Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የመናፍቃን ጂሃድ | አባታችን አባ ዘ-ወንጌል ለመናፍቁ ዶ/ር ወዳጄነህ ይህን መልዕክት ሊልኩለት አይችሉም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 7, 2021

💭 ሚያዝያ ፪ሺ፲፫/ 2013 .

አዲስ የዓለም ስርዓት ኢሉሚናቲ የዘመን መጨረሻ ሰይጣናዊ “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ /”

(NWO Illuminati Endtime Satanic “Problem – Reaction – Solution )

/ር ወዳጄነህ በምስጢር ይዞት የነበረውንና ከ አባ ዘወንጌል የደረሰውን ትንቢት ተናገረ”

በእንግሊዝኛ ስለተኮላተፉ፣ ‘ዶ/ር’ የሚል ማዕረግ ስላጠለቁና ፊታቸውንም ለፈረንጅ ስላስመቱ ብቻ ለሕዝባችን የሚያሳዩት ንቀትና አሰልቺው ፍዬላዊ ድፍረታቸው ተወዳዳሪ የለውም። እንደው ይህ ተግባራቸው መቅሰፍቱን እንደሚያመጣባቸው ማወቅ ተስኗቸዋልን? አዎ! ፈሪሃ እግዚአብሔር በጭራሽ የላቸውም እኮ።

አባታችን አባ ዘ-ወንጌል ዶ/ር ወዳጀነህን የሚያውቁት ከሆነ እንኳን፤ አዎ! ብዙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ገደል ይዞ እየገባ ነውና በተለይ አሁን በደንብ ነው የሚያውቁትና የሚያሳድዱት፤ ከዚያ ውጭ “ንስሐ ግባ! ገሃነም እሳት ይጠብቅሃል” ከማለት ውጪ መለኮታዊ ትንቢትና ማስጠንቀቂያ በጭራሽ ሊልኩለት አይችሉም። የአባ ዘ-ወንጌል መልዕክቶች መጀመሪያ ማስተላለፍ የጀመሩት እነ ዘመድኩን በቀለ ናቸው። ዘመድኩን በቀለ እራሱ አይታመንም፤ ምንም እንኳን አባ ዘ-ወንጌል ብዙ ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ቢኖሩም ቅሉ፤ ዘመድኩን በቀለ እንደሚያመቸው አድርጎ መልዕክቶቹን እየቆራረጠ ሲያሰራጭ ሳይ በወቅቱ ይህ ግለሰብ ከጋንኤል ክስረት እና ግራኝ አብዮት አህመድ ጋር ሆኖ የአውሬው አገዛዝ በትግራይ ሕዝብ ላይ፣ በጥንታውያኑ ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ ያቀደውን የጭፍጨፋ ጂሃድ ይደግፍለት ዘንድ በተለይ የትግራይ ተዋሕዷውያንን ህሊና ለማለማመድ ታስቦ የተዘጋጀ መልዕክት ሊሆን እንደሚችል ነው። የትግራይ ተዋሕዷውያን ሲጨፈጨፉ ፣ አክሱም ጽዮንን እና ደብረ ዳሞን ጨምሮ በጥንታውያኑ ገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ውድመት ሲደርስ ቤተ ክህነት እና በተለይ የአማራ ተዋሕዷውያን እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ጸጥ ማለታቸው የእነ ዘመድኩንን መል ዕክት በጽኑ እንደጠራጠራው አድርጎኛል። በተለይ አሁን መናፍቁ ዶ/ር ወዳጄነህ ሲታከልበት ሁሉም ነገር ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስለኛል። ለማንኛውም ጉዳዩ በትግራዋያን ተዋሕዷውያን መጣራት ይኖርበታል፤ በተቀሩት ላይ ተስፋ ቆርጫለሁ!

_____________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: