅት የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን መልዕክት ለማፈን ድምጽ /ኦዲዮ-አርታኢው ድምጹን “ምን ሊሉ ነው?” በሚል ፍርሃት እየተከታተለ ለማገድ/ለመዝጋት ሲሞክር እንደነበር ሆኖ በወቅቱ ተሰምቶኛል። ብዙዎችም፤ “ምነው ተቋረጠ? ድምጹ ምን ሆነ?” ብለው በቻት ክፍል ሲጽፉ ይነበብ ነበር።

ብጹእነታቸው መልዕክታቸውን ሳይጨርሱ ምስሉም ድምጹም ከቆመ/ከቀዘቀዘ በኋላ የዋቄዮ-አላህ-አቴቴ ጭፍራን አርዮስ-ኢሬቻ በላይን አመጡት፤ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥም በኢንተርኔት የቀጥታ ስርጭት ላይም የነበሩት ምዕመናኑም ሁሉ ተረበሹ፣ ኩምሽሽ! አሉ።

ኢሬቻ በላይ ከሚያነባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ለመረዳት እንደሞከርኩት፤ አውሬው በላይ “… የኢትዮጵያ ችግር የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ነው፤ በትግራይ ሰላም አይኖርም፣ ልጆቻቸው ያልቃሉ፣ ሰዎች ይራባሉ…ኢትዮጵያም ትፈርሳለች…”

የሚለውን መልዕክት ለማስተላለፍ የሞከረ ይመስላል፤ “አቡነ ፋኑኤል” የተባሉት “አባትም” የአርዮስን ፈልግ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ናቸው። ወዮላቸው!

አርዮስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር “ወልድ ለአብ የመጀመሪያ ፍጥረቱ እንደሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ለወልድ የመጀመሪያ ፍጥረቱ ነው” ይል ነበር፡፡

ይህን የአርዮስን ክሕደት የሰማው የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስን አስጠርቶ የሚያስተምረው ትምህርት ሁሉ የተሳሳተ መሆኑን ገልጾለት ከስሕተቱ ተመልሶና ተጸጽቶ ከቅዱሳን አበው ሲተላለፍ በመጣው በኦርቶዶክስ እምነት እንዲጸና መከረው፡፡ አርዮስ ግን ከአባቱ ከተፍጻሜተ ሰማዕት ጴጥሮስ የተሰጠውን ምክር ወደ ጎን በመተው የክሕደት ትምህርቱን በሰፊው ማስተማር ቀጠለ፡፡ ይህንን የተመለከተ ያ ደግ አባት አርዮስን አውግዞ ከዲቁና ማዕረጉ ሻረው፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት እንደሚለው፣ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስን ያወገዘው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በራእይ ተገልጦለት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነው፡፡

በአንድ ሌሊት በራእይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ ወጣት አምሳል እንደ ፀሓይ የሚያበራ ረጅም ነጭ ልብስ (ቀሚስ) ለብሶ ለቅዱስ ጴጥሮስ ይታየዋል፡፡ ልብሱ ለሁለት የተቀደደ ሆኖ ቢያየው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ ጌታን ‹‹መኑ ሰጠጣ ለልብስከ፤ ልብስህን ማን ቀደደብህ?›› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ጌታም ‹‹አርዮስ ልብሴን ቀደደብኝ›› ብሎ መለሰለት፡፡ ይኸውም በአባቶች ትርጕም ‹‹አርዮስ ከባሕርይ አባቴ ከአብ ለየኝ (አሳነሰኝ)›› ማለት ነው፡፡ ጌታም አርዮስን ከእንግዲህ ወዲያ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዳይቀበለው አዝዞት ተሰወረ፡፡

👉 ባለፈው ዓመት በትንሣኤ የቀረበ፦

✞“የፋሲካ የጸሎት መርሀ ግብሮችን ያስተላለፈውን የ ”ባላገሩ”ን የሉሲፈር ኮከብ አላያችሁምን?” ✞

__________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: