የቀን ጅቦች (የግራኝ ሰአራዊት) ንጉሥ አንበሣን (አክሱም ጽዮንን) ከብበው አጠቁት ከዚያ…
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2021
የአባ ዘ-ወንጌልን መልዕክት የ666ቱ ጭፍሮች ለራሳቸው አጀንዳ ያመቻቸው ዘንድ እንዳሰኛቸው ጠምዝዘው ሲያቀርቡት ይታያሉ። 👉 አባታችን አባ ዘ-ወንጌል የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል በማለት ጉዳዩን እነ ዘመድኩን በቀለ ለተከታዮቻቸው በተደጋጋሚ ሲያወሱት ነበር። ስለ አባ ዘ-ወንጌል የተወራው ሁሉ ትክክል አይደለም የማለት ድፍረት የለኝም፤ ሆኖም እራሳችንን መጠየቅ ያለብን፤ “እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድና እንደ ጋንኤል ክስረት እና ገመድኩን ሰቀለ ያሉት ካድሬዎቹ ተዋሕዶ ክርስቲያኑን የትግራይን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ አስቀድመው ያወጡት ጽሑፍ/ስክሪፕት ቢሆንስ? “የራሳችሁ አባት አባ ዘ-ወንጌል የተነበዩት ነውና ጭፍጨፋውንም፣ የዓብያተ ክርስቲያናትና ገዳማቱን ውድመትም ተቀበሉ፤ በሃጢአታችሁ ነውና፤ አሁን ለደህንነታችሁና ብልጽግናችሁ ስትሉ በሉ ጴንጤ ሁኑ” ብለው ተንኮለኛው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል ያረቀቀላቸውን “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” የተባለውን መመሪያ ተከትለው ቢሆንስ? መቼስ ይህን እንደሚያደርጉት አልጠራጠረም።
💭 አባ ዘ-ወንጌል ‘አስተላልፈውታል’ የተባለው መልዕክት እንዲህ ይላል፦
“በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ትወረራለች። ሰላም በማስከበር በሚል ሰበብም በ፪/2 ሃያላን ሀገራት የሚመሩ ሰባት የሙስሊም ሀገራት በኢትዮጵያ ምድር ላይ እሳት ያዘንባሉ። በአሰብ ወደብ ላይ በልዩ ሁኔታ የተከማቸው የጦር መሣሪያ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንደበረዶ ይዘንባል። ብዙ ፍጅትም ይሆናል። ኦርቶዶክሳውያን በያሉበት፣ በየተገኙበት እንደከብት ይታረዳሉ። የኢትዮጵያ ምድር በደም ትጨቀያለች። የደም ጎርፍ፣ የደም አበላ በምድሪቱ ላይ ይፈሳል።”
👉 ሰባቱ የሙስሊም ሀገራት እነ ግራኝ ትግራይን ለመጨፍጨፍ ገና ከሦስት ዓመታት በፊት የሰበሰቧቸው እነዚህ የጅቦች መንጋ ሰራዊት አይደሉምን?
🔥 አማራ
🔥 ኦሮሞ
🔥 መናፍቅ
🔥 እስላም/አረብ
🔥 ኤርትራ
🔥 ሶማሊያ
🔥 ብሔር ብሔረሰቦች
የይሁዳ አንበሣን (አክሱም ጽዮን)ከብበው አጠቁት፤ በመጨረሻም ረዳቱ/ረዳታችን (መንፈስ ቅዱስ) ደረሰለት። ነጫጮቹን እርግቦች አየናቸው?
“ያዘው! በለው! ስቀለው!”ሲሉ የነበሩት መቶ ጅቦች ፈረጠጡ! ሦስቱ አንበሦች ግን አንድ ሆነው ንጉሥነታቸውን አረጋገጡ!
ዲያብሎስ የአክሱም ጽዮን ልጆች የእርሱ አለመሆናቸውን ቆጭቶት እነርሱን ለመጣል ብሎ ለዘመናት በተለያየ መንገድ ተፈታተናቸው[ማቴ.፬፥፫]፡፡ ጌታችንን ከሀገራቸው እንዲሄድላቸውና ወደ ግብጽ እንዲሰደድ እንደ ለመኑት፤ የአክሱም ጽዮን ልጆችንም የክርስቶስ በመሆናቸው ከሀገራቸው እንዲወጡላቸው እያደረጓቸው ነው፤(ማቴ.፰፥፴፬)፡፡ የይሑዳ አንበሣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ጋኔን አለበት”(ሎቱ ስብሐት!)እንዳሉት ለአክሱም ጽዮን ልጆችም የተለያየ ስም እየሰጧቸው በመጥፎ እና በጠላትነት እንዲታዩ አደረጓቸው፤[ዮሐ.፲፥፳]፡፡ የይሑዳን አንበሣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቅንዓት ተነሣሥተው “ይሰቀል ይሰቀል” እንዳሉት፤ እንደዚሁ የክርስቶስ ተቃዋሚው የግራኝ አህመድ የአህዛብ አገዛዝም በተለያየ መንገድ አመካኝቶ ግርግር አንሥቶ፣ መነሻውም ሰሜን ዕዝ እንደ ሆነ ዋሽቶ መንጋ ተከታይ መንጋውን “ያዘው! በለው! ይወገሩ፣ ይቀጥቀጡ! ግደላቸው!” እያስባለ የአክሱም ጽዮን ልጆች የክርስቶስ በመሆናቸው ብቻ እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ገረፏቸው፣ ደፈሯቸው፣ አስራቧቸው፣ ጨፈጨፏቸው[ማቴ.፳፯፥፳፪፡፳፫]፡፡
ገና ከልጅነታችን በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀን ክርስቲያን የሆንን ሁሉ ከእኛ ጋር ያለውን፣ “በኪሳችን የያዘነውን” ተንከባክበን ወደ ውስጥ ከተመለከትን ከውጭ ያለውና አላፊና ሰብዓዊ ከሆነው እርዳታ መጠበቅ አይገባንም/ አያስፈልገንም። ይህ ሰው፣ ይህ ሕዝብ፣ ይህ ተቋምና ድርጅት ለምን ስለኛ መከራ እና ሰቆቃ አልተናገረልንም? ለምንስ ለእርዳታ ከእኛ ጋር አልቆሙልንም? እያልን እራሳችንን የሚያጽናናን፤ ማለትም የሚያጽናን፣ የቅርብ ረዳታችን፣ የመንገዳችን ደጋፊ፣ የነፍሳችንን ሲቃ አዳማጭና የማይለይ ታዳጊ መንፈስ ቅዱስ ሁሌ ከእኛ ጋር አለና ነው። መንፈስ ቅዱስ በማይመረመር ፍርዱ የደሀን ደም ይበቀላል፣ ፍትሕን ይተክላል፣ እውነትን ያነግሳል፣ ሀሰትን ይደመስሳል፣ በኃጢአት የከበሩትን ያዋርዳል፣ ስለጽድቅ የተዋረዱትን ግን ያከብራል።
[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬፥፳፮]
“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”
✞✞✞የሐና ማርያም ወራዊ መታሰቢያ በዓል✞✞✞
[መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፪]
፩ ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች። ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።
፪ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።
፫ አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።
፬ የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል።
፭ ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች።
፮ እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።
፯ እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።
፰ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።
፱ እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።
፲ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
_______________________________________
Leave a Reply