ወቅታዊ ጥሪ ለአማራ | እስከ ጌታችን ስቅለት ድረስ ሚሊሻዎቻችሁን ሁሉ ከትግራይ አስወጡ!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2021
ግን ምን ያህል ቢወድቁ ነው ተዋሕዶ የትግራይ አባቶቻቸውንና እናቶቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ለመውጋት ጦራቸውን ወደ አክሱም ጽዮን የላኩት? መንፈሳዊ ዓይናቸው ምን ያህል ቢታወር ነው ይህን ግልጽ የሆነ (ዓለም እየተሳለቀችባቸው ነው)ትልቅ ስህተትና ከባድ ኃጢዓት አይተውትና ተረድተውት፤ “አይ ተሳስተናል፣ ከባድ ኃጢዓት ሠርተናልና ተጸጽተናል ስለዚህ አሁን ጦራችንን ባፋጣኝ ከትግራይ እናውጣ” ማለት እንኳን የተሳናቸው? ምን ያህል ሕሊና–ቢስ ቢሆኑ ነው“አይሆንም! ልጆቻችን ወደ ትግራይ ልከን አናስጨረስም! እንዲያውም ልጆቻችን ጎንደርን፣ ጎጃምን፣ መተከልን፣ ግድቡን እና አጣዬን መከላከል አለባቸው፣ ወደ ጎረቤት ትግራይ ሄዶ ለጥቃት የሚሰማራ በቂ ጦረኛ የለንም፤ በኋላ ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል!” በማለት ብልጠትንና ብልሕነትን ማሳየት ያልቻሉት? አማራም ‘ቧ!ያለው በሬ ግራኝም ወደ እንቁራሪትነት የተለወጠ በሬ?!
☆ፀሐይ ወጣልኝ ለሰላሳ ዓመት እነግሣለሁ ያለው ‘በሬ‘
☆በሶስት ዓመት ውስጥ እንቁራሪት ሆኖ እራሱ ገደል ገባ!
“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው…የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው”። ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ
❖ [መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፮፥፲፮፡፲፱]
፲፮ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
፲፯ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
፲፰ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
፲፱ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
______________________________________
Leave a Reply