አቡነ ማትያስ፤ “የትግራይ ሕዝብ ምን ቢያደርጋችሁ ነው ከምድረ ገጽ ልታጠፉት የፈለጋችሁት?”
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2021
እንግዲህ አሁን ቃኤላውያን የዋቄዮ-አላህ-አቴቴ ጭፍሮች የሚቀድማቸው የለምና እንደ ቁራዎች መንጫጫት ይጀምራሉ። እስከ አሁን “አባታችን ይፍቱን!” ሲሉ የነበሩት ሁሉ አሁን “ጁንታችን ይተውን!” ማለት ይጀምራሉ። እንግዲህ ምን ይደረጋል ይቅበዝበዙ እንጅ! ግን ልብ ብለናል፤ ብጹእነታቸውንም ሆነ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ለማነጋገር ወይም ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ የሞከረ/የፈለገ አንድም “ኢትዮጵያዊ” ሜዲያ የለም። ባለፉት ስድስት ወራት ይህን ቃለ-መጠይቅ ያደረጉት ባዕዳውያን ፈረንጆች ብቻ መሆናቸው ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ውርደት ነው። ብዙ የትግራይ ልጆች የሚከታተሏቸውና ኢትዮጵያ ያሉ እንደ “ኢትዮ-ፎረም” + “አውሎ ሜዲያ” ለምን ይህን የቤት ሥራ ሊሠሩ አልቻሉም/አልፈለጉም? ጋዜጠኛ ነን ለሚሉ ሁሉ ከዚህ የበለጠ ትልቅ ዕድልና አጋጣሚ እኮ የለም።
የትግራይ ልጆች ከእነዚህ ሜዲያዎች “ተጠንቀቁ፤ መስማት የምትፈልጉትን እየነገሯችሁ በስሜታቸውና በመንፈሳችሁ እየተጫወቱባችሁ ነው፤ እግረ መንገዳቸውንም ትንሽ የውጭ ገንዘብ ይሰበስቡ ዘንድ ነው” ብያለሁ። እስኪ በቻነሎቹ የአስተያየት መስጫ ሳጥኖች ውስጥ የሚቀመጡትን መል ዕክቶች አንብቡ፤ በተሰራጨው ዜና ላይ ሳይሆን አስተያየት በመስጠት ፋንታ ቻነሎቹን/ባለቤቶቹን “የሚያመልኩ” ነው የሚመስሉት። ተጠንቀቁ እንጠንቀቅ! ባሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ሆኖ ትግራይን በመደገፍ የአረመኔውን ግራኝ አብዮት አህመድን አጀንዳ የማያራምድ ሜዲያ በጭራሽ ሊኖር አይችልም፤ በሃሳቤ ስህተተኛ ብሆን ደስ ባለኝ፤ ግን በኢትዮጵያ ነፃ የሆነ ሜዲያ በጭራሽ ሊኖር አይችልም፤100% እንኳን ትግራይን የሚደግፍ። ዛሬ የትግራይ ሕዝብ ከእግዚአብሔርና ቅዱሳኑ በቀር ማንም አጋርና ወዳጅ የለውምና፤ የስሜት ማስታገሻ ወገኖችን፣ ልሂቃንን፣ ሜዲያዎችን፣ ስልኮችን በመፈለግ ፈንታ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ብቻ መዘርጋት ይኖርበታል።
_______________________________________
Leave a Reply