ጸሎተ ሐሙስ / የነጻነት ሐሙስ ፪ሺ፲፫ ዛሬ በኢየሩሳሌም፤ እስራኤል | ግብጾች የኢትዮጵያን ገዳም አወኩት!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2021
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
👉 ማክሰኞ 👉 ሐሙስ 👉 ዓርብ 👉 ቅዳሜ 👉 እሑድ
በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ገዳም ግብጾች “መውረስ አለብን” እያሉ አሁን ኢትዮጵያውያን ምዕመናንን በመበጥበበጥ ላይ እንደሆኑ ከደቂቃዎች በፊት የደረሰኝ መልዕክት ይጠቁማል። ዋው! በእርግጥም አጋንንቱ ተለቅቀዋል!
ሕማማተ እግዚእ ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ በገብርኤል፣ ጸሎተ ሐሙስ በማርያም፣ ዓርብ ስቅለት በኡራኤል፣ ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ) በጊዮርጊስ እንዲሁም እሑድ ትንሣኤ በተክለ ሐይማኖት ዕለታት ሲውሉ ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ (፲፱፻፵/1940ዓ.ም)ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ዘንድሮ በትግራይ ሕዝብና በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነት የታወጀው በእነዚህ ቀናት ነበር፤ በቅዱስ ጊዮርጊስና በአባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለታት።
👉 በ ፲፱፻፵/1940ዓ.ም የታዩ ቁልፍ ታሪካዊ ክስተቶች፦
☆ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ ነፃ ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጥ ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ፤ በ፲፱፻፶፩/1951 ዓ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ (ገብረ ጊዮርጊስ)ቀዳማዊ ሆኑ።
☆ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና ትቀላቀል ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ
☆ አይሁዶች በ ፪ሺ፱፻/2900 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበረ እና ሉዓላዊ ሀገር በመሆን ለእስራኤል ነፃነት አወጁ – እስራኤል አገር ሆነች
👉 እነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች ምንን እየጠቆሙን ይሆን?
❖ በኦሮማራው ንጉሥ አፄ ምኒልክ የተለያያኡት የትግራይ እና ኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ሰሜን ኢትዮጵያውያን መዋሐድና አንድ መሆን?
❖ የሰሜን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስረታ?
_______________________________________
Leave a Reply