Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2021
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 28th, 2021

ሰሙነ ሕማማት – ረቡዕ ፤ የይሁዳ ክህደት፥ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2021

ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ተስጥቷል። ይሁዳ ለ፴/30 ዲናር ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው፤ ከዚያም ዲናሩን መልሶ እራሱን አጠፋ። የዘመናችን ሰቃልያን የሆኑት ኦሮማራዎቹ የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ደግሞ “አክሱም ጽዮን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያፈራችውን እውቀት፣ ስልጣኔና ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ፣ አሳልፎ ለመስጠትና ለማውደም ጊዜው አሁን ነው” ብለው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ከሆኑት አህዛብ፣ መናፍቃንና ግብረ-ሰዶማውያን ጋር ተባበሩ። በዚህም በዚያም ትልቅ ክህደት እና ስቅለት። በተለይ ተዋሕዶ ክርስትናን የተቀብሉትና ማሕተብ ያጠለቁት አማራ ወገኖች ክህደት ታሪክ የማይረሳው ነው፤ ብዙ ዋጋም የሚያስከፍላቸውና ከሌሎቹ ሁሉ የከፋው ክህደት ነው። ከይሁዳ ይልቅ የጴጥሮስ ዓይነት ክህደት ያድርግላቸው።

የአስቆሮቱ ይሁዳ ክህደት + የቃኤል ቅናት = ☠️

አወቁትም አላወቁትም፤ ዛሬ በአማራዎችና ኦሮሞዎች ህብረት በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጂሃዳዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ የመጨረሻው ግብ፤ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ትግራዋያንን ከአኩም ጽዮን አጽድቶ የሕይወት ዛፍ እና ጽላተ ሙሴ የሚገኙበትን ቅድስት ምድር ለተለከፉት ባዕዳውያኑ ውሾች ማስረከብ ነው። አዎ! ኢትዮጵያን/አክሱም ጽዮንን ለባዕዳውያኑ ሉሲፈራውያን ለማስረከብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። እስኪ እናስበው! ዋው!

በሰባዎቹ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ ድርቅና ረሃብ ፈጥረው በዚህ አካባቢ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሃገራት፤ በተለይ ብሪታኒያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሰራዊቶቻቸውን በእርዳታ ስም አስፍረው እንደነበር እናስታውስ። ከዚያ በሰማኒያዎቹ እና በባድሜው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪዎች” እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ዛሬም ዓለም የተራቡ የትግራይን ሕፃናት ምስሎች በበቂ እንድታይ ከተደረገች በኋላና የተረፉትንም ትግራይ ወገኖቼንም በስደት የተቀደሰችውን ምድር እየለቀቁ እንዲወጡ (የአውሮፓን እና አሜሪካን ድንበሮች ይከፍቱላቸዋል፤ ከጥቂት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚገኙት የዓለማችን ቦታዎች በቀር አውሮፓና አሜሪካ ሌሎችም አኅጉራት ይጠፋሉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል) ከተደረጉ በኋላ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሠራዊቶች በትግራይ ይሰፍራሉ።

ገና ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት “ኔቶ በአፍጋኒስታን የሚገኘው ለኢትዮጵያ ለመለማመድ ነው፤ ተመሳሳይ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ስላላቸው…” በማለጥ ጽፌ ነበር። ምዕራባውያኑ እዚያ መስፈር ከጀመሩ በኋላ ቀስ በቀስ ዜጎቻቸውን ማስገባት ይጀምሩና በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያኑም ተዋሕዶ ክርስቲያኖቹም እኛ ነን” በማለት እያታለሉና ደማቸውን እያፈሰሱ ለብዙ ሺህ ዓመታት ጠብቀውት የነበረውን ብኩርናቸውን በምስር ወጥ እንዲሸጡ ብሎም የመንፈስ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እየተነጠቁ “ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን” ቀስበቀስ እንዲከዱ ይደረጓቸውን “የቀድሞ ኢትዮጵያውያን” “አናስገባም!” ብለው ከኢትዮጵያ ድንብር ይመልሷቸዋል። ይህ ትንቢት ሳይሆን የሉሲፈራውያኑ ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተልዕኳቸውን እንደሚያጨናግፈው አልጠራጠረም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ደንቆሮነት፣ ስንፍና እና እንደ ግራኝ ያሉትን የውስጥ ጠላታቸውን በሰዓቱ ለማስወገድ ባለመድፈራቸው ብሎም አክሱም ጽዮንን ለመከላከል ባለመሻታቸው ብዙ መስዋዕት ይከፍሉ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ከሃዲዎቹ ኦሮማራዎች!

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: