የይሑዳ አንበሣ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቷል | ጎይታ ተንሢኡ | He Is Risen
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 2, 2021
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
✞✞✞ተነስቷል!✞✞✞
ሰማያት (ሰማያውያን መላእክት) የደስታ በዓልን ያደርጋሉ፤ ደመናት (ቅዱሳን) የደስታን በዓል ያደርጋሉ። ምድር (ምድራውያን ሰዎችም) በክርስቶስ ደም ታጥባ (ታጥበው) የፋሲካን በዓል ታደርጋለች (ያደርጋሉ)። ያከብራሉ (ታከብራለች)። ዛሬ በሰማያት (በመላእክት ዘንድ) ታላቅ ደስታ ኾነ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ የፋሲካን የነጻነት በዓል ታደርጋለች። የትንሣኤያችን በኵር ክርስቶስ ከሙታን ሰዎች ዂሉ ተለይቶ ቀድሞ ተነሣ፤” (ድጓ ዘፋሲካ)።
✞ ✞ ✞በችግር፣ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካም፣ በስቃይና በስደት ላይ ያሉትን አባቶቻችንና እናቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን እንዲሁም ልጆቻቸውን ሁሉ እግዚአብሔር ወልድ ተነስቶላቸዋልና በየሰዓቱ ያስባቸው፤ አሜን።✞ ✞ ✞
✞✞✞ተነስቷል!✞✞✞
ተነስቷል ጌታ ተነስቷል
ከሙታን መሃል የለም ጌታ ተነስቷል
ከሙታን መሃል የለም ክርስቶስ ተነስቷል
በመቃብር ተኛ ተነስቷል
ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ……….
ሞትን አሸንፎ ……….
የዓለም መድኀኒት ……….
ግርማን ተጐናጽፎ ………
ይኸው ተነሳልን ………
ሞትን አሸንፎ መውጊያውን ሰባብሮ
ተነስቷል ክርስቶስ ጠላትን መዝብሮ
በሞት ያሸለበው ተነስቷል
የሞት ባለጸጋ ……….
የትንሣኤው በኩር ………..
አልፋና ኦሜጋ ……….
ግርማን ተጐናጽፎ ………
እሁድ በማለዳ ……..
ማኅተሙን ተፈታ ድንጋዩም ደቀቀ
ሲኦልም ተሻረ ዲያብሎስ ወደቀ
ሞትና መውጊያውን ተነስቷል
ከጥልቁ ጣለልን ………
የልባችን መብራት ………
ይብራ ለአምላካችን ……….
ወተንሥአ እንበል ………..
ሲኦል ተሻረልን ………..
ትንሣኤው ልዩ ነው ………..
የመከራ ቀንበር ከእኛ አርቆልናል
የሞት ኃይልን ሰብሮ ጌታችን ተነስቷል።
[፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፲፭]
፶ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ። ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም።
፶፩-፶፪ እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበት ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።
፶፫ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
፶፬ ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ። ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።
፶፭ ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?
፶፮ የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤
፶፯ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
በዐቢይ ጾም አጋማሽ በደብረ ዘይት/ዘመነ ሃጋይ ባሰብነው የጌታችን ዳግም ምጽአት መሠረት ጌታችን በታላቅ ክብርና በልዕልና እንዲሁም እጅግ በጣም በሚያስፈራ ግርማ ለሁለተኛ ጊዜ በቅርቡ ለፍርድ ይመጣልና ([ራዕይ ፳፪፥፲፪] እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።)ሁላችንም የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንያዝ። በተለይ በክርስቲያኖች ላይ ግፍ እየሠሩ ያሉት፤ በትግራይ/አክሱም ጽዮን ጭፍጨፋውን ዛሬም በማካሄድ ላይ ያለው ከሃዲ ትውልድ ለመጭው የፍርድ ቀን እራሱን ያዘጋጅ። ዝም ያለ ሁሉ የዚህ ከሃዲ ትውልድ አባል ነው። በአክሱም ጽዮን ብቻ አንድ ሺህ ምዕመናን ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፤ የሰይጣን ጭፍሮች የሆኑት አረመኔ ገዳዮቻቸው ግን ተገቢውን ፍርድ ያገኛሉ። አንድ ሺህ የዋልድባ መነኮሳትን ያንገላቷቸው፣ ያፈናቀሏቸውና የገደሏቸው በዚህም ኢትዮጵያ ለአንድ ሺህ ዓመታት ርቃኗን እንድትቀር፣ እንድትዋረድና እንድትወድቅ ያደረጓትና ለጉዳዩም ተገቢውን ትኩረት ለመስጠት ያልፈለጉት ግብዞች ሁሉ ምን ዓይነት ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ከእኔ ይልቅ እነርሱ እራሳቸው የተሻለ ያውቁታል።
በትግራይ አክሱም ጽዮን ላይ የፀረ–ክርስቲያን ዘመቻ/ጂሃድ በመክፈት እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ጭፍጨፋውን፣ ደፈራውን፣ ማሳደዱን፣ ዘረፋውንና ጥላቻውን ያለምንም ሃፍረትና መጸጸት ቀጥለውበታል። ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ኢ–አማንያን፣ አህዛብና መናፍቃን የዋቄዮ–አላህ ጭፍሮች የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ከተነሳሱ በዛሬው የፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት ስድስተኛ ወር ሞላቸው።
👉 እነዚህ ወንጀለኞች፤
❖ በአክሱም ጽዮን ላይ፣
❖ በዋልድባ ላይ፣
❖ በደብረ አባይ ላይ፣
❖ በደንገላት ቅድስት ማርያም ላይ፣
❖ በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ላይ፣
❖ በውቅሮ አማኑኤል ላይ፣
❖ በዛላምበሳ ጨርቆስ ላይ፣
❖ ገዳም ማርያም ውቅሮ እምባስነይቲ
❖ የቸሊ/ግጀት ከሁለት መቶ በላይ ተዋሕዷውያን ሕፃናትና ወጣቶች ጭፍጨፋ!
❖ የእንዳ ማርያም መድኃኒት አዲ ዳዕሮ ጭፍጨፋ
❖ በሌሎች ባልተወራላቸው የትግራይ ዓብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማት እንዲሁም ሌሎች ቦታዎች ላይ
እጅግ በጣም ከባድ ወንጀል ሠርተዋልና የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፤ እረፍት የላቸውም፣ እንቅልፍ አይኖራቸውም፤ እንደ ቃኤል እየተቅበዘበዙ ያችን ቀን ይጠብቁ ዘንድ ተወስኗል።
እንግዲህ ይህን በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ወንጀል እየሰሩ ስላሉትና “እግዚአብሔር አያይም፤ አይ እርሱ እንዴትስ ያውቃል? ምን ቸገረን?” እያሉ በክህደት፣ በአመጽና በትዕቢት መንፈስ የሚኩራሩት ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ኢ–አማንያን፣ አህዛብና መናፍቃን የዋቄዮ–አላህ ወንጀለኞች ሁሉ የዘሯትን በቅርቡ ያጭዷታል፤ የጭንቀት ቀናት በሮቻችሁን ያንኳኳሉ፤ የበቀል ጊዜም እየመጣ ነው፤ ወዮላችሁ! ወዮልን!
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፮፥፳፯]
“የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።”
[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩፥፳፪፡፳፯ ]
“የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና። በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤ በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።
በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።”
✞✞✞የዘ/ት ምርትነሽ ጥላሁን “ሂዱ ንገሩ ለዓለም”✞✞✞
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና
ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው ብብገና
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን የምንዘምረው
መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው
ዳንን የምንለው
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘላለም
በመቃብር ሞት ይይዝህ ዘንድ ከቶ አልቻለም
ኃይለኛውን በኃይል አስረኽው ላይፈታ
ዘመርንልህ አሸናፊ ነህ የኛ ጌታ
ከፍ በል በዕልልታ
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
ሞቶ ማዳን ለማን ተችሏል ከአንተ በቀር
ጌትነትህ ስራህ ይኖራል ሲመሰከር
ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ
ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጠላት ፈራ
ዕፁብ ያንተ ሥራ
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
መስክሩለት የምሥራች ነው ታላቅ ዜና
መለክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና
ከተማዋ አንዳች ሆናለች በሌሊቱ
በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወህኒ ቤቱ
ከበሮውን ምቱ
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
______________________________________
Leave a Reply